Skip to main content
x

የስደተኞች አያያዝ አዋጅ ሊሻሻል ነው

ለአሥራ አራት ዓመታት በሥራ ላይ ያለው የስደተኞች አያያዝ አዋጅ ሊሻሻል መሆኑ ታወቀ፡፡ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አስተዳደር ጉዳይ ጽሕፈት ቤት የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሱሌማን ዓሊ ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ከዚህ በፊት ዓለም አቀፉ የአፍሪካ ኅብረት የስደተኞች አያያዝ ሕጎችን መሠረት በማድረግ ወጥቶ የነበረው አዋጅ በቅርቡ ይሻሻላል፡፡