Skip to main content
x

ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ያስተናግዳል የተባለው ሆስፒታል ተመረቀ

በሰባት መቶ ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ጅማ የሕክምና ማዕከል ተመረቀ፡፡ ማዕከሉ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢ በምዕራብ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሚኖሩ ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች የሚጠቀሙበት ነው ተብሏል፡፡

በኤችአይቪ የመያዝ ምጣኔው ባለበት ቆሟል ተባለ

ኢትዮጵያ ውስጥ ከ17 ዓመታት በፊት በኤችአይቪ ኤድስ የመያዝ ምጣኔ በየዓመቱ 81 ሺሕ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ምጣኔው በዓመት ወደ 15 ሺሕ፣ አጠቃላይ ሥርጭቱም ከ15 ዓመት በፊት ከነበረው 5.8 በመቶ ወደ 0.9 በመቶ መውረዱን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አሚር አማን (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

የባለቤትነት ካርታ የመከነባቸው ቦታዎች ላይ የተዘጋጁት አዳዲሶቹ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች ሥራ ጀመሩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለዓመታት በባለይዞታዎች ባለመልማታቸው ምክንያት የባለቤትነት ካርታ ካመከነባቸው ቦታዎች መካከል፣ በአሥሩ ላይ ያዘጋጃቸው ጊዜያዊ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራዎች በሳምንቱ መጨረሻ ሥራ ጀመሩ፡፡

ምክትል ከንቲባው ከዚህ በኋላ የሚፈናቀል አንድም አርሶ አደር እንደማይኖር ማረጋገጫ ሰጡ

ባለፉት 20 ዓመታት ቅሬታ ሲያቀርቡ የቆዩ የአዲስ አበባ ከተማ ተፈናቃይ አርሶ አደሮች ኑሮ እንደሚለወጥና ከዚህ በኋላ አንድም የሚፈናቀል አርሶ አደር እንደማይኖር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ማረጋገጫ ሰጡ፡፡

ሙዚቃና ዳንኪራ ያጀበው የባንግላዴሽ ገጽታ

ባንግላዴሽ ሁሉን ያቀፈች አገር ናት ይሏታል፡፡ ከሃይማኖት አንፃር እስልምና፣ ቡድሂዝም፣ ሂንዱዝምና ክርስትና በአንድነት የሚኖሩበት በርካታ ነገዶችና ጎሳዎችንም በጉያዋ ያቀፈች ናት፡፡ ከተለያዩ ነገዶቿና ሃይማኖቶቿ ጋር ተያይዘው የሚፈልቁ ባህሎች ትውፊቶችና ልማዶችም ባለፀጋ ናት፡፡

አነጋጋሪው ጉዲፈቻ

ከሰውነት ተራ ያወጣት ሕመሟ ደጋግሞ ሲደቁሳት ቆይቷል፡፡ አንዴ በወጉ እንዳትራመድ እግሯን ሲሸመቅቅ፣ ሲለው ደግሞ ውስጥ አፏን እያቆሰለው እንዳትናገር እንዳትጋገር ሲያደርጋት አትደናገጥም፡፡