Skip to main content
x

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የአበል ማሻሻያ ረቂቅ አዘጋጅ

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች አፈጻጸምን የተመለከተውን መመርያ በማሻሻል፣ የትራንስፖርትና ሌሎች አበሎችን ክፍያ የሚያሻሽል ተጨማሪ ተፈጻሚ ድንጋጌዎችን ያካተተ ረቂቅ መመርያ አዘጋጀ፡፡ ሚኒስቴሩ በአዲሱ ረቂቅ መመርያ የትራንስፖርት አበልና የመጓጓዧ ወጪን በተመለከተ እንደጠቀሰው፣ ከግብር ነፃ እንዲሆን በቀድሞ ድንጋጌው ላይ የተጠቀሰውን የቀን ውሎ አበል ጣሪያ ከ225 ወደ 500 ብር ከፍ ተደርጓል፡፡

የታክስና የጉምሩክ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ከ15 በላይ መመርያዎች ይፋ ሊሆኑ ነው

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከ15 በላይ አዳዲስ ረቂቆችና ማሻሻያ የተደረገባቸውን መመርያዎች ለመተግበር ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ ከጉምሩክና ከታክስ አስተዳደር ጋር ተግባራዊ ያደርጋቸዋል ተብሎ በሚጠበቁት በእነዚህ አዳዲስ መመርያዎችና ማሻሻያዎች ላይ፣ ከንግድ ኅብረተሰቡ ጋር እንደሚመክርባቸው ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ የተፈራረሙበት የሠራተኛ ቅጥር ስምምነት አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

የኢትዮጵያና የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥታት ከኢትዮጵያ በሚሄዱ የቤት ሠራተኞች ቅጥርና የሠራተኛና አሠሪ መብቶችን በተመለከተ ያደረጉት ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡ ስምምነቱ የሠራተኛና የአሠሪውን መብቶች፣ የሁለቱን አገሮች ሉዓላዊነት በጠበቀ መንገድ እንዲፈጸም የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የምሕረት አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

የምሕረት አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡ ረቂቅ አዋጁ ምሕረት የሚሰጥባቸውን ጉዳዮች እንዴት እንደሚለዩ፣ የምሕረት ውሳኔ አሰጣጥና የምሕረት ቦርድ የሚቋቋምበትን ሁኔታ ይዘረዝራል፡፡

ኢሕአዴግና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በብሔራዊ መግባባት ላይ ቅድመ ድርድር አካሄዱ

ኢሕአዴግና 15 አገር አቀፍ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉን አሁንም በቀጠሮ አሳድረው፣ የመጨረሻ በነበረው ብሔራዊ መግባባት አጀንዳ ላይ ቅድመ ድርድር አካሄዱ፡፡ የሁለቱ ወገኖች ድርድር በጥር ወር ነበር የተቋረጠው፡፡ ረቡዕ ግንቦት 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ለድርድር ተቀምጠው የነበሩት ኢሕአዴግና ፓርቲዎቹ፣ ብሔራዊ መግባባት በሚለው አጀንዳ ላይ ለመደራደር የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች ምን መሆን አለባቸው? በሚለው ላይ ዘለግ ያለ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ኢሕአዴግና አገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያቋረጡትን ድርድር ጀመሩ

ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ የተቋረጠው የገዥው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) እና 15 አገር አቀፍ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአገሪቱ ምርጫ፣ ተያያዥ ሕጎችና አዋጆች ላይ የሚደረገው ድርድር እንደገና ተጀመረ፡፡ ጥር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ኢሕአዴግና 15 አገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በድርድሩ አራተኛ አጀንዳ በሆነው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 ላይ የሚያደርጉትን ድርድር መቋጨት ባለመቻላቸው፣ ድርድሩ በይደር እንዲቆይ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

ከአጉል ልማድ ጋር መኖር ከእውነታ ጋር ያጋጫል!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር የሚኮራባቸውና የማንነቱ መገለጫ የሆኑ የተለያዩ ባህሎች፣ ወጎችና ልማዶች አሉት፡፡ የማኅበረሰብ ህልውናን የሚያጎለብቱና አብሮ መኖርን የሚያጠናክሩ እነዚህ እሴቶች፣ ዘመናትን እየተሸጋገሩ በትውልዶች ቅብብሎሽ እዚህ ዘመን ላይ ደርሰዋል፡፡ በሌላ በኩል ጎጂ ተብለው የሚታወቁ ልማዶች ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርሱ ኖረዋል፡፡

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ

መንግሥት ከፍተኛ የገንዘብና የእስራት ቅጣት የሚጥል ሕግ ያወጣ ቢሆንም፣ በተደራጀና ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ሕጉን ተግባራዊ ሊያደርግ ባለመቻሉ በሕገወጥ ደላሎች የሰዎች ዝውውር ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ፡፡ ከአራት ዓመታት በፊት በተለይ በሳዑዲ ዓረቢያ በቤት ሠራተኝነትና በሌሎች ሥራዎች ተሠማርተው በነበሩ ኢትጵያውያን ላይ በደረሰው ግድያ፣ አካል ማጉደልና ከፍተኛ እንግልት ምክንያት መንግሥት ዜጎች ወደ መካከለኛው ምሥራቃዊ አገሮች እንዳይጓዙ ዕግድ ጥሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ለአዲስ አበባ ካቢኔ ተጨማሪ ሥልጣን እንዲሰጥ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ውዝግብ አስነሳ

ሐሙስ ሚያዚያ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማውን አስፈጻሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት እንደገና ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ የምክር ቤቱን ሥልጣን ለካቢኔው የሚሰጥ ነው በሚል ምክንያት ከፍተኛ ውዝግብ አስነሳ፡፡