Skip to main content
x

የአልጀርስ ስምምነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለመፅደቁ በሕግ ፊት ዋጋ ቢስ ነው ተባለ

በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተካሄደውን ዕልቂት ያስከተለ ጦርነት በማስቆም ቀጣናውን ወደ ሰላም ለመመለስ የተደረገው የአልጀርስ ስምምነትና የድንበር ኮሚሽኑ ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች፣ በሕግ ፊት ቦታ እንደሌላቸው የኢሮብ ብሔረሰብ ተወላጆች አስታወቁ፡፡

ሕወሓት የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለኢኮኖሚው ችግር የሰጣቸው መፍትሔዎች ጊዜያዊ ናቸው ሲል ወቀሰ

የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ረቡዕ ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ለመሠረታዊ የኢኮኖሚ ችግር ጊዜያዊ መፍትሔ ላይ ከማተኮር ይልቅ ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጥ ይገባ ነበር ሲል ወቀሰ፡፡

ፈረሱን ወንዝ ድረስ መውሰድና ውኃውን ማጠጣት ለየቅል ናቸው!

እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 12 ቀን 2000 ዓ.ም. የተፈረመው የአልጀርስ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን በቅርቡ በኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ውሳኔ ከተሰማ ወዲህ በርካታ አስተያየቶች እየተደመጡ ነው፡፡

መኢአድ የአልጀርሱን ስምምነት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል የአገር ክህደት ነው አለ

ባለፈው ሳምንት መጀመርያ ላይ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የአልጀርስን ስምምነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደሚቀበል መግለጹ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አስታወቀ፡፡

ኢሕአዴግ ባድመ ለኤርትራ እንድትሰጥ የወሰነውን የአልጀርስ ስምምነት ሙሉ በሙሉ መቀበሉን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ማክሰኞ ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ፣ ባድመ ለኤርትራ እንድትሰጥ የወሰነው የአልጀርሱን ስምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ እንደወሰነ አስታወቀ፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አመሻሸ ላይ ባወጣው መግለጫ ከ20 ዓመታት ውዝግብና እሰጥ አገባ በኋላ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የድንበር ማካለል ኮሚሽን የወሰነውንና በሁለቱ መንግሥታት በአልጀርስ የተፈረመውን ስምምነት እንደሚቀበል ይፋ ሲያደርግ ምክንያቱ ምን እንደሆነ አሥፍሯል፡፡

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የአልጄርሱ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን ወሰነ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የአልጀርሱ ስምምነትና የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲደረግ ወሰነ፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ፣ ‹‹በጥቅም ብቻ ሳይሆን በደም ለተሳሰሩት የሁለቱ አገር ሕዝቦች የጋራ ጥቅም ሲባል የኢትዮጵያ መንግሥት የአልጀርሱን ስምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ የወሰነና ለተግባራዊነቱ ያለማመንታት በቁርጠኝነት የሚሠራ መሆኑን ለመግለጽ ይፈልጋል፤›› ብሏል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ረዳት ኃላፊ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ለመወያየት አዲስ አበባ ይገባሉ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ተቀዳሚ ምክትል ኃላፊ አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ለመምከር፣ ሐሙስ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡

የዕርቀ ሰላም ጅማሬ

ቅዳሜ መጋቢት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ሶማሌ ክልል ያቀኑት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አጋጥሞ የነበረው ግጭት ‹‹ያልተገባ፣ ከኢትዮጵያዊነት ባህል ያፈነገጠና የሁላችንንም አንገት ያስደፋ የሽንፈት ታሪካችን ነው፤›› በማለት ከኅብረተሰቡ ለተወከሉ የኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ንግግር አድርገው ነበር፡፡ ከሁለቱም ክልሎች በርካታ ዜጎች ለሕልፈት የተዳረጉበትን፣ በርካቶች ለአካል ጉዳት የተጋለጡበትንና ከ700 ሺሕ በላይ የተፈናቀሉበትን ግጭት በዕርቀ ሰላም እንዲቋጭም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያና የኤርትራ የወደፊት ተስፋና የወቅቱ ፈተና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሰየሙ ባደረጉት ንግግር ከጠቀሷቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታትን ግንኙነት የተመለከተ ነበር፡፡

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የምትደራደረው ባድመ ከተመለሰላት ብቻ እንደሆነ አስታወቀች

ኤርትራ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ያላትን የፖለቲካ ልዩነት በማጥበብ ልትደራደር የምትችለው፣ ባድመ ከተመለሰላት ብቻ እንደሆነ አስታወቀች፡፡ የኤርትራ መንግሥት ይህን ያለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተሰየሙ በኋላ፣ ባደረጉት ንግግር ለኤርትራ መንግሥት ላቀረቡት ጥሪ በሰጠው ምላሽ ነው፡፡