Skip to main content
x

የዕረቀ ሰላም ኮሚሽኖቹ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ጥር 28 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ለአስተዳደር፣ ወሰንና ማንነት ጉዳዮች በዕጩነት የቀረቡትን 41 አባላት አፅድቋል፡፡

የታክስ ንቅናቄ መድረክ በአዲስ አበባ

በቅርቡ በገቢዎች ሚኒስቴር ‹‹ግዴታዬን  እወጣለሁ፣ መብቴንም እጠይቃለሁ›› በሚል መርሐ ግብር የተጀመረውን አገር አቀፍ ንቅናቄ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለሥልጣን መተግበር ጀምሯል፡፡

የኪዩር ሕፃናት ሆስፒታል 10ኛ ዓመት

ኪዩር የሕፃናት ሆስፒታል አሥረኛ ዓመቱን ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም. ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት አክብሯል፡፡ ሐምሌ 19 መናፈሻ አጠገብ የሚገኘው ኪዩር ሆስፒታል ከተመሠረተ ወዲህ 17 ሺሕ ያህል በሕክምና ሊስተካከል የሚችል የላንቃ መሰንጠቅ፣ የአጥንት መወላገድ የአካል ጉዳት ያለባቸውን ሕፃናት አክሞ በጉድለታቸው እንዳይሸማቀቁ ማስቻሉ ተገልጿል፡፡ ከ100 ሺሕ በላይ ደግሞ ያለቀዶ ሕክምና ሕክምናን ሰጥቷል፡፡

የጥምቀት ክብረ በዓል እዚህና እዚያ

የጥምቀት ክብረ በዓልን የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኮፕቲክ/ግብፅ እንዲሁም የመካከለኛ ምሥራቅ ኦርቶዶክሳውያን ጥር 11፣ 2011 ዓ.ም. በጁሊያን ካላንደር  ጃንዋሪ 6 (በግሪጎሪያን ካላንደር ጃንዋሪ 19፣ 2019) እንደየትውፊታቸው አክብረዋል፡፡

ገናን በሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት

የእግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት (ገና) በዓል ታኅሣሥ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ሲከበር ብዙዎች ችግረኞችን በመርዳት ማሳለፋቸው በየሚዲያው ተዘግቧል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ታዋቂ ሰዎችና ግለሰቦች የተቸገሩትን በበዓል ለመጎብኘት በየሥፍራው ጎራ ያሉበት ዕለትም ነበር፡፡

የገናው ባዛር

የዘንድሮውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በመዲናዪቱ ከተዘጋጁት ባዛሮች አንዱ በሚሌኒየም አዳራሽ የተዘጋጀው ይገኝበታል፡፡ በዚሁ ባዛር ለሸመታ ከቀረቡት ቁሳቁሶች ባሻገር የበዓሉ ምልክት የሆኑ የገና ዛፎች፣ ማሸብረቂዎች፣ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም የተወለደበት በረት አምሳያዎችም ለዕይታ በቅተዋል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ስንብት

የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሆነው ለ12 ዓመታት ያገለገሉት የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ሥርዓተ ቀብር ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በአገራዊ ክብር ተፈጽሟል፡፡

‹‹በብዝኃነት የደመቀ ኢትዮጵያዊ አንድነት››

13ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀንን አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ ኅዳር 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በተካሄደው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት የቡና ጠጡ ባህላዊ መስተንግዶ የተከናወነ ሲሆን በዚህም ከአሥር ሺሕ ሰው በላይ ታድሞበታል ተብሎ ተገምቷል፡፡