Skip to main content
x

ለአርሶ አደሮች የሚቀርበው ማዳበሪያ ላይ የዋጋ ጭማሪ ተደረገ

በዓለም አቀፍ ገበያ ከዩሪያ በስተቀር በሌሎች የማዳበሪያ ዓይነቶች ላይ  የዋጋ ጭማሪ ባይደረግም፣ ብር ከዶላር ጋር ያለው ምጣኔ በ15 በመቶ እንዲቀንሰ በመደረጉ ምክንያት ለአርሶ አደሮች በሚቀርበው ማዳበሪያ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ፡፡

አርሶ አደሮች ምርት ሰብስበው እንደ ጨረሱ ወደ መስኖ እንዲገቡ ተጠየቀ

በተያዘው የምርት ዘመን አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት ሰብስቦ እንደ ጨረሰ፣ የተለያዩ የውኃ አማራጮችን ተጠቅሞ ወደ መስኖ ልማት እንዲገባ ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ መንግሥቴ ሐሙስ ታኅሳስ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ ከዚህ በፊት አርሶ አደሩ በዓመት አንድ ጊዜ አምርቶ ረዥም የበጋ ወራትን ያለሥራ ይቀመጥ ነበር፡፡ አርሶ አደሩ ይህንን ልምድ እንዲለውጥና ወደ መስኖ እንዲገባ ጥሪ ተላልፏል፡፡

ጨረታ ማውጣት ሳያስፈልግ ማዳበሪያ በድርድር መግዛት የሚያስችል መመርያ ፀደቀ

ለ15 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ግዢ 600 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተይዟል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ለምርት ዘመኑ የሚያስፈልገውን 15 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ፣ ጨረታ ማውጣት ሳያስፈልግ በቀጥታ ከአምራቾች ጋር በመደራደር ግዥ መፈጸም የሚያስችል መመርያ አፀደቀ፡፡

ጤፍን ወደ ሜካናይዝድ እርሻ የሚያሸጋግሩ ማሽኖች አገር ውስጥ ገቡ

ማሽኖቹን አገር ውስጥ ለማምረት ታስቧል በኢትዮጵያ ከ50 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በቋሚነት የሚመገበውን ጤፍ ከኋላቀር አስተራረስ አላቀው ወደ ዘመናዊ ግብርና ያሸጋግራሉ የተባሉ ማሽኖች አገር ውስጥ ገቡ፡፡ እነዚህን ማሽኖች አገር ውስጥ እንዲመረቱ ለማድረግ የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

የነፍስ ወከፍ የጤፍ መዝሪያ ማሽኖች ግዥ የሙስና ጥያቄ አስነሳ

ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች አንዳንዶቹ ከአገር ወጥተዋል ለሦስት ክልሎች የተከፋፈሉ 30 ሺሕ ያህል የነፍስ ወከፍ የጤፍ መዝሪያ ማሽኖችን በመግዛት ያከፋፈለው የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር፣ ከማሽኖቹ ግዥና ሥርጭት ጋር የተያያዘ የሙስና ጥያቄ ተነሳበት፡፡