Skip to main content
x

አራት ዓመት ጠብቀው አህጉር የሚሻገሩ ደጋፊዎች

እንዲህ እንደ ዛሬው ቴክኖሎጂ ባልረቀቀበት ዘመን በአራት ዓመት አንዴ ብቅ የሚለውን የፊፋ ዓለም ዋንጫ መመልከት ቀላል አልነበረም፡፡ በሁሉም ዕድሜ የሚወደደው ዓለም ዋንጫ በሁሉም ሰው ልብ  ውስጥ የራሱን ትዝታ ጥሎ አልፏል፡፡ ውድድሩን በቴሌቪዥን መስኮት ለመመልከት የጎረቤቱን ቤት ደጅ ያልጠና አልነበረም፡፡ በተለይ በጊዜው ቴሌቪዥን ያላቸውን ሰዎች የማየት ፍቃድ ለማግኘት ብዙ ትዕዛዞችን መወጣት ያስፈልጋል፡፡

ደደቢት የኢትዮጵያ ክለቦች የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ይለፈኝ አለ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ሁለት አሠርታትን ካስቆጠረው የፕሪሚየር ሊጉ መጀመር ማግሥት ጀምሮ በተለይ የጥሎ ማለፍ ውድድር መርሐ ግብር በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የተጠናቀቀበት ወቅት ለመኖሩ እርግጠኛ መሆን ይከብዳል፡፡ ይባስ ብሎ ጥሎ ማለፉ አሁን ላይ ‹‹የኢትዮጵያ›› የሚለውን ስም ብቻ ይዞ መርሐ ግብሩ ሲደረግ የሚስተዋለው በፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ብቻ ሆኖ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስና የባለሙያው ቅኝት

እግር ኳስ በኢትዮጵያ እንዲህ እንደ አሁኑ ባልዘመነበት በ1910ዎቹ መጨረሻ አካባቢ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ኢትዮጵያ በመጡ አውሮፓውያንና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አማካይነት ቀስ በቀስ እየተስፋፋና እየተለመደ መምጣቱ በዘርፉ የተጻፉ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡

የኮፓ ኮካ ኮላ ብሔራዊ የታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ውድድር ተጀመረ

በዓለም ላይ የታዳጊዎች የእግር ኳስ ፕሮጀክቶች በርካታ ከዋክብት በማፍራት ትልቅ ሚና ሲጫወቱ ይታያሉ፡፡ በቀደመው ጊዜ በየሠፈሩ እየተመለመሉ፣ ለክለብና ለብሔራዊ ቡድኖቻቸው ትልቅ ሚና ከተጫወቱ አንጋፋ ተጫዋቾች መካከል፣ የዓለም የኳስ ንጉሡ ፔሌና ጋሪንቻ ይጠቀሳሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜዎቹ ደግሞ ምትሐተኛው አርጀንቲናዊ ሊዮኔል ሜሲ አይታለፍም፡፡

የዲሲፕሊን መመርያዎች የፍትሕ አካልን ትኩረት ይሻሉ

የእግር ኳስ ሜዳዎች የዲሲፕሊን ጥሰት እሰየው፣ ግፋበት የተባለ ይመስላል፡፡ ልጓም ያዥ፣ ሃይ ባይ ያጣ፣ ለያዥ ለገራዥ አልጨበጥ እስኪመስል ድረስ ሜዳ የሚጀምረው ብጥብጥና ግርግር በየመንገዱና በየመንደሩ መግባት ከጀመረ ሰነባብቷል፣ እንደቀጠለም ይገኛል፡፡ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ለአንዳንዶቹ ፈጣን ለአንዳንዶቹ ደግሞ እየዘገዬ፣ እያቆጠቆጠና ሥር እየሰደደ የመጣውን የስፖርታዊ ጨዋነት  መጓደል ከእንጭጩ ማድረቅ እንዳልተቻለ የሚናገሩ አሉ፡፡

ሉሲዎቹ ከአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ውጪ ሆኑ

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ጋና የ2018 ሴቶች የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫን ታስተናግዳለች፡፡ በማጣሪያው ከጫፍ ደርሶ የነበረው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) በአልጀሪያ አቻው ተሸንፎ ከጋናው የአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆኗል፡፡ ቡድኑ በሜዳውም ከሜዳው ውጪም መሸነፉ ከቁጭት ይልቅ ለመድረኩ የሚያበቃ ሥራ እንደሚያስፈልግ አመላክቷል የሚሉ አሉ፡፡

ለእውነተኛ ለውጥ ከሰው ይልቅ የተቋም ትኩረት ይሻል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ፣ ከብዙ መጓተትና ውጣ ውረድ በኋላ ባለፈው ሳምንት ግንቦት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. መቋጫውን አግኝቷል፡፡ ምንም እንኳን አመራሮቹ ለመጪው አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን ለመምራት ቢመረጡም በቀጣዩ ምርጫ እንዲህ እንደ አሁኑ ዓይነት አላስፈላጊ መፋጨቶች እንደማይፈጠሩ ምንም ዋስትና አይኖርም፡፡

በፌዴሬሽኑ ያላለቀው ምርጫ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ላለፉት ዘጠኝ ወራት በአመራር ምርጫ ውዝግብ ሲናጥ ቆይቷል፡፡ ብዙ ውጣ ውረዶችን ያለፈው ፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ግንቦት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በአፋር ስመራ  በተደረገው ምርጫ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

አዲሱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሚታወቅበት የሰመራው ጉባዔ

ከብዙ ንትርክና አተካራ በኋላ ቀጣዩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እሑድ ግንቦት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ለመምረጥ የጠቅላላ ጉባዔ አባላቱ ሰመራ ላይ ከትመዋል፡፡ በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ጣልቃ ገብነት ምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዳግመኛ ከተዋቀረ በኋላ ውዝግብ የተነሳበትን የዕጩ ውክልናን በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎችን ሲያስተናግድ ቆይቷል፡፡

በወልዋሎ አዲግራት ክለብና መሪው ላይ የተጣለው ቅጣት ሲፀና የአራት ተጫዋቾች ቅጣት ተነሳ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ፣ በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ክለብ ላይ በዲስፕሊን ኮሚቴ ተጥሎ የነበረው ቅጣት ላይ ማሻሻያ አደረገ፡፡ የክለቡ የቡድን መሪ ቅጣት ሲፀና፣ በአንድ ተጫዋች ላይ ተጨማሪ ቅጣትን አስተላልፏል፡፡ ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ከተደረጉ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከመካላከያ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ሳይጠናቀቅ የተቋረጠው ጨዋታ ይጠቀሳል፡፡