Skip to main content
x

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሕክምና ከየት እስከ የት

በባህላዊ የሕክምና ጥበብ ድልድይ ተሻግሮ ለተዓምር የቀረቡ ፈውሶችን መስጠት የቻለው ዘመናዊ ሕክምና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ቆይቶ ነበር፡፡ ጉንፋን ሲይዘው ዳማከሴ ጨምቆ፣ አላስቆም አላስቀምጥ ለሚለው ጥርሱ ስራስር ነክሶ፣ ለሚያዋክበው ቁርጠት ጤና አዳም ጨምቆ፣ ክፉ መንፈስ ተጠናወተኝ ሲል በየሃይማኖቱ ፀልዮ፣ ድኝ ታጥኖ ሌላም ድንገተኛና አጣዳፊ ሕመም ሲያጋጥመው ቅጠል መበጠስ ለሚቀናው የኅብረተሰብ ዘመናዊ ሕክምና ብዙም አንገብጋቢ ጉዳይም አልነበረም፡፡

ዕውቅና ለሰብዓዊ አገልግሎት

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ ‹‹ለውጥን እንደግፍ›› በሚል መሪ ቃል ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በወጡ ሠልፈኞች ላይ በደረሰው የቦንብ ጥቃት ሕይወት የማዳንና ሰብዓዊ አገልግሎት ለሰጡ 115 በጎ ፈቃደኞችና ለቀይ መስቀል አመራሮች ዕውቅና ሰጠ፡፡

በቤቶች ኮርፖሬሽን መጋዘኖች የታጎረው የኤርትራዊያን ንብረት ባለቤቶቹን እየጠበቀ ነው

ከአቡነ ጴጥሮስ አደባባይ ወደ አውቶብስ ተራ (መርካቶ) መንገድ በስተቀኝ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ወረዳ 01 ቀበሌ 01 ጨው በረንዳ አካባቢ፣ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ይዞታ የሆኑ መንታ መጋዘኖች ከኢትዮጵያ በጦርነቱ ጊዜ የተባረሩ ኤርትራውያን ንብረቶችን እስካሁን ድረስ ይዘው ቆይተዋል፡፡

አዲሱ የጡት ወተት ፕሮጀክት

በመንግሥት ተቋማት ውስጥ ላሉ እናቶች የ120 ቀናት የወሊድ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ ይህ ቀድሞ ከነበረው የ90 ቀን ፈቃድ ጋር ሲነፃፀር ለውጡ ተጠቃሽ ቢሆንም፣ አሁን ያለው የወሊድ ፈቃድ ሕፃናትን በሚፈለገው ሁኔታ ጡት ለማጥባት የሚያስችል አይደለም፡፡

መንግሥት ጣልቃ ካልገባ በስተቀር አዲስ አበባ በውኃ እጥረት እንደምትመታ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አወቀ ኃይለ ማርያም (ኢንጂነር)፣ በአገሪቱ የሚገኙ ባንኮች ለውኃ ፕሮጀክቶች የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ተገቢውን ትኩረት በመንፈጋቸው ከአንድ ዓመት በኋላ ከተማው ከፍተኛ የውኃ እጥረት ሊያጋጥመው እንደሚችል አስጠነቀቁ፡፡

የደቂቅ ዘአካላት እሴቶች

ነገሮች ከመሬት ተነስተው ሲያረጁና ሲበሰብሱ፣ ጤናማው ሰው በበሽታ ሲዳከምና ሞት አፋፍ ሲደርስ፣ በዓይን የማይታዩ ፍጥረታት ለተከሰተው ነገር ሁሉ ማሳበቢያ ይደረጉ የነበረው በ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ነበር፡፡

ሦስተኛ ደረጃ የሕክምና ማዕከልን ለአዲስ አበባ የሰነቁት ሐኪሞች

በአሜሪካ በካናዳ፣ በአውሮፓና በሌሎችም አገሮች በሕክምና የተሰማሩ ቁጥራቸው ከ300 በላይ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች በአዲስ አበባ ከተማ ከመንግሥት በተገኘ 60 ሺሕ ካሬ ሜትር ላይ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ ሦስተኛ ደረጃ የሕክምና ማዕከል እየገነቡ ነው፡፡

የሐኪሞች የምሥጋና ቀን

በአደጋ የተጎዱን፣ በቁርጠት የተዋከቡን፣ በከባድ ደዌ የተንገላቱትን፣ በሞትና በሕይወት መካከል ሆነው የሚያጣጥሩትን በወሳንሳ አጋድሞ፣ በአምቡላንስ አጣድፎ፣ ሐኪም ቤት ማድረስ አማራጭ የሌለውና የተለመደ ጉዳይ ነው፡፡ ስቃይን የማስታገስና ከሕመም የመፈወስ ፀጋ የተሰጣቸው ሐኪሞች በሥራቸው ሊመሰገኑ ሲገባ ወቀሳ እንደሚበዛባቸው፣ የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ፕሬዚዳንት ዶ/ር ገመቺስ ማሞ ይናገራሉ፡፡