Skip to main content
x

‹‹አንድ ባንክ ሲዘረፍ ማንም ቆሞ ማየት የለበትም››

ባለፈው ሳምንት በምዕራብ ወለጋ አካባቢ በተለያዩ ባንኮች ቅርንጫፎች ላይ ዘረፋ መካሄዱ ተሰምቷል፡፡ በአንዳንድ ቅርንጫፎች ላይም ያልተሳካ የዘረፋ ሙከራ እንደነበርም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በተደራጀና በታጠቀ ኃይል በተፈጸመው ዘረፋ ምክንያት በአካባቢው ያሉ የባንክ ቅርንጫፎች ሥራ ተስተጓጉሏል፡፡ እስካሁን ድረስ የተዘረፈው የገንዘብ መጠን ባይታወቅም፣ መጠኑን ለማወቅ መረጃ የማሰባሰብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

‹‹ቻይና ኢትዮጵያን ለምዕራባውያን መተው አትፈልግም›› አቶ ጌዲዮን ገሞራ፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ተመራማሪ

አቶ ጌዲዮን ገሞራ ጃለታ በፖለቲካና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በተመራማሪነት ለስምንት ዓመታት በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አገልግለዋል፡፡ በዚያ ቆይታቸው ወቅትም ከ80 ያላነሱ ጥናታዊ ጽሑፎችን በመሥራት በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ጭምር አሳትመዋል፡፡ ከእነዚህ ሥራዎቻቸው ውስጥም በቻይናና በአፍሪካ ግንኙነት ላይ ያተኮሩ ምርምሮቻቸው ይገኙበታል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ አገሬን እናድናት ብለን ከተነሳን ሁሉም ችግሮቻችን ይወገዳሉ››

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የ88 ዓመት አዛውንት ናቸው፡፡ በምዕራብ ወለጋ ቦጂ ዲርመጂ አካባቢ የተወለዱት አቶ ቡልቻ የመጀመርያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በኢኮኖሚክስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና አሜሪካ ከሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ወስደዋል፡፡ በሕግ ዲግሪ አላቸው፡፡ በንጉሡ ዘመን የገንዘብ ምክትል ሚኒስትር ሆነው ሠርተዋል፡፡ ከዚያም በኋላ በዓለም ባንክ በቦርድ ዳይሬክተርነት አገልግለዋል፡፡

‹‹ብሔራዊ ባንክ መቼ እንደሚመለስ የማይታወቅ ገንዘብ ነው ለመንግሥት የሚያበድረው›› አቶ አብዱልመናን መሐመድ፣ የተመሰከረላቸው የሒሳብ አዋቂና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ተንታኝ

አቶ አብዱልመናን መሐመድ በ1988 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ንግድ ሥራ ኮሌጅ በመመረቅ በባንክ ውስጥ ለአጭር ጊዜ ካገለገሉ በኋላ፣ በውጭ ኦዲተርነት እስከ 1998 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ኦዲተርነትና የኦዲት ኃላፊ ባለው ዕርከን አገልግለዋል፡፡

‹‹እውነተኛ ውድድር ሲመጣ ባንኮቻችንና የኢንሹራንስ ኩባንያዎቻችን መሸሸጊያቸው ኅብረተሰቡ ነው›› አቶ ፍቅሩ ፀጋዬ

አቶ ፍቅሩ ፀጋዬ የኢትዮጵያ የጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር የቢዝነስ ዴቨሎፕመንትና የኮርፖሬት ጉዳዮች ኃላፊና የቦርድ ጸሐፊ በመሆን እያገለገሉ ናቸው፡፡ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ከህንድ የማስትሬት ዲግሪያቸውን ሲያገኙ፣ በሰው ሀብት አስተዳደርና በተቋም ግንባታ፣ እንዲሁም በጋዜጠኝነትና በኮሙዩኒኬሸን መስክ ሁለት የማስትሬት ዲግሪዎችን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡

‹‹የኮርፖሬሽኑን ቤቶች በሕገወጥ መንገድ በያዙና ባስተላለፉ ላይ ዕርምጃ ይወሰዳል››

በኢትዮጵያ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የመኖርያ ቤቶች እጥረት እንዳለ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጠረው እጥረት ነው፡፡ የደርግ ዘመን ካበቃ በኋላ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በሕዝብ ቁጥር ዕድገቱ ልክ የመኖሪያ ቤቶች ባለመገንባታቸው፣ ጫናው መሰማት የጀመረው ዘግይቶ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ1996 ዓ.ም.

‹‹ከ6.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚፈልጉ የኤሌክትሪክ ኃይልና የትራንስፖርት ፕሮጀክቶችን በመንግሥትና በግል አጋርነት ለማከናወን የጨረታ ሒደት እየተጠበቀ ነው››

ተሾመ ታፈሰ (ዶ/ር) ዋና ዳይሬክተር በመሆን በቅርቡ በአዋጅ የተቋቋመውን የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነት ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የተሰኘውንና በገንዘብ ሚኒስቴር ሥር የሚገኘውን መሥሪያ ቤት በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ተመድበው ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡

‹‹በነዳጅ ላይ እየተከሰተ ያለው ችግር አሻጥር ነው›› አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም፣ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ

አገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከምታወጣባቸው የገቢ ምርቶች ውስጥ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ ነዳጅ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በዓመት እስከ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ለነዳጅ ግዥ ታወጣለች፡፡

‹‹ወደብ አልባ አገር ሆኖ ባህር ኃይል መገንባት ይከብዳል››

ካፒቴን አየለ ኃይሌ፣ የቀድሞ ባህር ኃይል አካዴሚ ዋና አዛዥና የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት የሥልጠና ማዕከል መሥራች ካፒቴን አየለ ኃይሌ የተወለዱት የቀድሞው ሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ኤጀርሳ ጎሮ ለመድረስ ሦስት ኪሎ ሜትር ሲቀረው በሚገኘውና ልዩ ስሙ ጣጤሳ በተባለው መንደር ነው፡፡ የሦስት ዓመት ሕፃን እያሉ አባታቸው በጦር ሜዳ በፋሺስት ጣሊያን ጦር ተረሽነዋል፡፡ አባቶቻቸው በጦር ሜዳ ለተሰውባቸው ልጆች ተብሎ በተቋቋመው ሐረር ልዑል ራስ መኮንን የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከዚያም በአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ትምህርት ቤት ገብተው ተምረዋል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ያለበትን ጉዞ ባናጨናግፍ ጥሩ ነው›› አቶ ግርማ ዋቄ፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

አቶ ግርማ ዋቄ በወጣትነታቸው ኢትዮጵያ አየር መንገድ በመግባት፣ እዚያው ተምረውና አድገው በተለያዩ ኃላፊነት ቦታዎች ለ34 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በመካከል ቅሬታ አድሮባቸው ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሄደው የገልፍ አየር መንድንና ዲኤቾ ኤል ኩባንያን በኃላፊነት አገልግለዋል፡፡