Skip to main content
x

አገር ላጋጠማት ችግር ምን መደረግ አለበት?

አገራችን ባልተጠበቀ፣ በሚደንቅ፣ በሚያሳሳና በሚያሳስብ የለውጥ ምዕራፍ ውስጥ ገብታለች፡፡ አዲሱን ምዕራፍ ያልተጠበቀ የሚያደርገው ከኢትዮጵያ ሕዝቦችና ወጣቶች ትግልና ከገዥው መንግሥት የረገጣና የድቆሳ መስተጋብር ውስጥ ተፈልቅቆ የወጣ በመሆኑ ነው፡፡

የመንግሥት የአጣዳፊ ጊዜ ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣንን እጀ ሰባራ ያደረገው ምንድነው?

ለመላው ዓለም ምሳሌ የሚሆን ሕገ መንግሥትና ፌዴራሊዝም አለን በምትል (እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም ትልም በነበር) ኢትዮጵያ ውስጥ የብሔረሰብ ንቁርያዎች፣ መጤ እያሉ መበደልና መግፋት ሲተካተኩባትና ዋጋ ሲያስከፍሏት፣ በየጊዜውም ሲያስጠነቅቋት ቆይቶ ዓብይን ድንገት የወለደው፣ ዘግናኝ ግድያዎችን የታዩበትና በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ያፈናቀለ ቀውስ ተዘረገፈባት፡፡

የዴሞክራሲ ጮራ እየፈነጠቀ ነው! ወዴት እንደምናመራ ግን እርግጠኛ ነን?

በአገራችን የዴሞክራሲ ጮራ እየፈነጠቀ ነው፡፡ አንዳንዶች ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ፈላጭ ቆራጭነት እየተጠናከረ ሆኖ ይታየቸዋል፡፡ ዕውን እንደዚያ ነው? ይኼንን ለማስባል ያደረሰው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉን ነገር ለኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ምክር ቤት እያስወሰነ አለመሥራቱ ከሆነ፣ ይህ አድርጎቱ የሚገጥመው ከፈላጭ ቆራጭነት ይልቅ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተሰጠው ሕገ መንግሥታዊ ነፃነት ጋር ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር እንዴት አድርገው የፓርላማውን ነፃነት ያግዛሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አዲሱ የአገራችን መሪ ከመሆናቸው ልክ ከአንድ ዓመት በፊት መጋቢት 2009 ዓ.ም. ላይ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል የተባለ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ድንብ የተቋቋመና ተጠሪነቱም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆነ ተቋም ባቀረበው የጥናት ሪፖርት ላይ ተመሥርቶ የተካሄደና በቴሌቪዥንም ለሕዝብ የቀረበ፣ ሌሎች ውይይቶችንም ያስከተለ ውይይት፣ ቀውስ ውስጥ በምትገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ራሱን የቻለ ዜናና ወሬ ሆኖ ነበር፡፡

የምንታገለው ምኞታዊነትና ሕልመኛነት የጋረጠብንን ተላላ ፖለቲካ ነው

ሁለት ዓለማት አሉ፡፡ በአካል የምንኖርበት ተጨባጭ ዓለምና የተምኔት (ፋንታሲ) ዓለም፡፡ ጥንት ከተምኔት ጋር የምንገናኘው በሌሊት ቅዠት፣ በቀን ቅዠትና በእነ ዓሊ ባባ ዓይነት ተረቶች (መናፍስት ጂኒዎች ብዙ ተዓምራት በሚሠሩባቸው) አማካይነት ነበር፡፡

ክፍልፋይ ወገንተኝነትና አፈናቃይነት የፖሊሲ ችግር አይደለምን?

ለዓለም ምሳሌ የሚሆን ሕገ መንግሥትና ፌዴራሊዝም አለኝ የምትለው ኢትዮጵያ ብሔረሰብ ነክ ንቁሪያዎች፣ መጤ እያሉ መበደልና መግፋት ሲያንቀረቅቡን  ቆይተው ድንገት ዘግናኝ ግድያዎች የሚታዩባትና በሚሊዮን የሚደርስ ሕዝብን ያፈናቀለ ቀውስ የሚገዝፍባት አገር ሆናለች፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ጎህ ሊቀድ ነው ልበል?

በዓለማችን ውስጥ ያልተጠበቁ አስገራሚ ድርጊቶች መከሰታቸው ዛሬም ቀጥሏል፡፡ የሰሜን ኮሪያና የአሜሪካ የፍጥጫ ቀረርቶ ወደ ሰላም ጎዳና (የኑክሌር ሙከራ ወደ ማቋረጥና ተቋማዊ አቅም ወደ መነቃቀል አቅጣጫ) ይጠመዘዛል ብሎ የገመተ አልነበረም፡፡

የኢትዮ ኤርትራ ጉዳይ ምን ይሻለዋል?

የኤርትራ መንግሥት/ሻዕቢያ ባድመንና አካባቢውን የወረረው በ1990 ዓ.ም. ግንቦት ወር መጀመርያ ላይ ነው፡፡ ይህ ከሆነ ከ20 ዓመታት በኋላ የካቲት 21 ቀን 1991 ዓ.ም. ከተጠናቀቀው ከዘመቻ ፀሐይ ግባት ከግንቦት 1992 ዓ.ም. ሌላው ግዙፍ ጦርነት ወዲህ ታኅሳስ 3 ቀን 1993 ዓ.ም