Skip to main content
x

‹‹ማባሪያ የሌለው መንደርተኝነትና ጎጠኝነት እየረበሸን ነው››

አባተ ጌታሁን (ዶ/ር)፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት   የወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2010 ዓ.ም. ብቻ 25 ሺሕ ተማሪዎችን በመደበኛውና በኤክስቴንሽን ፕሮግራም በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡ አንድ ሺሕ መምህራንና አንድ ሺሕ አምስት መቶ የአስተዳደር ሠራተኞችን ይዞ የማስተማር ሥራውን እያከናወነ ነው፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ ችግር ፈቺ የሆኑ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እሑድ ታኅሳስ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተካሄዶ በነበረው የአማራና የኦሮሞ ምሁራን ኮንፈረንስ ላይ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አባተ ጌታሁን (ዶ/ር) ተገኝተው ነበር፡፡ አባተ ጌታሁን (ዶ/ር)፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት   የወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2010 ዓ.ም. ብቻ 25 ሺሕ ተማሪዎችን በመደበኛውና በኤክስቴንሽን ፕሮግራም በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡ አንድ ሺሕ መምህራንና አንድ ሺሕ አምስት መቶ የአስተዳደር ሠራተኞችን ይዞ የማስተማር ሥራውን እያከናወነ ነው፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ ችግር ፈቺ የሆኑ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እሑድ ታኅሳስ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተካሄዶ በነበረው የአማራና የኦሮሞ ምሁራን ኮንፈረንስ ላይ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አባተ ጌታሁን (ዶ/ር) ተገኝተው ነበር፡፡

‹‹በኢትዮጵያ የምትከሰት ትንሿ ችግር ለጂቡቲም ከባድ ልትሆን ትችላለች››

ጂቡቲ ነፃነቷን ካገኘች 40ኛ ዓመቷ ላይ ትገኛለች፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መጠነ ሰፊ የመሠረተ ልማት አውታሮችን በመገንባት ላይ ትገኛለች፡፡ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ያላት ጂቡቲ እስከ 12 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ኢንቨስት በማድረግ አምስት አዳዲስ ወደቦችን ገንብታለች፡፡ የባቡር መስመር ለመዘርጋት እስከ 500 ሚሊዮን ዶላር አውጥታለች፡፡ እነዚህን ኢንቨስትመቶች የማካሄዷ መሠረታዊ መነሻው በኢትዮጵያ እያደገ የመጣው የገቢና የወጪ ንግድ ፍሰት እንደሆነ፣ የአገሪቱ የኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒስትር ኢሊያስ ሙሳ ደዋሌህ፣ በጂቡቲ ንግድ ምክር ቤት ጋባዥነት ወደ ጂቡቲ ላቀኑት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

‹‹የሕገ መንግሥት ‘ሪፎርም’ ለብዙ ዘመናት ሲንከባለሉ ለመጡና ለሚጨመሩ አንገብጋቢ አገራዊ ችግሮቻችን መላ የምንፈልግበት ዕድል ይሰጠናል››

አቶ ሞላ ዘገዬ፣ የሕግ አማካሪና ጠበቃ አቶ ሞላ ዘገዬ ጠበቃና የሕግ አማካሪ ናቸው፡፡ አቶ ሞላ ከንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ጀምሮ በውትድርና፣ በፖለቲካና አስተዳደር የመንግሥት ሥራ ያገለገሉም ናቸው፡፡ በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ትንታኔ በመስጠትም ይታወቃሉ፡፡ የ‘ውይይት’ መጽሔት ማኔጂንግ ኤዲተርም ናቸው፡፡ በቅርቡም በሕገ መንግሥት ‘ሪፎርም’ ላይ አነስ ያለ መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡

‹‹መንግሥት ፖለቲካዊው ሽኩቻ የልማት ጠንቅ ከመሆኑ በፊት ሊቆጣጠረው ይገባል››

ፕሮፌሰር ኬኒቺ ኦህኖ፣ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ከፍተኛ አማካሪ ፕሮፌሰር ኬኒቺ ኦህኖ እ.ኤ.አ. በ1987 ከስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን፣ በበርካታ የኢኮኖሚ ልማትና የኢንዱስትሪ ፖሊሲዎች ላይ በማማከርና በማስተማር፣ እንዲሁም በርካታ የምርምር ሥራዎችን በማሳተም ይታወቃሉ፡፡ በማኅበራዊ ሳይንስ መስክ ላበረከቷቸው አስተዋፅኦዎች ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል፡፡

‹‹በእኔ ዕይታ የአፈጻጸም ክፍተት ካልሆነ በስተቀር የፌዴራል ሥርዓቱ ችግር አላመጣም››

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከ1987 ዓ.ም. እስከ 1993 ዓ.ም. የኢፌዴሪ ርዕሰ ብሔር ወይም ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡ ከዚያ በፊት በሽግግሩ ጊዜ በመጀመርያ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ በኋላ የማስታወቂያ ሚኒስትር፣ እንዲሁም ጎን ለጎን የፓርላማ አባል ነበሩ፡፡ ከ1984 ዓ.ም. እስከ 1987 ዓ.ም. ሥራ ላይ የነበረውና የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥትን ያረቀቀው የሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽንም አባል ነበሩ፡፡ ሕገ መንግሥቱን ያፀደቀው የሕገ መንግሥት ጉባዔም አባልና ሰብሳቢ ነበሩ፡፡

‹‹የምርጫ ሥርዓታችን ትልቁ ፈተና ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ የማካሄድ እንጂ የመወከል ጉዳይ ነው ብዬ አላምንም››

አቶ ሙሼ ሰሙ፣ የቀድሞ የኢዴፓ ፕሬዚዳንትና አንጋፋ ፖለቲከኛ አቶ ሙሼ ሰሙ የቀድሞው የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከማንኛውም የፓርቲ ፖለቲካ ራሳቸውን ያገለሉ ቢሆንም፣ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ስለአገሪቱ ፖለቲካና ሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮች በግላቸው ሐሳቦችን ይሰነዝራሉ፡፡ ከፓርቲ ፖለቲካ ሙሉ በሙሉ የተገለሉት አቶ ሙሼ በአንድ የግል ባንክ በኃላፊነት በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡

‹‹አዲስ አመራር በመጣ ቁጥር የቀድሞውን እያፈረሱ ከመሄድ ይልቅ የተጀመረውን ማስቀጠል ይመረጣል››

አቶ መላኩ እዘዘው (ኢንጂነር)፣ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አዲሱ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከ70 ዓመታት በላይ ዕድሜ አስቆጥሯል፡፡ አንጋፋ ከሆኑ መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ተርታ የሚሠለፈው ይህ ንግድ ምክር ቤት፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ አመራር ለመምጣት በሚሹ ወገኖች ይደረጋል በተባለ ሽኩቻ ስሙ ሲነሳ ቆይቷል፡፡ በተለይ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫዎች በሚካሄዱበት ወቅት ተደጋጋሚ ውዝግቦችና ቅሬታዎች ሲስተዋሉ እንደነበር ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ በተደረገው ምርጫ ከበፊቶቹ በተሻለ ያለ ውዝግብ ተፈጽሟል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ለደን ያደላ ኢኮኖሚ ብትመሠርት ኖሮ ይህን ያህል የምግብ ዋስትና ችግርም ሆነ ድህነት ይኖራል ብዬ አልገምትም››

ሙሉጌታ ልመንህ (ዶ/ር)፣ በፋርም አፍሪካ የምሥራቅ አፍሪካ የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኃላፊ ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በደን ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪቸውን ያገኙት ሙሉጌታ ልመንህ (ዶ/ር)፣ ከኔዘርላንድስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሲያገኙ፣ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ደግሞ በስዊድን ተከታትለው በመምጣት ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ የደን ሳይንስ መስክ አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ ጊዜ ውስጥ 18 ዓመታትን ያሳለፉት በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በደን ሳይንስ መስክ በማስተማር እንደሆነ ገልጸው፣ የወንዶ ገነት የደን ምርምር ማዕከልን ተቀላልቀው ከማስተማር ባሻገር 90 የሚደርሱ በርካታ ምርምሮችን ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር ሲያከናውኑና የምርምር ውጤቶቻቸውንም ሲያሳትሙ ቆይተዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ እስካሁን የሚመጥናትን ፖለቲካ አላገኘችም››

አቶ ገብሩ አሥራት፣ አንጋፋ ፖለቲከኛ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ጥልቅ ተሃድሶ አካጂጃለሁ ባለና ከሁለት ዓመት በፊት ለተነሳ ሕዝባዊ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ጀምሬአለሁ ባለ ማግሥት አዳዲስ የፖለቲካ ክስተቶች መታየት ጀምረዋል፡፡ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል በተነሳ ግጭት በአሰቃቂ መንገድ የዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፡፡ በርካቶች ተፈናቅለዋል፡፡

‹‹በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ለኢትዮጵያ አንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር የማቅረብ ፍላጎት አለን››

አቶ አድማሱ ይልማ፣ የኮሜሳ የንግድና የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት   አቶ አድማሱ ይልማ ታደሰ የኢኮኖሚ ባለሙያ ብቻ ሳይሆኑ፣ በአፍሪካ ከፍተኛ ተቀባይነት ካገኙ የባንክ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች መካከል የሚመደቡ ናቸው፡፡ ባለፈው ዓመት ጥር ወር ከዚህ ቀደም የደቡብና ምሥራቃዊ አፍሪካ አገሮች የጋራ ገበያ ባንክ (ፒቲኤ ባንክ) እየተባለ የሚጠራውን ተቋም፣ ወደ ኮሜሳ ንግድና ልማት ባንክ እንዲለወጥ አድርገዋል፡፡