Skip to main content
x

የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስለምን ተነጋግሮ ምን ነገረን?

‹‹እውነት አሁን ደርግ አለ?›› የተባለውና የተጠየቀው፣ ጥያቄያዊ አባባሉም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ መተረቻ፣ መሳቂያም መተረቻም የሆነው ዛሬ፣ ‹‹ኢሕአዴግ አለ?›› ተብሎ ከሚነሳው (መነሳት ከሚችለው) ጥያቄ በጭራሽ በተለየ ድባብ፣ ዓውድ፣ ስሜትና አግባብ ጭምር ነው፡፡

ድሮ’ኮ ወርቁ ቢጠፋ ቢያንስ ‘ሚዛኑ’ ነበር

አንድ ዓመት የሞላውና በተለያየ ስሜት በመከበርና በመዘከር ላይ ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ መንግሥት የሚመራው ለውጥ ብዙ ዓይነት የማይናቁ ተጠናዋቾች ቢኖሩትም፣ ‹ሀ› ብሎ ሥራውን የጀመረው የጠላትነት ፖለቲካን እናፍርስ፣ ለየትኛውም ቡድንና ወገን የማያገለግል፣ ከቡድናዊ ቁጥጥር፣ ወገናዊነትና ታማኝነት የተላቀቀ፣ ለፓርቲም ሆነ ለብሔርተኛ ማንኛውም አድልኦ የማይበገር፣ ዓይኑ የተጋረደ ሆኖ የሁሉም የጋራ አለኝታ ተደርጎ ለመታየት የበቃ አውታረ መንግሥት እንገንባ ብሎ ነው፡፡ ይህ በራሱ ትልቅ ግኝት፣ ትልቅ ዕውቀት፣ ትልቅ ጅምር ነው፡፡

አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ!

ዛሬ አገራችን ከጥብቅ አሃዳዊ አስተዳደር ወጥታ ወደ ዴሞክራሲና ፌዴራላዊ አስተዳደር ለመግባት ጉዞ ጀምረናል የሚል ተስፋ አለ፡፡ ነገር ግን ይኼ ተስፋ እንዲሁ በቀላሉ በጥቂት ወራትና ሳምንታት ይፈጸማል የሚል የዋህነት ሊኖረን አይገባም፡፡ በዚህ ጉዞ ላይ በርካታ መሰናክሎች አሉ፡፡ ከሁሉ በፊት ዕድገታችን ቀርቶ ሰላማችን እንኳን ዕረፍት የሚነሳቸው በርካታ የቅርብና የሩቅ ኃይሎች አሉ፡፡

ትልቁን ጉዞ የሚያስቱ ዕይታዎችና ንጭንጮች

በኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ታሪክ ውስጥ የእያንዳንዱን አካባቢ መሬት ‹‹እውነተኛ›› ባለቤት መርምሮ ለመለየት እሞክራለሁ ማለት የማይወጡት ነገር ውስጥ ገብቶ መዳከር ይሆናል፡፡ በቅድሚያ ‹‹እውነተኛ›› ባለቤትነት በምን ይለካል? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ከባድ ነው፡፡ ቀድሞ በሥፍራው ላይ መኖርን የባለቤትነት መመዘኛ ብናደርግ ለቀዳሚም ቀዳሚ ይኖረዋል፡፡

በባሮ ቱምሳ መንገድ ከክፍልፋይነት አዘቅት ውስጥ መውጣት

መቋሰልን ሊያፈልቁ የሚችሉ ትልልቅ የብሔርተኛ ቀዳዳዎችን እስካልዘጋን ድረስ ስሜታችንን ብናስታርቅም፣ ተመልሰን የመናቆር ወጥመዶች ውስጥ መግባታችን አይቀርም፡፡ እንዲያውም እነሆ ዛሬ የትርምስና የሰዎችን በገፍ የመፈናቀል ጣጣዎችን ማስቆም ባለመቻላችን፣ ዕርዳታ ፈላጊነትና ረሃብተኝነት ‹‹በአዲስ መልክ›› ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ጀምሮ የጌዴኦን ፈተና ይዞልን መጥቷል፡፡

ከተቀረቀርንበት ጉድጓድ እንዴት እንውጣ?

ዛሬም መማረር ታመመ እንጂ ገና ነፍሱ አልወጣም ለምን? የሕወሓት ኢሕአዴግ ብልጣ ብልጥ አገዛዝና የክልል ገዥዎች ‹‹ተለጣፊነት››፣ ወዲያውኑ ፈጦ የወጣና ማንም ተራ ሰው የማይደናገርበት እውነታ ሆኖ ሳለ፣ አንድ ላይ ተያይዞ መነሳት እንደምን ተሰለበን? የአገዛዙ ሸረኛና ፖሊሳዊ ጥርነፋ፣ ለውጥ ፈላጊዎች ለመተባበር ካደረጉት ጥረት በልጦ፣ ብሔረተኛ አስተሳሰብና አገዛዝ ደጋፊዎቹንም ተቃዋሚዎቹንም በጥላቻ ስሜት እየመረዘ አዕምሮና ማኅበራዊ ግንኙነታቸውን ለመከታተፍ ከሩብ ምዕት ዓመት በላይ ዕድሜ ማግኘቱ ዋናው ምክንያት ነው፡፡

ተረጋግቶ የመኖር ብርቅነት እንደምን ያብቃ?

የዱር እንስሳት የአዳኝነትና የታዳኝነት ዓለም የሚነግረን፣ ኅብረት ውጤት አምጪና ዕድሜ ቀጣይ መሆኑን ነው፡፡ ብቻውን የሮጠ አድኖ ነፍሱን ለማቆየት ይከብደዋል ወይም ታድኖ ለመበላት ይጋለጣል፡፡ የዛሬው የእኛ ዓለምም ብንወድም ብንጠላም ዕጣ ፈንታችንን አንድ ላይ አስተሳስሯል፡፡

ዴሞክራሲያችን ለየትኛውም ቡድን ሳይወግን የሚያገለግል አውታረ መንግሥት ይሻል

ላለፉት 11 ወራት ብቻ ሳይሆን ከዚያም በፊት ከጎደለን፣ ኢትዮጵያን ካጎደሏት ነገሮች መካከል አንዱና ዋነኛው ኢወገናዊ በሆኑ ተቋማት ላይ ዴሞክራሲን ለማቋቋም አለመቻላችን መሆኑን፣ በተለይም በዚህ ጋዜጣ በዚህ ዓምድ ደግመን፣ ደጋግመን አውርተናል፣ ተናግረናል፣ ጽፈናል፡፡ ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ በተለይም ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም.

ዕድል የማበላሸት ልማዳቸውን አበላሽተው አያውቁም እንዳንባል

ከጥላቻ ፖለቲካ ውስጥ እንውጣ፣ በዕርቅ እንተቃቀፍ፣ ወገንተኛ ባልሆኑ አውታራት ላይ ዴሞክራሲን እንገንባ፣ ማንነትን፣ በተለይም ብሔራዊ ማንነትን ከኢትጵያዊነት ጋር እናግባባ፣ እንደ አገር ህልውናን በሚወስኑ የቀጣናችንና የአኅጉራችን አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ እናተኩር፣ በአጠቃላይ በውስጧ ሰላም የሆነች፣ ከሌሎችም ጋር በሰላም የምትኖር እውነተኛ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብክ ኢትዮጵያን እንገንባ ብሎ የተነሳውና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የሚመሩት ለውጥ እነሆ መጋቢት 24 ሲመጣ አንድ ዓመት ይሞላዋል፡፡