Thursday, September 21, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

ክቡር ሚኒስትር

[ክቡር ሚኒስትሩ ለሁለት ቀናት የተካሄደውን የፓርቲያቸውን የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ አጠናቀው ወደ ቢሯቸው ሲመለሱ ቢሯቸው ውስጥ አማካሪያቸው አንድ ጽሑፍ በተመስጦ እያነበበ አገኙት]

ምንድነው እንደዚህ መስጦ የያዘህ ጉዳይ? መጡ እንዴ ክቡር ሚኒስትር፣ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያወጣውን መግለጫ እያነበብኩ ነው፡፡ ግን እኮ ፊትህ ላይ የመገረም ስሜት ይነበባል፡፡ አዎ፣ መግለጫው ላይ...

[ክቡር ሚኒስትሩ እየጠራ ያለውን ሞባይል ስልካቸውን ተመለከቱ፣ የህዳሴ ግድቡ ተደራዳሪ መሆናቸውን ሲያውቁ ስልኩን አነሱት]

ሃሎ... ጤና ይስልጥኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስልጥልኝ ክቡር ተደራዳሪ... የጥረትዎን ፍሬ በማየትዎ እንኳን ደስ አለዎት፡፡ እንኳን አብሮ ደስ አለን፣ ምን ልታዘዝ ታዲያ? የውኃ ሙሌቱንና አጠቃላይ የግድቡን የግንባታ ሁኔታ...

[የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሩ ክቡር ሚኒስትር ሌሊቱን በእንቅልፍ ልባቸው በህልም እየተወራጩ ሳለ የሞባይል ስልካቸው ጥሪ አነቃቸው። አለቃቸው ስለነበሩ ስልኩን በፍጥነት አነሱት]

በሌሊት ስለደወልኩኝ ይቅርታ፡፡ ችግር የለውም ክቡር ሚኒስትር፣ ምን ልታዘዝ? አንድ የአውሮፓ ባለሥልጣን ነገ በጠዋት ወደ አዲስ አበባ ይገባል። እሺ። ሌሎች የመንግሥት አመራሮች ስላልቻሉ እርስዎ መንግሥትን ወክለው ቦሌ ኤርፖርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ እረፍት አደርጋለሁ ብለው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ቢገቡም ባለቤታቸው በፖለቲካ ወሬ ጠምደው ይዘዋቸዋል]

ቆይ አንቺ ምን አሳሰበሽ? እንዴት አያሳስበኝም? አንቺን የገጠመሽ ችግር በሌለበት ለምንድነው ስለ አገሪቱ ፖለቲካ የምትጨነቂው? እኔን የገጠመኝ ችግር እንደሌለና እንደማይኖር በምን አወቅህ? ባለቤትሽ የመንግሥት ሰው ሆኖ እንዴት አንችን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በቅርበት ከሚያውቁት አንድ ወዳጃቸው ጋር የህዳሴ ግድቡ ፖለቲካዊ ሁነቶችን በተመለከተ በስልክ እየተነጋገሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ጊዜ ሰጥተው ሊያነጋግሩኝ ስለፈቀዱ እጅግ አመሠግናለሁ። አንተም ለህዳሴ ግድቡ ስኬት የምታበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ትልቅ ምሥጋና አለኝ። ክቡር ሚኒስትር የህዳሴ ግድቡ ለእኔ የኃይል ማመንጫ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ጉዳዮች አማካሪያቸው ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው]

እና ሕዝቡ ሥራችንን አልወደደውም እያልክ ነው? እኔ ባሰባሰብኩት መረጃ ያስተዋልኩት እንደዛ ነው ክቡር ሚኒስትር። እስኪ ምሳሌ ጠቅሰህ አስረዳኝ? ምን ዓይነት ትችት ነው የሚቀርበው? ምን እየተባለ ነው? መንግሥት...

[ክቡር ሚኒስትሩ በፓርቲያቸው የሕዝብ ድጋፍ ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት እንዲያካሂድ የተዋቀረው ኮሚቴ ሰብሳቢ ባቀረቡት የጥናት ውጤት ላይ እየተወያዩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር የተደረገው የዳሰሳ ጥናት የፓርቲው የሕዝብ ድጋፍ በፍጥነት እየቀነሰ መምጣቱን የሚያሳይ ነው። እኔ በዚህ ድምዳሜ አልስማማም! ክቡር ሚኒስትር እርሶ ባይስማሙም የተደረገው የዳሰሳ ጥናት የሚያሳየው እንደዚያ...

[በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለክትትልና ግምገማ የተሰማሩት ከፍተኛ አመራሮች ያገኙትን ውጤት ሪፖርት ያደረጉበት የቴሌቪዥን ፕሮግራምን የሚኒስትሩ ባለቤት ለብቻቸው በመገረም እየተከታተሉ ሳለ ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ...

እኔ ብቻ ይሆን ግን እንዲህ የምሆነው? ምን ሆንሽ? ግርም፣ ብግን የሚያረገኝ? ምንድነው ያስገረመሽ? የምትሠሩት ነገር ሁሉ ግርም ይለኛል። እንዴት... ምን ሰምተሽ ነው? ውይይቱ ላይ የሚባሉት ነገሮች ናቸው? ምን ሲባል ሰምተሽ ነው? ክልሉ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ አማካሪያቸው ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያዩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ከማኅበረሰባችን በተለያየ መልኩ ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰብን መሆኑ ሥጋት ፈጥሮብኛል። አትሥጋ... መፍትሔ መፈለግ እንጂ መሥጋት ጥሩ አይደለም፡፡ ለመፍትሔውም እኮ አቅም ያስፈልጋል። እንዴት? አቅም የለንም እያልክ ነው? ክቡር...

[ክቡር ሚኒስትሩ በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን የአርሶ አደሮች የማዳበሪያ እጥረት ቅሬታ ዘገባ እየተከታተሉ ሳለ ባለቤታቸው በጥያቄ ያዟቸው]

ሕዝቡ በጣም እየተማረረ መምጣቱን ግን ታውቁታላችሁ? በምን ምክንያት? በኑሮ ውድነቱም በሌላውም። ግን ግን? ግን ምን? ሕዝቡ ተማሯል ያልኩትን ተወውና ... እ ...? በአገሪቱ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት መኖሩን ግን ታውቃላችሁ? እንዴት አናውቅም?...

[ክቡር ሚኒስትሩ ‹‹ፈተናዎችን ወደ ዕድል መቀየር›› በሚል መሪ ቃል ከላይ የወረደው አቅጣጫ በከተማ አስተዳደሩ እንዴት እየተተገበረ እንደሚገኝ እየገመገሙ ነው] 

እንደምታውቁት የብልፅግና ጉዟችን በፈተናዎች የተሞላ ቢሆንም፣ መንግሥታችን ፈተናዎችን ወደ ዕድል መቀየር እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል። ትክልል ነው። የዛሬ አመጣጤም ከላይ የወረደው ይህ አቅጣጫ በከተማ አስተዳደሩ እንዴት እየተተገበረ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን ከዕገታ ካመለጠው አማካሪያቸው ጋር ስለሁኔታው እያወጉ ነው] 

እሺ እስኪ ስለገጠመህ ሁኔታ አጫውተኝ? ሁኔታ አሉት ክቡር ሚኒስትር? ያው ሙከራ እንጂ አላገቱህም ብዬ እኮ ነው? ዕድለኛ ሆኜ ለቀቁኝ እንጂ መታገቱንማ ታግቻለሁ። እኮ... እንዴት እንደለቀቁህ እንድታጫውተኝ እኮ ብዬ...

[ክቡር ሚኒስትሩ የፖለቲካ አማካሪያቸው እንዲፈጽም ባዘዙት አንድ ሚስጥራዊ ኃላፊነት ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ነው]

ነገሩ በዕቅዳችን መሠረት ጥሩ ውጤት ያመጣ ይመስለኛል፣ ትክክል ነኝ? በሚገባ ክቡር ሚኒስትር፣ ሴትየዋ ከሞላ ጎደል ያቀድናቸውን በሙሉ አድርገውታል። መቼም አንተ ተዓምረኛ ሰው ነህ፣ ለመሆኑ እንዴት ስትል...

[ክቡር ሚኒስትሩ ለባለቤታቸው ስለሰላም አስፈላጊነትና ስለመንግሥት አቋም እያስረዷቸው ነው] 

መንግሥት ስለሰላም አብዝቶ የሚናገረው ለምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? ኧረ ጨርሶ ሲናገር ሰምቼ አላውቅምኧ ይናገራል እንዴ? እንዴታ፡፡ ስለሰላም ይናገራል? አዎ፣ የመንግሥትም ሆነ የፓርቲያችን የሙሉ ጊዜ ሥራ በሰላም ላይ ነው። ይህንን አላውቅም...

[ክቡር ሚኒስትሩ የዕርዳታ ስንዴ ተመዝብሯል ተብሎ በመንግሥት ላይ ስለተሰነዘረው ክስ የተሟላ መረጃ እንዲቀርብላቸው ባዘዙት መሠረት አማካሪያቸው ያጠናቀረውን መረጃና ትንታኔ እያደመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር ካሰባሰብነው መረጃ መረዳት የቻልነው በጀመርነው የስንዴ ልማት ስኬታማ መሆናችን ያልገመትነው ዓለም አቀፍ ፖለቲካ ትግል ውስጥ እየከተተን ነው። እንዲቀርብልኝ የጠየኩት መረጃ እኮ ተፈጸመ ስለተባለው...
167,271FansLike
273,905FollowersFollow
13,700SubscribersSubscribe
- Advertisment -
- Advertisment -spot_img
- Advertisment -
Category Template 49 – Pandemic PRO - NewsInBrief | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

ትኩስ ዜናዎች

ትኩስ ዜናዎች እንዲደርሶ