Skip to main content
x

የሽግግር ወቅት ጉዳዮች ፈጣን ውሳኔና አመራር ይሻሉ

የ2011 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፖለቲካ መሪዎችና ተዋናዮች የኢትዮጵያን የብሔር ፖለቲካ አየር በአንድ ወገን በታሪክ ሻሞ ትርክቶችና መግለጫዎች አፍነውታል። በሌላው ወገን በማንነት፣ በወሰን፣ በክልሎችና በከተሞች ባለቤትነት ጥያቄዎች ወጣጥረውታል። አሳሳቢና አስፈሪ መግለጫዎች እየተሠራጩ ነው። አሳሳቢና አስፈሪ ቅስቀሳዎች እያተካሄዱ ነው።

ሕዝብ ጌዴኦን በተመለከተ ከመሪዎቹ እውነት እንዲነገረው ይጠብቃል

በጌዴኦ ሕዝብ ላይ ለደረሰው የጠኔ ግፍና የሕይወት ሕልፈት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ መንግሥት ከተጠያቂነት ሊያመልጥ የሚችልበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም። ምንም ዓይነት ሐሰት፣ ምንም ዓይነት ሰበብ የተሠራውን ጥፋት ሊሸፍነውም አይችልም።

ከፖለቲካዊ መውገርገር ወደ ደልዳላ ሜዳ ማቅናት ይመረጣል

በዚህ ርዕስ ሥር ሰፋፊና ራሳቸውን የቻሉ በርካታ ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ለዛሬ ግን በተወሰኑ አንኳርና ወቅታዊ ችግሮች ላይ አንዳንድ ነጥቦችን በማንሳት፣ በአገራችን የተጀመረው ሁለንተናዊ ለውጥ የሚጎለብትበትን መንገድ ለማመላካት ተሞክሯል፡፡

ወጣ ወጣና እንደ ሸንበቆ…

ውብ አገራችን ኢትዮጵያ የጋራ ገንዘባችን ናት፡፡ መዲናችን አዲስ አበባማ በበለጠ ምክንያት የየትኛውም ኢትዮጵያዊ አሻራ ያረፈባት የሁላችንም መዳረሻ መሆኗን ልብ ይሏል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ ግብዞች ከተማይቱ መሀል ኦሮሚያ ላይ ስለምትገኝ፣ ይህ ኩነት ብቻውን ዛሬ ኦሮሚያ የሚባለው ክልል አንጡራ ሀብት ናት ሊሉን ሲዳዳቸው እየተመለከትን ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ከልብ ያስቃል፣ ያንከተክታልም፡፡

ግብር በሩጫ. . . !? በኮንሰርት. . . !?

የኦቶማን ኢምፓየር ፍልስጤምን ይገዛ በነበረበት ጊዜ ግብር ይጥል የነበረው ተክልና ዛፍን በመቁጠር ነበረ፡፡ ፍልስጤማውያን፣ ዓረቦችና አይሁዳውያን ይኼን ከባድ ቀረጥ በመፍራት ግብር በመጣያው ሰሞን ዛፍን ይቆርጡ፣ ተክሉን ይነቃቅሉ ነበር፡፡ በዚህም አካባቢውን ክፉኛ አራቁቶት በረሃማ አድርጎት እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያትታሉ፡፡

‘አዲስ አበባ የማን ናት?' የሚለው ጥያቄ ኢትዮጵያን የኢትዮጵያዊያን በማድረግ ይፈታል!

በእዚህ መጣጥፍ ሁለት ጉዳዮች ተነስተዋል፡፡ አንዱ የአዲስ አበባ ከተማ የባለቤትነት ጉዳይ ሲሆን፣ ሁለተኛው ከዚህ ጋር ተያይዞ በቅርቡ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሚተላለፉት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ጋር የተነሳው ውዝግብ ነው።

ለውጡን አለመደገፍ መብት ቢሆንም ለውጡን ማደናቀፍ ግን…

ሐሙስ የካቲት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢሕአዴግ ሊቀመንበር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ኢትዮጵያን ወደፈለጉት አቅጣጫ ሊመሩበት የሚያስችሏቸውን ሁለት ቁልፍ ሥልጣኖች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደማይፈልጓቸው አስታወቁ፡፡

በጅምላ ስም ማጠልሸት አያዋጣንም በደቦ ማሞካሸቱም ቢሆን አያዛልቀንም

ገና ከለጋ ዕድሜዬ አንስቶ በፈረንጅ አፍ እየተደጋገመ ሲነገር የምሰማው አንድ ዘይቤያዊ አነጋገር ትዝ ይለኛል፡፡ ሰውየው ብዙ ያወቀና በጥልቅ የተመራመረ በሚመስል አቀራረብ “All hasty generalizations are wrong” (በጅምላ የሚሰጡ ማጠቃለያዎች ሁሉ የተሳሳቱ ናቸው) በማለት ተራግሞ ሳይጨርስ በአንክሮ ያዳመጠው ትንታግ ባልንጀራው፣ “Including this one” (አሁን የምትለውን ጨምሮ) ሲል ባልተጠበቀ የመልስ ምት ኮረኮመውና አንገቱን አስደፋው አሉ፡፡

የምን መድበለ ፓርቲ?

መድበለ ፓርቲ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት የዕድገት ደረጃ አንፃር ከታየ የማይሠራ መሆኑንና ምርጫ እንደማያስፈልግ ሁለት ተከታታይ ጽሑፎችን አቅርቤአለሁ፡፡ በመሆኑም ይህ የመጨረሻውና የመደምደሚያው ጽሑፌ ይሆናል፡፡ ስለመድበለ ፓርቲም ይሁን ስለፌዴራሊዝም ወይም ስለሌላ ዓብይ የፖለቲካ ጥያቄዎች  አዎንታዊ መልስ ለመስጠት፣ በቅድሚያ አገርን በተለይም ያለችበትን የዕድገት ደረጃ ማወቁ እጅግ  አስፈላጊ ነው እላለሁ፡፡