የአፄ ቴዎድሮስ 150ኛ ዓመት መታሰቢያ
ከዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ጋር ስማቸው አብሮ የሚነሳው አፄ ቴዎድሮስ በአኃዳዊ የአገዛዝ ሥርዓት አገሪቷን ያስተዳደሩ መሪ ናቸው፡፡ በትውልድ ስማቸው ካሳ ኃይሉ፣ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ፣ በወታደራዊ ስማቸው መይሳው ካሳ እንዲሁም አንድ ለእናቱ የተባሉ የአፄውን የተለያዩ ማንነቶች የሚያንፀባርቁ ስያሜዎች ናቸው፡፡ የተወለዱትም አገሪቷ በባላባቶች ተከፋፍላ በምትመራበት በዘመነ መሳፍንት ወቅት ነበር። አባታቸው ደጃዝማች ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ የቋራ ገዢ ነበሩ።