Skip to main content
x

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ በምክትላቸው ተተኩ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዷለም አድማሴ (ዶ/ር) ከኃላፊነታቸው ተነስተው በምትካቸው ምክትላቸው የነበሩት ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ ተተክተዋል፡፡

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር የነበሩት አቶ ኢሳያስ ዳኘው ተነስተው፣ በምትካቸው ቺፍ ቴክኖሎጂ ኦፊሰር የነበሩት አቶ አማረ አሰፋ ተተክተዋል፡፡

የካፒታል ገበያ ላይ ያተኮረ ዓውደ ጥናት ሊካሄድ ነው

የፋይናንስ ተቋማት ባለሙያዎች የሚሳተፉበትና በካፒታል ወይም በስቶክ ገበያ አሠራር ላይ ያተኮረ ዓውደ ጥናትና ሥልጠና፣ ተቀማጭነቱ በአዲስ አበባ ከሆነው ሊንከን ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር በሚሠራው ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አስተባባሪነት መካሄድ እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡

ኔክሰስ ሆቴል በ410 ሚሊዮን ብር ያካሄውን የማስፋፊያ ግንባታ  አጠናቀቀ

ኔክሰስ ሆቴል በ410 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ 85 የመኝታ ክፍሎች ያሉት ሕንፃ ግንባታ አጠናቆ ለአገልግሎት ማብቃቱን አስታወቀ፡፡ ሆቴሉ በሁለት ምዕራፍ ያካሄደው ኢንቨስትመንት ከ560 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሆነና የመኝታ ክፍሎቹንም ወደ 115 እንዳደረሰ አስታውቋል፡፡

የግል ባንኮች ትርፍ ከ10.5 ቢሊዮን ብር በላይ ደረሰ

የአገሪቱ የግል ባንኮች በ2010 ሒሳብ ዓመት ከታክስና ከሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ10.5 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፋቸው ታወቀ፡፡ የ16 የግል ባንኮች የ2010 ሒሳብ ዓመት ግርድፍ የሒሳብ ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ ከታክስና ከሌሎች ተቀናሾች በፊት ያገኙት የትርፍ መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ2.7 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ አለው፡፡

ቻይና ለገርቢ ግድብ ፕሮጀክት የብድር ማራዘሚያ ሰጠች

ለሰሜን አዲስ አበባ፣ ሱሉልታና አካባቢው ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውኃ ማቅረብ ያስችላል ለተባለው የገርቢ ግድብ ፕሮጀክት የተገኘው ብድር የመጠቀሚያ ጊዜው በማለፉ የተቋረጠ ቢሆንም፣ የፌዴራል መንግሥት ከቻይና መንግሥት ጋር ባደረገው ድርድር የሁለት ወራት ማራዘሚያ ተሰጠው፡፡

ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን ለመጠቀም እንቅስቃሴ ጀመረች

ግንኙነታቸውን ዳግም እያደሱ የሚገኙት የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች ከሃያ ዓመታት በኋላ የአሰብ ወደብ ሥራ እንዲጀምር ትዕዛዝ ሰጡ፡፡ሁለቱ መሪዎች በሰጡት ትዕዛዝ መሠረት በኢትዮጵያ በኩል የትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ማሪታይም ጉዳይ ባለሥልጣንና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በጋራ ግብረ ኃይል አቋቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለሥልጣን የአነስተኛ ግብር ከፋዮችን አብዛኛውን ቅሬታ መፍታቱን አስታወቀ

ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በመውጣት እንደገና እንደ አዲስ እንዲደራጅ የተደረገው የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለሥልጣን፣ ባለፈው ዓመት ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳውና የቀን ገቢ ግምት ላይ ተመሥርቶ የሚሰላው ታክስ ላይ ሲነሱ የቆዩ ቅሬታዎች ላይ ምላሽ ሲሰጥ መቆየቱን አስታውቋል፡፡