Skip to main content
x

‹‹ወጣቶች ተነሱ ተብሎ የሚደረገው ነገር ለእኔ እሳት የማጥፋት አሠራር ነው››

ዶ/ር ወልዳይ አመሐ፣ የኢኮኖሚ ባለሙያ ዶ/ር ወልዳይ አመሐ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚጠቀሱ የኢኮኖሚ ምሁራን መካከል አንዱ ናቸው፡፡ በኢኮኖሚ ሙያቸው ከዩኒቨርሲቲ ጀምሮ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ተሳትፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማኅበርን በፕሬዚዳንትነት ከማገልገላቸው በተጨማሪ፣ አያሌ መጻሕፍትን አሳትመዋል፡፡ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ጆርናሎችም የኢኮኖሚ ትንታኔዎች የሰጡባቸውን በርካታ የምርምር ሥራዎች አሳትመዋል፡፡

‹‹የተረጂዎች ቁጥር እጥፍ ቢሆን እንኳን የመቋቋም አቅም አለን››

አቶ አይድሩስ ሐሰን፣ የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአቅርቦትና የሎጂስቲክስ ዋና ዳይሬክተር ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ ሰፊ ቦታ የሚሸፍን የድርቅ አደጋ ደርሶባታል፡፡ በዚህም ድርቅ 10.2 ሚሊዮን ወገኖች ለምግብ ዋስትና ዕጦት የተዳረጉ ሲሆን፣ መንግሥት 15 ቢሊዮን ብር ወጪ በማድረግ አደጋውን ተጋፍጧል፡፡ በተያዘው ዓመትም እንዲሁ 5.6 ሚሊዮን ዜጎች ለአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ የተዳረጉ ሲሆን፣ ችግሩን ለመቋቋም 948 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል፡፡ በሁለቱም ተከታታይ የድርቅ አደጋዎች ይህ ነው በሚባል ደረጃ የውጭ ዕርዳታ ባይገኝም፣ መንግሥት ከራሱ ግምጃ ቤት በጀት በመመደብ ችግሩን ለመቀልበስ እየሞከረ ነው፡፡