Skip to main content
x

‹‹በሥራ ላይ ያለው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና ስትራቴጂ የቆየና አላስፈላጊ ዝርዝሮችን የያዘ ስለሆነ ነው የሚቀየረው›› አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ (ዶ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ

በኢትዮጵያ እየተደረጉ ካሉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች መካከል አንዱና የበርካታ ባለሙያዎችን ትኩረት የሳበው፣ በውጭ ጉዳይና በአገራዊ ደኅንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ የሚደረገው ማሻሻያ ነው፡፡ በሥራ ላይ ያለው ፖሊሲና ስትራቴጂ ከ17 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን፣ አሁን ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ በእጅጉ በመቀየሩ ፖሊሲውና ስትራቴጂውን ማሻሻል የግድ ብሏል፡፡

‹‹ችግራችሁ ይህ ነው የሚለውን የምዕራባውያን አተያይ መሞገት መቻል አለብን›› ኤልሳቤጥ ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር

ኤልሳቤጥ ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር) ለስድስት ዓመታት ያህል የኢትዮጵያ የጥናት ተቋምን በዋና ዳይሬክተርነት መርተዋል፡፡ በመቀጠልም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለፈለገ ሰላም ትምህርት ቤት መምህር በመሆን በማገልገል ላይ ናቸው፡፡

‹‹አብዛኞቹ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ችግራቸው ብዙ ነው››

አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ ከተሾሙ ጥቂት ወራት ተቆጥረዋል፡፡ በዚህ ወቅት የተቋሙን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴና ተቋሙ ስለሚገኝበት ደረጃ ሰፊ ግምገማ ማካሄዱን ይናገራሉ፡፡

‹‹የሕዝብ ጥያቄ ባልሆነ ጉዳይ ካልተጠነቀቅን ጠንቁ ለአገር ሊተርፍ ይችላል››

አቶ ክቡር ገና የአዲስ አበባና የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ በተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ መጣጥፎችን በማቅረብ ይታወቃሉ፡፡

‹‹የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ለኢትዮጵያ ይዞ የመጣው መልካም ዕድል ነው›› አቶ እንዳልካቸው ስሜ፣ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ

በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ አኅጉር ነፃ የንግድ ቀጣና ለመመሥረት የተጀመረውን እንቅስቃሴ በመደገፍ 49 አገሮች ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ የአፍሪካን የእርስ በርስ የንግድ ልውውጥ ለማጠናከርና የጠነከረ ኢኮኖሚ ለመገንባት እንዲረዳ ታስቦ አገሮቹ የፈረሙት፡፡

‹‹ከዘመቻና ሩቅ አልመው ከማይመለከቱ ፖለቲካዊ ቅኝት ካላቸው አሠራሮች መውጣት አለብን››

ደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) በተለይም በኢትዮጵያ ግብርና መስክ ከሚጠቀሱ ዋነኛ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ለዓመታት ከመምህርነት እስከ ተማራማሪነትና አማካሪነት በካበተው ተሞክሯቸው፣ በሚያቀርቧቸው ጥናታዊ ሥራዎችና በሚጽፏቸው መጻሕፍት በዘርፉ ባለሙያዎች ዘንድ በጉልህ የሚታወቁት ደምስ (ዶ/ር)፣ ከሙያቸው አኳያ መንግሥትንም ሆነ ሌሎች አካላትን በድፍረት በመተቸት የሚታወቁና ለሙያቸው ተገዥ ከሚባሉ ምሁራን መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

‹‹የአገሪቱ የፖለቲካ ሽግግር ጤናማ ነው ቢባልም አለመረጋጋቱ ግን ኢኮኖሚውን ሊያሽመደምደው ይችላል›› ቴዎድሮስ መኮንን (ዶ/ር)፣ የኢንተርናሽናል ግሮዝ ሴንተር ካንትሪ ኢኮኖሚስት

ቴዎድሮስ መኮንን (ዶ/ር) ኢንተርናሽናል ግሮዝ ሴንተር የተባለ የምርምር ተቋም ውስጥ ካንትሪ ኢኮኖሚስት በመሆን እያገለገሉ ናቸው፡፡ ተቋሙ በተለይ በኢኮኖሚና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ጥናት በማድረግ፣ ለፖሊሲ አውጪዎች ጭምር ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶችንና ምክረ ሐሳቦችን ያቀርባል፡፡

‹‹በጃፓን ያሉትን ዕድሎች ኢትዮጵያዊያን እንዲጠቀሙባቸው ለማስቻል በሚረዱ ሥራዎች ውስጥ እሳተፋለሁ›› ዶ/ር ናጋቶ ናትሱሚ፣ በጃፓን የኢትዮጵያ የክብር ቆንስላ

ዶ/ር ናጋቶ ናትሱሚ በሕክምናው መስክ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያላቸውና በከንፈር ብሎም በላንቃ መሰጠንቅ ሕክምና መስክ ስፔሻላይዝ ያደረጉ ጃፓናዊ ምሁር ናቸው፡፡ የጃፓን የላንቃ መሰንጠቅ ፋውንዴሽንን በዳይሬክተርነት የሚመሩት ዶ/ር ናትሱሚ፣ በበርካታ አገሮች ውስጥም በሙያቸውና ከሙያቸው ውጪ ባሉ መስኮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

‹‹የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ በሚቀጥሉት አምስትና አሥር ዓመታት ምን መልክ መያዝ እንዳለበት የሚያሳይ ፍኖተ ካርታ ዝግጅት እየተደረገ ነው›› ይናገር ደሴ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ወደ ኃላፊነት ከመጡ ወዲህ የመጀመርያ የሆነውን መግለጫ ለጋዜጠኞች ሰጥተዋል፡፡ እሳቸው በሰጡት መግለጫ በዋናነት ትኩረት ያደረጉት የአገሪቱን ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ በተለይም ከወጪ ንግድ ገቢ ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮች ላይ ነው፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ግን አጠቃላይ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ያስቃኘም ነበር፡፡

‹‹የውጭ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው አመኔታ እየጨመረ ስለሆነ በርካታ ሥራዎችን ለማከናወን ሲመጡ እያየን ነው››

ሚስተር አዳሙ ላባራ የዓለም ባንክ የግሉ ዘርፍ ቀኝ እጅ እንደሆነ በሚነገርለት የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይኤፍሲ) የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የጂቡቲ፣ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ የሶማሊያና የሱዳን ኃላፊ ናቸው፡፡