Skip to main content
x

የግብፅ ነገር ‹‹በቅሎ ማሰሪያዋን በጠሰች ቢሉ አሳጠረች›› እንዳይሆን 

ለዛሬ የጽሑፌ መግቢያ ያደረግኩት በማኅበራዊ ድረ ገጽ (ፌስቡክ) ላይ ታማኝ  የምለው የአገራችን አንድ የውኃ ተመራማሪ በቅርቡ ያሠራጨው ቅንጫቢ የአኃዝ  መረጃን ነው፡፡ መረጃው የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ የቅርብ ጊዜውን ወደኋላ የሚመልስ ንግግር ተከትሎ፣ ከፍተኛ የሚባል ጫጫታ ያስነሱትን የካይሮ  ሚዲያዎች በመታዘብ፣ እኛ በተፈጥሮዊ ሀብታችን ሳንጠቀም እንዴት ወደኋላ እንደቀረን የሚያሳይ ንፅፅር ነው፡፡

የኮንግረንስ አባላቱ ጨዋታ አራምባና ቆቦ

ማኅበራዊ ሚዲያ አዲሱ የዓለማችን ክስተት ነው፡፡ የተለምዶ ሚዲያዎችን (ሬድዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ጋዜጣ፣ ወዘተ.) ታሪክ የሚሆኑበት ዕድል አለ፡፡ ማኅበራዊ ሚዲያ ሁሉም ሰው ጋዜጠኛም፣ አርታኢም እንዲሆን ዕድል ፈጥሮለታል፡፡ በቅርቡ አሜሪካ ውስጥ የተካሄደው ጥናት እንደሚያሳየው 23 በመቶ የሚሆኑ ወጣቶች አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ያልተገባ መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያ ያስተላልፋሉ፡፡ አጀንዳ ይቀርፃሉ፣ ፖሊሲ ያስቀይራሉ፡፡ ሐሰተኛ ዜና (Fake News) አገሩን ይንጣል፡፡

የውጭ ኢኮኖሚ ግንኙነት አንድምታን ማን ይተነትንልናል?

የዓለም ባንክና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስተሮችን ለመሳብ በሯን ለንግድ ክፍት ለማድረግ የምትወስዳቸውን ዕርምጃዎች እያደነቁና እየሸለሙ ይገኛሉ፡፡ እኛ ከድህነታችን ጋር አገናዝበን በምሬት እርር ድብን ያልንበትን በውጭ ምንዛሪ ለውጥ ምክንያት የተከሰተ የዋጋ ንረት በአጠገቡ ቢያልፍም፣ የማይነካው የዓለም ባንክ አሳሳቢ አይደለም ለማለትም በቅቷል፡፡

አንድነት ተፈርቶ አገርን ማዋሀድ እንዴት!?

ከቀደመው የትግል አስተዋፅኦቸውም ሆነ ከአየር ኃይል ዋና አዛዥነታቸው ይልቅ (በዙም በዚያን ጊዜ ስለ እርሳቸው መረጃ ስለሌለኝ)፣  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተወዳጁ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በሚያቀርቧቸው ጠንካራ ምሁራዊ ሐሳቦች የማከብራቸው ሜጀር ጄኔራል አበበ ተክለ ሃይማኖት ሰሚ ካገኙ ጠቃሚ ሐሳቦችን እያነሱ ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ሳምንታትም በዚሁ ጋዜጣ ላይ ‹‹ኢትዮጵያዊነት በዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ያብባል-ይለመልማል›› በሚል ርዕስ ጥልቅ ትንታኔ በተከታታይ አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያዊነት በዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ያብባል - ይዘምናልም

ባለፈው ሳምንት ዕትም ጸሐፊው ማንነትን፣ የወል ማንነትን፣ የማንነቶች ብዝኃነትን፣ የማንነት ቅራኔዎችን፣ ብሔርተኝነትና አገራዊነትን፣ የኢትዮጵያዊነት እንቆቅልሽን፣ የኢትዮጵያዊነት ፖለቲካን፣ ወዘተ በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ትንታኔ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡ በዚህኛው ዕትም ደግሞ ሁለተኛውንና የመጨረሻቸውን ክፍል ያስነብቡናል፡፡

የኢሕአዴግ ‹‹ዴሞክራሲ›› እና ‹‹ማዕከላዊነት›› የመጨረሻ ምዕራፍ

የኢሕአዴግ መንግሥት ሥልጣን ላይ ከቆየባቸው 27 ዓመታት ባለፉት ሁለት ዓመታት ያጋጠሙት ፖለቲካዊ ችግሮች በጥልቀትና በውስብስብነት አስቸጋሪዎቹ ይመስሉኛል፡፡ የተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ኅብረተሰባዊ ጥያቄዎችን ባነሱ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተቃውሞና ተያይዞ በተፈጠረ ሁከት ዜጎች ክቡር ሕይወታቸውን አጥተዋል፣ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፣ ለፍተው ደክመው ያፈሩት ንብረት ወድሟል፡፡

አገራችን ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሰላም እንድትሸጋገር ለማድረግ የቀረበ የመነሻ ሐሳብ

ኢትዮጵያ አገራችን አሁን የምትገኘው የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በሕገ መንግሥቱ በተቀመጠው መሠረት የማይከበሩበት፣ ይህን ለማድረግ የሚያስችል የፖለቲካ ሥርዓት መፍጠር የሚጠበቅባቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች በፍፁም መንቀሳቀስ ያልቻሉበትና የአንድ ፓርቲ ፍፁም አምባገነን ኢዴሞክራሲያዊ አገዛዝ በሠፈነበት ሁኔታ ነው፡፡

ወደ ኋላ ሳያዩ ወደ ፊት መሄድ ይቻላል ወይ?

ይህች አገር ምናባዊ ሆናለች፡፡ በደራሲው ላይ እንደሸፈተ ገጸ ባህሪ መነሻውን እንጂ መድረሻውን ለመገመት አዳጋች ነው፡፡ አበቃላት ተብሎ ደረት ሲደቃ ድንገት ትባንናለች፡፡ ደግሞም ደህና ሆነች ሲባል ተመልሳ ታስጨንቃለች፡፡ በተቃዋሚው ጎራ ለአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ተጠያቂ የሚደረገው በብሔር ላይ የተመሠረተ ፌዴራሊዝም፣ በእነዚህ ወገኖች በሚወደስ ሌላ መድረክ ላይ ሲሞገስ እንሰማለን፡፡

በሕዝብ ውስጥ የጥላቻና የጥርጣሬ ስሜት መፍጠር መወገዝ አለበት

ምትክ ከማይገኝላቸው የተወሰኑ ነገሮች ውስጥ አገርና እናት ይገኙባቸዋል፡፡ ስለዚህም እኛ አገርን እንደ እናት ስለምንቆጥር ኢትዮጵያን እናት አገሬ ብለን እንጠራታለን፡፡ እነዚህን ሁለቱን በሌላ ለመተካት እንኳን ብንሞክር በእንጀራ እናትና በሌላ በምንኖርበት አገር ነው፡፡ እነዚህ ደግሞ እናትም አይደሉም፣ አገርም አይደሉም፡፡ ታዲያ እነዚህ ሁለቱም የሚከበሩትና የሚታፈሩት በልጆቻቸው ነው፡፡ የልጆቻቸው ማንነት ህልውናቸውን ይወስነዋል፡፡