Skip to main content
x

መፍትሔ አልባው የአዲስ አበባ ቤቶችና የይዞታ ጉዳይ

ከመሬት ይዞታና ከመኖሪያ ቤት ጉዳይ በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም በየካ ክፍል ከተማ ያለውን ችግር በተመለከተ፣ ሰሞኑን በአዲስ ቴሌቪዥን የቀረበው ፕሮግራም ነገሩን ለማያውቀው አስገራሚ ሊሆንበት ይችላል፡፡ ችግሩ ለገጠመውና ለደረሰበት ግን የተለመደ ነው፡፡ በተላፈው ፕሮግራም እንደታየው ከሆነ፣ በክፍለ ከተማው ከ1984 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም. ያላለቀ የመሬትና የቤት ጉዳይ አለ፡፡ 26 ዓመት ሙሉ አንድ ጉዳይ መፍትሔና ፍጻሜ አለማግኘቱ ለግለሰቡ የዕድሜ ልክ ስቃይ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ መንግሥት በየጊዜው መሬትን በተመለከተ ጥሩ መመርያ ያወጣል፡፡ ፈጻሚዎቹ ግን መመርያዎችን በትክክል መረዳት ስላልቻሉ እንደሆነ አይታወቅም ሕዝቡን ማሰቃየታቸውን ቀጥለዋል፡፡

‹‹ዲላ ዩኒቨርሲቲ በቁልቁለት ጐዳና››

መስከረም 21 ቀን 2010 ዓ.ም. በታተመው የአማርኛው ሪፓርተር ጋዜጣ ‹‹ዲላ ዩኒቨርሲቲ አልሞተም!›› በሚል ርዕስ (የጋዜጣው አዘጋጅ የሰጠው) የዲላ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን ትምህርት የልቀት ማዕከል ሆኖ መመረጥ እንዴት ተሳነው በሚል ቁጭት አዘል ጥያቄ ዙርያ የምታጠነጥን መጣጥፍ ጽፌ፣ ታትማ ለንባብ መብቃቷም ይታወሳል፡፡

ለተሰጠን ውሳኔ የተግባር ዕርምጃ እንጠብቃለን!

ሁሉም እንደሚያውቀው፣ ለአንድ አገር ሕዝብ ከሚያምነው ፈጣሪ በታች ያሉት ያገሩ መሪና ሥራ አስፈጻሚዎቹ ናቸው። የአመራሩ ብቃት የሚፈተሸውም ባለው የማስፈጸም ችሎታ እንደሆነ ለማንም ግልጽ ይመስለኛል። በተገቢው ጊዜ ውሳኔ ማስተላለፍ ከብቃቶቹ አንዱ ሲሆን፣ ከዚህ በበለጠ የተወሰነውን ውሳኔ ማስፈጸምና መፈጸሙን መከታተል ዋነኛው የብቃት ማሳያ ናቸው።

ለማን አቤት እንበል

በኮዬ ፈጬ ኮንደሚኒየም ዕጣ ወጥቶልን ቁልፍ ከተረከብን አንድ ዓመት ከአራት ወራት ሆነን፡፡ ውኃና መብራት ሳይገባልን፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሳይሠራልንና በየደጃፋችን ያለው አፈር ሳይነሳ ተቆልሎ ተቀምጧል፡፡ አንድ ጀሪካን ውኃ አሥር ብር እየዛንና በሻማ እየኖርን ነው፡፡ ከዛሬ ነገ ይስተካከላል በሚል ተስፋ ዓመት አለፈን፡፡ ልጆቻችን እየተሰቃዩ ሲሆን፣ የኑሮ ሁኔታን መቋቋም ያልቻሉ ለሀብታም እየሸጡ ነው፡፡

ቃል ከተግባር ይዛመድ

 በ2005 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተጠቃሚ ለማድረግ በመንግሥት ምዝገባ መካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ ለተመዝጋቢዎቹ የተገለጸው 40 በመቶ ገንዘብ ቁጠባ ሲያደርጉ፣ በመንግሥት በኩል ከባንክ 60 በመቶ ብድር ተመቻችቶላቸው ከአምስት ዓመት ባነሰ ጊዜው ውስጥ የቤቶቹ ግንባታ አልቆ ለነዋሪዎች ይተላለፋ ተብሎ በመነገሩ፤ የተሻለ ገቢ ያላቸው፣ ዳያስፖራዎች እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች ጭምር የቤት ችግራቸውን ለመወጣት ብዙ ተስፋ ጥለውበት ነበር፡፡ ለዓመታት በብዙ ተስፋ ሲጠበቅ የነበረው የቤት ፕሮግራም፣ ከአምስት ዓመት በኋላ በ2010 ዓ.ም. ለ1,200 ቤቶች ለዕድለኞች ዕጣ ወጣላቸው ተባለ፡፡ 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዝክረ ሌፍተናት ጀኔራል ጃጋማ ኬሎ ጎን እንዲቆሙ እንጠይቃለን

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ዛሬ በነፃነት የምንኖርባት አገራችን ኢትዮጵያ፣ በበርካታ አባቶቻችንና እናቶቻችን ጀግንነትና ከብረት የጠነከረ ወኔ፣ ቆራጥነትና ብርቱ መስዋዕትነት በክብርና በኩራት የተረከብናት ነች፡፡

የአፄ ቴዎድሮስ ጦርነት አልባ ጦርነት

የኢትዮጵያን አንድነት ጠብቆ ለማቆየት ጉጉት የነበራቸው አፄ ቴዎድሮስ ወይም በቅጽል ስማቸው ‹‹መይሳው ካሳ››፣ ፍላጎታቸውንና እምነታቸውን እውን ለማድረግ አልፎ አልፎ የእኩይ ባህሪይ ተላብሰው የጨካኝነት ተግባር ይፈጽሙ እንደነበር እርግጥ ነው፡፡

ገንዘብ የሚገኘው በሥራ ሳይሆን በኪራይ እየሆነ ነው

ይህ አባባል በአገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች የሚኖሩ የአያሌ ተከራዮች የብሶት ድምፅ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ በተጋነነ መልክ በመጨመር ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ከምግብና ልብስ የበለጠ ፍላጎት በማሳደሩ ተከራይ ዜጎች ኑሮ ለከፍተኛ ምሬት እየዳረገ ይገኛል፡፡ ችግሩ ከዜጎች የመቋቋም አቅም በላይ በመሆኑ ተከራይ ወገኖች በመተሳሰብና በመረዳዳት ወርቃማ እሴት የተመሠረተው በጋራ ጥቅም የማመን አመለካከት በመሸርሸሩ በአገራቸውና በወገናቸው መተማመን አልቻሉም፡፡ ተስፋ መቁረጥና ስደትን መመኘት ይታይባቸዋል፡፡፡