Skip to main content
x

‹‹በነፃነት የመደራጀትና የመደራደር መብት በሕገ መንግሥቱ መሠረት ይከበር ነው የምንለው››

አቶ ካሳሁን ፎሎ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ ኢሠማኮ የሠራተኞች መብት ለማስከበር የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ይታወቃል፡፡ በተለይ የመደራጀት መብትን ለማስከበር በብርቱ እየታገለ መሆኑን ይገልጻል፡፡

‹‹ኢኮኖሚው በቂ የውጭ ምንዛሪና የሥራ ዕድል መፍጠር ካልቻለ ስትራቴጂን በመፈተሽ የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ሥራ መሆን አለበት››

በኢኮሚክስ ሙያ መስክ የካበተ ልምድና ተሞክሮ ያላቸውና በማክሮ ኢኮኖሚ ባለሙያነታቸው የሚታወቁት ኢዮብ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ በፋይናስ መስክም የዓመታት ልምድና ዕውቀቱ አላቸው፡፡

‹‹የግሉ ዘርፍ ተወካይ በመሆናችን የንግዱን ማኅበረሰብ ድምፅ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለማሰማት ሞክረናል››

ባለፈው ሳምንት መጀመርያ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ጋር ወደ ሁለት ሰዓት ከ40 ደቂቃ የቆየ ውይይት አድርገዋል፡፡ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በኩል ከቀረቡ ጥያቄዎች በተጨማሪ፣ በምክክር መድረኩ ላይ የነበሩ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች አንስተዋል፡፡

‹‹አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የተራቆተ የውጭ ምንዛሪ ካዝና ስለሚያገኙ የአጭርና የረዥም ጊዜ ዕቅድ ማውጣት ይኖርባቸዋል››

አቶ ፀጋዬ አበበ በኢትዮጵያ ውስጥ በአትክልትና ፍራፍሬ አምራችና ላኪነት ሥራ ላይ ከተሰማሩ የመጀመርያዎቹ ባለሀብቶች አንዱ በመሆን ይታወቃሉ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን የአበባ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ አምራች ኩባንያዎችን በአባልነት የያዘው የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማኅበር መሥራችና የመጀመርያ ፕሬዚዳንት በመሆን አገልግለዋል፡፡ በአበባ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እርሻዎቻቸው ላይ ከ1,700 በላይ ሠራተኞችን አሠማርተዋል፡፡

‹‹ለሕዝብ እውነቱን ተናግሮ መልቀቅን የመሰለ ነገር የለም››

በመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት (1923 - 1967) ከነበሩት መሳፍንት ብቸኛው በሕይወት ያሉ ራስ ናቸው፡፡ ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ዮሐንስ፣ የአፄ ዮሐንስ 4ኛ የልጅ ልጅ ልጅ፡፡ በሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በሚኒስትርነት፣ በአውራጃና ጠቅላይ ግዛት አገረ ገዥነት የረዥም ዘመን አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡ የሥራና መገናኛ ሚኒስትር (1950 - 1953 ዓ.ም.) በነበሩበት ወቅት በቦርድ ሊቀመንበርነታቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወደ ጄት ዘመን ያሸጋገሩ፣ በተመሳሳይ ኃላፊነት በአውራ ጎዳና ባለሥልጣን ዓብይ ድርሻ የነበራቸው ናቸው፡፡

‹‹ማንም ቢሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መኖሩ አያስደስተውም››

ሚስ አሁና ኤዚያኮንዋ-ኦኖቼ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ቋሚ ተጠሪ፣ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪና በተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ፕሮግራም ቋሚ ተጠሪ በመሆን በኢትዮጵያ ተመድበው መሥራት ከጀመሩ ሦስት ዓመታት አስቆጥረዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2015 ኢትዮጵያ በመምጣት የተመድ ተጠሪ ሆነው በቆዩባቸው በእነዚህ ዓመታት፣ አብዛኛውን ጊዜ በአስቸኳይ የዕለት ደራሽ የምግብ ዕርዳታዎች ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ ለማድረግ የተገደዱባቸውን ተከታታይ ሦስት የድርቅ ዓመታትን ታዝበዋል፡፡

‹‹የብሔር ጥያቄ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ገዥ አስተሳሰብ ሆኖ መቀጠል የለበትም››

አቶ ልደቱ አያሌው ባለፉት 26 ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎአቸው ይታወቃሉ፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲ ከማቋቋም ጀምሮ በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል፡፡ አገሪቱ ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ከዘመኑ ተናኘ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡  

‹­‹ሙስናን መታገስ የማይችል አሠራር ነው ያሰፈነው››

በቅርቡ የእናት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በሰብሳቢነት እንዲመሩት ሁለተኛዋን ሴት የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡ የመጀመርያዋም ሆኑ ሁለተኛዋ የባንክ ቦርድ ሊቀመንበር የተሰየሙት በዚሁ እናት ባንክ ነው፡፡ በአገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ በዚህ የኃላፊነት ደረጃ ያገለገለ ሴት አልነበረም፡፡ የመጀመርያዋን የቦርድ ሊቀመንበር ተከትለው ሁለተኛዋ የባንኩ ቦርድ ሊቀመንበር መሆን የቻሉት ደግሞ ወ/ሮ ሐና ጥላሁን ናቸው፡፡

‹‹ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ያስፈለገበት አንዱ ጉዳይ ተተኪ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሰየምበትን የሽግግር ሒደት ለማየት ነው››

አምባሳደር ዶናልድ (ዶን) ያማማቶ፣ በአሜሪካ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ውስጥ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ትልቅ ቦታ ያላቸው ዲፕሎማት ናቸው፡፡ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ ለአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት ሚኒስትር ተብለው ከተሾሙ ስድስት ወራት አስቆጥረዋል፡፡ ቀድሞውንም በአፍሪካ የካበተ የዲፕሎማሲ ልምድ ያላቸው ጎምቱ በመሆናቸው ወደ ሥራ ለመግባት ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በመሆን አራት ለዓመታት ማለትም እ.ኤ.አ. ከ2006 እስከ 2009 ማገልገላቸው አይዘነጋም፡፡

‹‹በኢትዮጵያ የአየር ብክለት ጉዳይ የሰዎችን ትኩረት መሳብ የጀመረው ገና አሁን ነው››

በአሜሪካ መንግሥት የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አማካይነት የአየር ብክለትና የብክለት ደረጃን የሚለካ ጥራቱን የሚከታተል፣ ‹‹ኤር ኳሊቲ ፕላኒንግ ኤንድ ስታንዳርድስ›› በሚል መጠሪያ የሚንቀሳቀስ ጽሕፈት ቤት አለ፡፡ ጽሕፈት ቤቱ በአሜሪካ ያለውን የአየር ብክለት ደረጃ ከመለካት ባሻገር፣ ለብክለት መንስዔ የሆኑ ምንጮችን በመከታተልና በማጥናት ጭምር ይታወቃል፡፡ ሳራ ቴሪም የዚህ ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ የፖሊሲ ጉዳዮች አማካሪ በመሆን ያገለግላሉ፡፡