Skip to main content
x

‹‹በአስመጪነት ላይ የተመሠረተ የንግድ ሥርዓት ሊኖረን አይገባም››

ባለፉት ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት፣ በተለይ ንግድና ኢንቨስትመንት ማካሄድና ከቦታ ቦታ በነፃነት መንቀሳቀስ አሳሳቢ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በዚህ ሒደት በተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የዋጋ ንረት፣ ኮንትሮባንድ ደግሞ የመስፋፋት አዝማሚያ አሳይቷል፡፡

‹‹መንግሥት የውጭ ብድር መፍራት የለበትም›› አቶ ፀደቀ ይሁኔ፣ የፍሊንትስቶን ሆምስ ኩባንያ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ

በኢትዮጵያ የሪል ስቴት ቢዝነስ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ ከሚገኙት አገር በቀል ኩባንያዎች ውስጥ ፍሊንትስቶን ሆምስ ይጠቀሳል፡፡ ኩባንያው በተለይ በአሁኑ ወቅት በርካታ ፕሮጀክቶችን በማንቀሳቀስም ይታወቃል፡፡ ፍሊንትስቶን ሆምስ በዚህ ዘርፍ ከአሥር ዓመታት በላይ የቆየ ሲሆን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን አስረክቧል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ በየትም ሥፍራ በነፃነት ተንቀሳቅሰን የምንሠራባት የጋራ ቤታችን መሆኗን መቀበል አለብን››

በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ከተሰማሩ ውጤታማ ከሚባሉ ባለሀብቶች መካከል፣ የኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ኩባንያ መሥራችና ሊቀመንበር አቶ ብዙአየሁ ታደለ አንዱ ናቸው፡፡ አቶ ብዙአየሁ በኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ሥር የሚተዳደሩና በተለያዩ ኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ የተሰማሩ ከ25 በላይ የሚሆኑ የተለያዩ ኩባንያዎችን በሊቀመንበርነት ይመራሉ፡፡

‹‹ጥቁር ገበያውን ለመቀነስ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ማስፋፊያ አሠራሮችን ማስፈን ይገባል››

አቶ አዲሱ ሃባ በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ባንኮች አባል የሆኑበት የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበርና የደቡብ ግሎባል ባንክ ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ በባንክ ኢንዱስትሪው ከ40 ዓመታት በላይ የሠሩ ሲሆን፣ በተለይ የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ በኋላም የአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንት በመሆን ሠርተዋል፡፡

‹‹ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ በኋላ ለሚመጣው ለውጥ ራሱን ማዘጋጀት አለበት››

ኢትዮ ቴሌኮም ረቡዕ ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ይፋ እንዳደረገው በተለያዩ አገልግሎቶቹ ላይ የዋጋ ቅናሽ አድርጓል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም አዲሷ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው፣ ኢትዮ ቴሌኮም የታሪፍ ማሻሻያ ብቻ ሳይሆን የደንበኞች ጥያቄዎች ሆነው ሳይፈቱ የቆዩ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ አንዳንድ አሠራሮች ተስተካክለዋል፡፡

‹‹በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ 2.2 ሚሊዮን ወገኖች ድጋፍ እያደረግን ነው››

በኢትዮጵያ በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ለችግር የሚዳረጉ ወገኖችን ማየት የተለመደ ቢሆንም፣ በግጭት ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖች ከቀዬአቸው ተፈናቅለው የሰው እጅ ማየታቸው ግን እንግዳ ነው፡፡

‹‹በጥቂት የፖሊሲ ማስተካከያ ብቻ አገሪቱ የምትለወጥባቸው ዕድሎች ብዙ ናቸው››

አቶ ጌታቸው ረጋሳ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ናቸው፡፡ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በኢኮኖሚክስ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በዴቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ አግኝተዋል፡፡

‹‹የነዳጅ መገኘት ተስፋ የሚሰጠው በአገር ውስጥና በውጭ እንዴት እንደምንጠቀምበትና እንደምናስተዳድረው በቅጡ ስናውቅ ነው››

ደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) ጎምቱ ከሚባሉት አንጋፋ የግብርና ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ከ40 ዓመታት በላይ በኢኮኖሚው መስክ በልዩ ልዩ መስኮች ሙያዊ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

‹‹ከእኔ ክስና እስራት በስተጀርባ በመንግሥት ውስጥ ጡንቻቸው የጠነከረ ማፊያዎች ነበሩ››

የዛሬው የቆይታ አምድ እንግዳ አቶ መላኩ ፈንታ ናቸው፡፡ የ50 ዓመት ጎልማሳው አቶ መላኩ ከ1981 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2005 ድረስ በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ከጀማሪ ኤክስፐርትነት እስከ ሚኒስትርነት ባሉ ኃላፊነቶች

‹‹ኢኮኖሚው ወይም አገር ሳይንኮታኮት የምናድንበት ዕድል ከሰጠ ለውጡ ትልቅ ስጦታ ነው›› አቶ አወት ተክኤ፣ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ

አቶ አወት ተክኤ የኢኮኖሚ ባለሙያ ናቸው፡፡ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በተመሳሳይ በኢኮኖሚክስ ከባንግሎር ዩኒቨርሲቲ (ህንድ) አግኝተዋል፡፡