Skip to main content
x

በመከላከያ ሠራዊት ሁለት አዳዲስ ሹመቶች ተሰጡ

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ በነበሩት ጄኔራል አደም መሐመድ ቦታ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ መሾማቸውን የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሞቱማ መቃሳ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ጄኔራል አደም የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው የሚታወስ ነው፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም፣ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የመከላከያው የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን አስታውቀዋል፡፡

የወላይታ ዞን ባለሥልጣናት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው ከኃላፊነት ለቀቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ግጭት በተከሰተባቸው የደቡብ ክልል የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የወልቂጤና የቀቤና የዞንና የወረዳ አስተዳዳዎች ከኃላፊነታቸው እንዲለቁና ለደረሱ ጥፋቶች ኃላፊነት እንዲወስዱ ማሳሰቢያ ከሰጡ በኋላ፣ የወላይታ ዞን አምስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከኃላፊነታቸው ተነሱ፡፡

‹‹ይህ ሙሉ በሙሉ አዎንታዊና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚደረጉ ለውጦችን ለመደገፍ የሚረዳ ነው፤›› ብለው እንደሚያምኑ የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ጌታሁን ጋረደው (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የአሠሪዎች ኮንፌዴሬሽን ሼሕ አል አሙዲ እንዲፈቱ ሊጠይቅ ነው

የኢትዮጵያ አሠሪዎች ኮንፌዴሬሽን ሼሕ መሐመድ አሊ አል አሙዲ ከእስር እንዲፈቱ የሳዑዲን መንግሥት እንደሚጠይቅ አስታወቀ፡፡

ከአገሪቱ ግንባር ቀደም አሠሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀመንበር ሼክ መሐመድ አል አሙዲ እንዲፈቱ ኮንፌዴሬሽኑ ብርቱ ፍላጎት ያለው በመሆኑ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከጀመሩት ጥረት ጎን ለጎን ኮንፌዴሬሽኑም የራሱን ጥረት ለማድረግ በመነሳሳት ላይ መሆኑን ኮንፌዴሬሽኑ ሐሙስ ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁከት የተነሳባቸው አካባቢዎች የሥራ ኃላፊዎች እንዲለቁ አሳሰቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በደቡብ ክልል ግጭት የተከሰተባቸው አካባቢዎች የሥራ ኃላፊዎች ከኃላፊነታቸው እንዲለቁ አሳሰቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት፣ በቅርቡ ግጭት ተከስቶባቸው በነበሩ  በሐዋሳ፣ በወላይታ ሶዶና በወልቂጤ ከተሞች ከኅብረተሰቡ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የጉራጌና የቀቤና የዞንና የወረዳ አስተዳደር ኃላፊዎች ሥራቸውን በአስቸኳይ እንዲለቁ ማሳሰባቸውን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

በሞጆ ከተማ በ100 ሚሊዮን ዶላር የቆዳ ኢንዱስትሪ ዞን ሊገነባ ነው

ከአዲስ አበባ ከተማ 76 ኪሎ ሜትር ርቀት በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ከተማ አቅራቢያ በ100 ሚሊዮን ዶላር የቆዳ ኢንዱስትሪ ዞን ሊገነባ ነው፡፡ ለአካባቢያዊ ብክለት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸውን የቆዳ ፋብሪካዎች አንድ ቦታ ለማሰባሰብ የታቀደው ከዓመታት በፊት ቢሆንም ዕቅዱ ተግባራዊ ሳይደረግ ቆይቷል፡፡ የኢትዮጵያ ቆዳና ቆዳ ውጤቶች ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ ለገሠ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የፕሮጀክቱ ጥናት ከሦስት ዓመት በፊት ቢጠናቀቅም ገንዘብ  ባለመገኘቱ ዘግይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በአነስተኛ ወለድ ብድር በመፍቀዱ ወደ ሥራ እየተገባ ነው ብለዋል፡፡

ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ሠራተኞችን ለመላክ የሚያስችል የመጨረሻ ውይይት በፓርላማ ተደረገ

ሠራተኞችን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ለመላክ በኢትዮጵያና በሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥታት መካከል የሁለትዮሽ ስምምነት አስፈላጊ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞችን መላክ የሚቻልበትን ሁኔታዎችን በሚመለከት የመጨረሻ ውይይት ማክሰኞ  ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በፓርላማ ተደረገ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አነጋጋሪ ማብራሪያ በፓርላማ

ሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በፓርላማ ለምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ለመስጠት የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ጊዜ ወስደው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዥ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋይናንስ ጉዳዮች አማካሪ ሆኑ

ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥነት የተነሱት አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋይናንስ ጉዳዮች ኃላፊ ሆኑ፡፡ ላለፉት 13 ዓመታት በገዥነት በቆዩት አቶ ተክለ ወልድ ምትክ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ሲሾሙ፣ አቶ በቃሉ ዘለቀ ደግሞ ምክትል ገዥ ሆነዋል፡፡ አቶ ተክለ ወልድ የተመደቡበት የፋይናንስ አማካሪነት ኃላፊነት ለመጀመርያ ጊዜ  ራሱን ችሎ መቋቋሙ ታውቋል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል ከኃላፊነታቸው ተነስተው በሌላ ኃላፊ ተተኩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አዲስ ካቢኔ ሲያዋቅሩ፣ የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አድርገው ሾመዋቸው የነበሩት ኃላፊ ተነስተው ሌላ ኃላፊ መሾሙ ተጠቆመ፡፡ በቅርቡ ተሹመው የነበሩትና ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በሌላ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል የተተኩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ናቸው፡፡ አቶ ያሬድን በመተካት የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው የተሾሙት ደግሞ አቶ ዘይኑ ጀማል መሆናቸውን የሪፖርተር ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

ሁከት ተከስቶባቸው የነበሩ አካባቢዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የክልልነት ጥያቄ አነሱ

ከሳምንት በፊት በተቀሰቀሰ ሁከት የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ተከስቶባቸው የነበሩት የደቡብ ክልል ነዋሪዎች፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በነበራቸው ውይይት የክልልነት ጥያቄ አጉልተው አነሱ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በፓርላማ ሪፖርታቸውን ካቀረቡና የአባላትን ጥያቄ ከመለሱ በኋላ በቀጥታ ወደ ሐዋሳ ከተማ በማቅናት፣ በነጋታው ማክሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ከሲዳማ ዞን ከፍተኛ አመራሮችና ከነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡