የሳምንቱ ገጠመኝ
እጅግ በጣም ባለፀጋ የነበረ አሜሪካዊ ሞቱ መቃረቡን ሲረዳ ካከማቸው ገንዘብ ላይ ለሕፃናት ማሳደጊያ፣ ለአረጋውያን መጦርያ፣ ለወጣቶች ንባብ ቤትና ለሴቶች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በሚገባ ይሰጥና 90 ሚሊዮን ዶላር ይተርፈዋል፡፡ ላለፉት በርካታ ዓመታት ከለፋበት ገንዘቡ ላይ ለራሱ የሚሆን ማስቀረት ፈለገ፡፡ ይኼንንም ተግባራዊ ለማድረግ ሐኪሙን፣ የንስሐ አባቱንና ጠበቃውን የምሳ ግብዣ አዘጋጅቶ ጠራቸው፡፡