Skip to main content
x

በልማዳዊ አሠራሮች የትም መድረስ አይቻልም!

በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ መስኮች በየዕለቱ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በአመርቂ ውጤት ማለፍ የሚቻለው ከልማዳዊ አሠራር በተላቀቁ ሳይንሳዊ ሥነ ዘዴዎች ነው፡፡ ማንኛውም ነገር የሚከናወነውና አፈጻጸሙም የሚለካው በሳይንሳዊ መንገድ በተዘጋጁ መሥፈርቶች ሲሆን ውጤቱ አጥጋቢ ይሆናል፡፡ ይህ ያለንበት ዘመን በሳይንስና በቴክኖሎጂ ከመራቀቁ የተነሳ፣ በማናቸውም የውድድር መስክ በመፎካከር ማሸነፍ የሚቻለው በቂ ዝግጅት ማድረግ ሲቻል ብቻ ነው፡፡

በባለሥልጣናት የውጭ ጉዞ ላይ ተጨማሪ ገደብ የሚጥል ሰርኩላር ተሠራጨ

ከሳምንታት በፊት በተሠራጨ ሰርኩላር መሠረት በመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ በዩኒቨርሲቲዎችና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለሥልጣናት፣ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የውጭ ጉዞ ላይ ገደብ የሚጥል ተጨማሪ ቁጥጥር ወጣ፡፡ በቀድሞ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ዓለማየሁ ተገኑ ተፈርሞ በወጣው ሰርኩላር መሠረት፣ ወደ ውጭ የሚደረጉ ጉዞዎች በጥብቅ ዲሲፕሊን መከናወን ይኖርባቸዋል፡፡

በኮማንድ ፖስቱ ታስረው የነበሩ የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ ምክትል አዛዥና የፍትሕ ቢሮ ቃል አቀባይ ተፈቱ

የካቲት 9 ቀን 2010 ዓ.ም. የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና ተግባራዊ መሆን የሚገባቸውን ድንጋጌዎች ተላልፈዋል ተብለው በኮማንድ ፖስቱ ታስረው የከረሙት፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ አድማ በታኝ ፖሊስ ምክትል አዛዥ፣ የፍትሕ ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን  ኃላፊና የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር ከእስር ተፈቱ፡፡

በዓድዋ ጦርነት የተሰው ጀግኖችን አፅም በክብር ለማሳረፍ ታሰበ

በዓድዋ ጦርነት የተሰው ጀግኖችን አፅም በጅምላ ከተቀበሩበት ሥፍራ አንስቶ በክብር ማኖር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው ሚያዝያ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡ የዚህ ሐሳብ መነሻም በአካባቢው በተደረገ ጥናት ምንድብድብ በሚባል ሥፍራ፣ በጅምላ ተቀብረው የተገኙ የዓድዋ ጀግኖች አፅሞች በቁፋሮ ወቅት እንደ ነገሩ ሆነው በመገኘታቸው ነው ተብሏል፡፡

 ዜጎች በሕገወጥ መንገድ ለምን እንደሚሰደዱ ጥናት ተጀመረ

ለቤት ሠራተኝነት ወይም ለተለያዩ የሥራ መደቦች ከኢትዮጵያ ክልሎች ወደ አዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች፣ እንዲሁም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮችና ሌሎችም አገሮች የሚሰደዱ ዜጎች በሕጋዊ መንገድ መሄድ ትተው ለምን ሕገወጥ መንገድ እንደሚመርጡ ለማወቅ ጥናት ተጀመረ፡፡

‹‹በታሪካችን በየትኛውም ጊዜ ዓይተነው የማናውቀው ተማሪ ሌላ ተማሪን የሚገድልበት ሁኔታ ተፈጥሯል››

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢሕአዴግ) ኢትዮጵያን መምራት ከጀመረ ከሃያ ስድስት ዓመታት በላይ ተቆጥሯል፡፡ ፓርቲው አገሪቱን በመምራት ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ባስቆጠረበት ጊዜ ውስጥ አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ እየተከሰቱ ባሉ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችና ግጭቶች፣ የአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ከመታወኩም በላይ የዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፣ ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለዋል፡፡

በአገሪቱ የተከሰተውን ቀውስ ለማስቆም የሚቀሩ ሥራዎች እንዳሉ ተጠቆመ

በአገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰና በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለውን ቀውስ ለማስቆም፣ በርካታ የሚቀሩ ሥራዎች እንዳሉ ተጠቆመ፡፡ የአገር መከላከያ ሚኒስትርና የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ጸሐፊ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ዓርብ ታኅሳስ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የፌዴራልና የክልል የፀጥታ ምክር ቤቶች የተካሄደው የጋራ ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን ያሉት፡፡ ከአንድ ወር በፊት በአገሪቱ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት በፌዴራልና በክልሎች የጋራ ምክር ቤት ዕቅድ ወጥቶና መግባባት ተፈጥሮ ወደ ሥራ በመግባት በርካታ ለውጦች ቢመዘገቡም፣ ሕገወጦችን በቁጥጥር ሥር ከማዋል አኳያ የሚቀሩ ሥራዎች አሉ ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች የፖለቲካ ትግል ማድረጊያ መሣሪያዎች መሆናቸውን የመንግሥት ሪፖርት አመለከተ

ዩኒቨርሲቲዎች ከመማር ማስተማርና ችግር ፈቺ የጥናትና የምርምር ሥራዎችን ከማከናወን ይልቅ፣ የፖለቲካ ትግል ማድረጊያ መሣሪያዎች እየሆኑ መምጣታቸውን በመንግሥት የተዘጋጀ ሪፖርት አመለከተ፡፡