እንቁላሎቿን ሆዷ ውስጥ የምትታቀፈው እንቁራሪት
እንቁላሎቿን ሆዷ ውስጥ የምትታቀፈው የአውስትራሊያ የእንቁራሪት ዝርያ (ጋስትሪክ ብሩዲንግ ፍሮግ) ያልተለመደ ዓይነት የመራቢያ ሥርዓት አላት፤ የዚህች እንቁራሪት ዝርያ ከ2002 ጀምሮ እንደጠፋ ይታሰባል የሚለው ጄደብሊው ዶት ኦርግ ድረ ገጽ ነው።
እንሽላሊቱ ኮሞዶ ድራጐን
ኮሞዶ ድራጐን የእንሽላሊት ዝርያ ነው፡፡ ከእንሽላሊት ዝርያዎች በትልቅነቱ የሚታወቀው ኮሞዶ፣ በማዕከላዊ ኢንዶኔዥያ ኮሞዶ ደሴት ላይ በብዛት ይኖራል፡፡ አንዱ ኮሞዶ ድራጐን እስከ 70 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን፣ ርዝመቱም ከሁለት እስክ ሦስት ሜትር ይደርሳል፡፡ መጋዝ የመሰሉ 60 ጥርሶች አሉት፡፡ ጥርሶቹ በተደጋጋሚ እየወለቁ የሚበቅሉም ናቸው፡፡
ድምፅ አልባ አጥፊዎች
ምስጦች ድምፅ አልባ አጥፊዎች በመባል ይታወቃሉ፡፡ ይህ ስም የተሰጣቸው ዛፎችን፣ የዛፍ ስሮችንና ተክሎችን እንዲሁም የእንጨት ውጤቶችን ከላይ ሳይሆን ከሥር ገብተው ውስጡን ቦጥቡጠው ስለሚበሉና ቅርፊት ብቻ ስለሚያስቀሩ ነው፡፡ ምስጦች ለ24 ሰዓት ሳያቋርጡ የሚመገቡ ሲሆን፣ የተመቻቸ ስፍራ ካገኙ እዚያው መጠለያቸውን ሠርተው ይሰፍራሉ፡፡
ፀጉሩ በክረምትና በበጋ የሚቀያየረው ሽኮኮ
ሽኮኮ ፅድ በሞላባችው ደኖች ውስጥ በብዛት ይገኛል። እንስሳው ረጅምና ፀጉራም በሆነው ጭራው በቀላሉ ይታወቃል። ፀጉሩ በክረምት ወቅት ቀይና ቡናማ ዓይነት ሲሆን፣ በበጋ ወቅት አመድማ ነጭ ይሆናል። ፍራፍሬና ተክሎች የሚመገብ ቢሆንም፣ ጫጩቶችንና የአዕዋፍ እንቁላል ሊበላ ይችላል። ክብደቱ እስከ ሁለት ኪሎ ግራም አካባቢ ይመዝናል።
አንበጦችና የነርቭ ሴላቸው
በራሪዎቹ አንበጦች እንቅስቃሴያቸውን የሚቆጣጠሩት በነርቭ ሴላቸው አማካይነት መሆኑ ይወሳል፡፡ ጄ ደብሊው ኦርግ በድረ ገጹ እንደጻፈው፣ በመንጋ የሚጓዙት አንበጦች ‹‹በአንድ ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ውስጥ 80 ሚሊዮን›› አንበጦች አብረው ሊበርሩ ይችላሉ፡፡
ትኩስ ፅሁፎች