Thursday, December 8, 2022
ሌሎች ዓምዶች

  ሥነ ፍጥረት

  - Advertisement -
  Category Template - Week PRO | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
  - Advertisement -

  አነር

  አነር (Several - Felis Serval) አነስተኛ ከሆኑት የድመት አስተኔ አባሎች ሁሉ እግሩ የረዘመ፣ አንጻራዊ ከፍታ ያለው ነው፡፡ የሚገኘው በአፍሪካ ብቻ ነው፡፡ የወንዱ ክብደት 13 ኪ.ግ. ገደማ ሲሆን፣ የሴቷ ደግሞ 11 ኪ.ግ. ገደማ ነው፡፡

  የምዕራባውያን አጋዘን

  ከአጋዘን ዘር የሚመደበው “ሮ አጋዘን” የምዕራባውያን አጋዘን በመባልም ይታወቃል፡፡  ወንድ ሮ አጋዘን ቀንዱ ቅርንጫፍ ያለው ሲሆን፣ አንድ ትልቅ ሮ አጋዘን ቁመቱ ከ64 እስከ 89 ሴ.ሜ ሊደርስ ይችላል።

  የአዕዋፍ ዝርያዎች የተለያዩ ባህርያት

  በዚህ አርዕስት ስር አንባቢያንን ሊያስደንቁና ሊስቡ ይችላሉ ተብለው የተመረጡ ዝርዝር ነገሮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡ እነዚህ ዝርዝር ነገሮች የተለያዩ የአዕዋፍ ዝርያዎችን የተለያዩ ባህርያትንና ተፈጥሮአቸውን የሚዳስሱ ናቸው፡፡

  ዛፍ ላይ የሚወጣ አሳ

  ፐርች (Perch) ከሚባሉት የአሳ ዝርያዎች ውስጥ ዛፍ ላይ የሚወጡ ዝርያዎች አሉ፡፡ እነዚህ አሳዎች በቁመት ከ7 እስከ 20 ሳ.ሜ. ሲደርሱ አነስተኛ መጠን አላቸው፡፡ በስንጥባቸው ሽፋን ላይ የሚገኘውን ተንቀሳቃሽ ሹል የአካል ክፍልን በመዘርጋት መሬት ሲቆነጥጡ ጭራና የፊት ክንፈ-አሳ (እግርን የተካው) በመጠቀም ደግሞ በኃይል ወደፊት ይገፋሉ፡፡

  ታይገር

  ታይገር እስያዊ እንስሳ ነው፡፡ በአፍሪካ ጨርሶ አይገኝም፡፡ ቀድሞ የሚገኝባቸው ሥፍራዎች፣ ከቱርክ ጀምሮ እስከ መካከለኛውና ምዕራብ እስያ ይደርስ ነበር፡፡ አሁን የሚገኝባቸው ግን፣ ከሕንድ እስከ ቪየትናም፣ ከዚያም በሳይቤሪያ፣ በቻይና፣ በኮሪያና በሱማትራ ኢንዶኔዥያ ነው፡፡

  ሸንቃጣው የመሬት ትል

  እግር የለሹ ሸንቃጣ የመሬት ትል የመሰሉና አካላቸው በቅርፍ የተሸፈኑ ሴሲሊያን ይባላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በጣም አጭር ወይም ጭርሱኑም ምንም ጅራት የሌላቸው ናቸው፡፡ ጎሬ ውስጥ ነዋሪ እንደመሆናቸው ምግባቸውም ትላትሎችና ሌሎች አነስተኛ እንስሳት ናቸው፡፡

  ድኩላ

  ድኩላ  መካከለኛ መጠን ያለው፣ ከሰሐራ በስተደቡብ በአብዛኛዎቹ ሥፍራዎች የሚገኝ እንስሳ ነው፡፡ የወንዶቹ ክብደት ከ40 እስከ 80 ኪሎ ግራም ሲሆን፣ ሴቶቹ ደግሞ ከ25 እስከ 60 ኪሎ ግራም ይመዝናሉ፡፡ ቀንድ ያላቸው ወንዶቹ ብቻ ናቸው፡፡ ቀንዳቸው አንድ ጥምዝ ብቻ ነው ያለው፡፡ ቀጥ ያለ ይመስላል፡፡

  ጉማሬ እና የውኃ ላይ ኑሮው

  ጉማሬዎች በአንድ ወይፈን የሚመሩ ከአሥር እስከ 15 የሚደርስ አባላት ባሉት መንጋ የሚኖሩ ማኅበራዊ እንስሳት ናቸው። እስከ 150 የሚደርሱ አባላት ያሏቸው መንጋዎች የታዩባቸው ጊዜያትም አሉ።

  ውድንቢ

  ውንድቢ ከአጋዘን አስተኔዎች ሁሉ ግዙፍ  ነው፡፡ ወንዱ በአማካይ ከ500 እስከ 600 ኪግ ሲመዝን ሴቷ ከ340 እስከ 445 ኪግ ትመዝናለች፡፡ ሁለቱም ፆታዎች አጫጭርና ጥምዝ ቀንድ አላቸው፡፡ የወንዱ ቀንድ አጠር ብሎ (54 ሴሚ) ወፍራም ነው፡፡ የሴቶቹ ረዘም ይላል 60.5 ሴሚ፡፡ ከአካሉ አንፃር ራሱ አጭር ነው፣ ጆሮው አጭርና ቀጭን ነው፡፡

  ጨኖ

  ጨኖ ግራጫ ቢጤ የሆነ፣ ፈርጠም ያለ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እስከ ደቡብ አፍሪካ፣ በተጨማሪም በኮንጎ ደኖች የሚገኝ ጦጣ ነው። በኢትዮጵያ የሚገኘው ዓይነት ጨኖ የፀጉሩ ቀለም ግራጫና ጥቁር የሆነ፣ ፊቱ የጠቆረ ሰማያዊ የሆነ፣ አገጭና አንገቱ ነጭ ነው።
  - Advertisement -

  ትኩስ ፅሁፎች

  ትኩስ ዜናዎች ለማግኘት