Skip to main content
x

‹‹የነዳጅ ፍለጋው ወደፊትም ስለሚቀጥል የሚፈለገው የክምችት መጠን እንደምንደርስ ተስፋ አደርጋለሁ››

አቶ ታደሰ ጥላሁን ላለፉት 40 ዓመታት በነዳጅ ኢንዱስትሪው ውስጥ የካበተ ልምድ አላቸው፡፡ በተለያዩ የኃላፊነት መስኮች ለረዥም ዓመታት በዘርፉ ሙያዊና አስተዳደራዊ ክህሎት ያዳበሩት አቶ ታደሰ፣ ከሼል ኩባንያ ጋር ከኢትዮጵያ ባሻገር በኬንያና በናይጄሪያም አገልግለዋል፡፡

‹‹ለግሉ ዘርፍ ክፍት የሚሆኑ ዘርፎች አሉን›› አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራዕይ 2025 የተባለውን የ15 ዓመት የዕድገት መርሐ ግብር ቀርጾ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረ እ.ኤ.አ. 2010 ጀምሮ ባሉት ስምንት ዓመታት ውስጥ በሦስት እጥፍ አድጓል፡፡

‹‹የኢኮኖሚ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያስፈልገናል››

አቶ መስፍን ነመራ ከ17 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውስጥ በልዩ ልዩ ኃላነት መስክ ያገለገሉ የፋይናንስ ባለሙያ ናቸው፡፡ እኚህ የቀድሞ የባንኩ ባለሙያ ከ1997 ዓ.ም. ወዲህም በፖለቲካው መስክ ተሳትፎ በማድረግ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን ማገልገላቸውም ይታወቃል፡፡

‹‹የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ማንም ኢትዮጵያዊ የሚዘለው ጉዳይ አይደለም››

ያዕቆብ ኃይለ ማርያም (ዶ/ር) ታዋቂ የሕግ ምሁር፣ ፖለቲከኛና ጠበቃ ናቸው፡፡ በናይጄሪያና በካሜሩን መካከል ተከስቶ የነበረውን የድንበር ይገባኛል ጥያቄ ለመፍታት በሥፍራው ከተሰማሩ ባለሙያዎች አንዱ ነበሩ፡፡

‹‹እኛ በራችንን ዘግተን ስንቀመጥ በዓለም ላይ ግን መሄጃ ያጣ የገንዘብ ውቅያኖስ አለ›› አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ባለሙያ

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ አክሰስ ሪል ስቴት ኩባንያን በማቋቋምና በቦርድ አመራር ሥራ አስፈጻሚነት  በመምራት እስከ ቅርብ ጊዜ ድርስ መርተውታል፡፡ በርካቶች አዳዲስ የኢንቨስትመንት ሐሳቦችን በኢትዮጵያ የተገበሩ፣ የፋይናንስ ኢንዲስትሪው ውስጥ ባለአንድ ቅርንጫፍ ባንክ የሚል መነሻም ዘመን ባንክን ያደራጁ እየተባሉም ይጠቀሳሉ፡፡

‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በኢሕአዴግ አመራሮች የተለመደውን የፖለቲካ ሰዋሰውና መዝገበ ቃላት ቀይረዋል›› አቶ አበባው አያሌው፣ የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ ታሪክ መምህርና ተመራማሪ

አቶ አበባው አያሌው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ትምህርት ክፍል ከ1991 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2002 ዓ.ም. በታሪክ መምህርነት ሠርተዋል፡፡ ከ2003 ዓ.ም. በኋላ እስካሁን ድረስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ የሥነ ጥበባትና ዲዛይን ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ ታሪክና በኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ ታሪክ በመምህርነት እያገለገሉ ናቸው፡፡

‹‹የአፍሪካውያን ፍልሰት በሜድትራኒያን ባህር ከመስጠም በላይ ሌሎች እውነታዎች እንዳሉት መገንዘብ ይገባል››

ሐሙስ ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ስደተኞችንና ስደትን የተመለከተው ሪፖርት ሌላ ዕይታ ይዞ ብቅ ብሏል። አፍሪካ የጎስቋላ ስደተኞች አመንጪ ማዕከል ብቻም ሳትሆን፣ የስደተኞች ተቀባይና ማረፊያ ስለመሆኗ የሚከራከረው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የንግድና የልማት ጉባዔ (UNCATD) ሪፖርት ነው።

‹‹የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትና ምክትላቸው ከሥልጣናቸው መቼ እንደሚወርዱ አይታወቅም››

አቶ ጌታሁን ሁሴን (ኢንጂነር) በኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነው የኢትዮጵያ አሠሪዎች ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በሲቪል ኢንጂነሪንግ ከዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ወስደዋል፡፡ የማስተርስ ዲግሪያቸውን በዓለም አቀፍ ቢዝነስ ከግሪኒውች ዩኒቨርሲቲ የወሰዱ ሲሆን፣ በሥራው ዓለም በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ ሠርተዋል፡፡

‹‹ከክልላዊ አስተሳሰብ ወጥተን ኢትዮጵያን እንዴት እንደምናደራጅ ማሰብ አለብን››

በኢትዮጵያ በንግድና በኢንቨስትመንት ሥራዎች ጉልህ ሥፍራ ካላቸው ጥቂት ባለሀብቶች መካከል አቶ በላይነህ ክንዴ አንዱ ናቸው፡፡ አቶ በላይነህ በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ግሼ ዓባይ አካባቢ ነው ተወልደው ያደጉት፡፡  ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ ዘለቀ ደስታ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ስምንተኛ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ፍኖተ ሰላም በመሄድ ዳሞት ትምህርት ቤት እስከ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ተከታትለዋል፡፡

‹‹የመንግሥት ኃላፊዎች ስለግብርና መር ኢንዱስትሪ ልማት መናገር ቢያቆሙም ስትራቴጂውን ግን ከወደቀበት በማንሳት መተግበር አለባቸው››

ጌታቸው ድሪባ (ዶ/ር)፣ በኢኮኖሚና በግብርና ሳይንስ መስክ ለዓመታት የካበተ የፊልድም፣ የስኮላርም ልምድ አላቸው፡፡ ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና በተመድ ውስጥ አገልግለዋል፡፡ ጡረታ እስከወጡበት እስካለፈው ዓመት እንኳ በተመድ የዓለም የምግብ ፕሮግራም የቻይና ዳይሬክተርና የፕሮግራሙ ተወካይ በመሆን አገልግለዋል፡፡