Skip to main content
x

አዲስ አበባን የፈተኗት አደገኛ የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች

የፍሳሽ ማስተላለፊያ ቱቦው እንደ ውኃ ጉድጓድ ክፍቱን ቀርቷል፡፡ በውስጡ እንደ የውኃ ኮዳ፣ ፌስታል የመሳሰሉ ቅራቅንቦዎች ሞልተውበታል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎችና አንዳንድ መንገደኞች እንደ መፀዳጃ የሚጠቀሙት ቱቦው የተገኘውን ነገር የሚወረውሩበት ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ከሆነ ቆይቷል፡፡ ፍሳሽ የማስተላለፍ ሚናውን መጫወትም የተሳነው ይመስላል፡፡

ከሦስት ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች የውኃና የንጽሕና ችግሮችን እየተጋፈጡ ነው

በኢትዮጵያ ከ3.3 ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የሆነ የንጹሕ መጠጥ ውኃና የመፀዳጃ ቤት ዕጦት ገጥሟቸዋል፡፡ አጋጣሚው ለውኃ ወለድና ለተለያዩ የሆድ ትላትል በሽታዎች እየዳረጋቸው እንደሚገኝ፣ የክትባት እጥረትና የመጠለያ ዕጦት፣ እንዲሁም የሰው ኃይል እጥረትና የደኅንነት ሥጋቶች ችግሩን ውስብስብ እንዳደረጉት የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር በየነ ሞገስ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ ሕፃናት ቅድመ መደበኛ ትምህርትን አለማግኘታቸው ዩኒሴፍ አስታወቀ

ዓለም አቀፍ የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በሚያዝያ መባቻ ይፋ ባደረገው ዓለም አቀፍ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ሪፖርት ላይ፣ በኢትዮጵያ ካሉ ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ከደረሱ ሕፃናት ከግማሽ በላዩ ዕድሉን አለማግኘታቸውን አስታውቋል፡፡

የነዳጅ አቅርቦትና ሥርጭትን የሚቆጣጠር ባለሥልጣን ሊቋቋም ነው

የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ሥርጭትን የሚቆጣጠር ባለሥልጣን ሊቋቋም ነው። የነዳጅና ነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ሥርጭት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን የሚል ስያሜ የሚኖረውን ይኼንን ተቋም የሚያቋቋም ረቂቅ አዋጅ ተሰናድቶ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ሚያዚያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀርቧል።

በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ተለዋዋጭ የአየር ፀባይ እንደሚኖር ተገለጸ

በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ሊኖር የሚችለውን ተለዋዋጭ የአየር ፀባይ ግምት ውስጥ በማስገባት ኅብረተሰቡ በዚህ ወቅት የግብርና፣ ሌሎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥራዎችን ከባለሙያዎች ጋር በመመካከር በአግባቡ እንዲያከናውን፣ የኢትዮጵያ ሚቲኦሮሎጂ ኤጀንሲ ማሳሰቢያ ሰጠ፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ለተጠለሉ ተፈናቃዮች ቤቶቻቸው ሊሠሩላቸው ነው

በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተጠለሉ ተፈናቃዮችን ቤቶች ለመሥራት፣ የክልሉ መንግሥት 155 ሺሕ ቆርቆሮዎችን ገዝቶ ወደ ቀበሌዎች እያስገባ መሆኑ ታወቀ፡፡ በግጭቱ የተቃጠሉ ቤቶችን ለመገንባት ራሱን የቻለ የመሐንዲሶች ቡድንም መቋቋሙን የተናገሩት የዞኑ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መንበሩ አውደው፣ መንግሥት ቤታቸው ለተቃጠለባቸው ተፈናቃዮች የቆርቆሮና የሚስማር እንዲሁም የአናጢ ወጪ እንደሚሸፍን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ቁመት የፈተናቸው

መንገድ ላይ ስትንቀሳቀስ የሚያዩዋት እንደ እንግዳ ፍጥረት ትክ ብለው ነው፡፡ ዓይኗ የተለየ ኃይል እንዳለው ሁሉ እንዳታያቸው የሚጠነቀቁም አሉ፡፡ እንደ ትንግርት ከሚመለከቷት አዋቂዎች በተቃራኒው ሕፃናት ደግሞ ይወዷታል፡፡ በተረት ላይ የሚያውቋትን ገፀ ባህሪ በአካል ያገኙ እስኪመስላቸው ሲያገኟት ይፍነከነካሉ፡፡

የተመጣጠነ ምግብ የያዘው ስፓይሩሊና በአገር ውስጥ ሊመረት ነው

በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት የተጎዱ ሕፃናትና ነፍሰ ጡሮች፣ እንዲሁም በሕመም ምክንያት በሽታ የመከላከል አቅማቸው የደከመውን ይታደጋል ከተባለው ስፓይሩሊና (ሰማያዊ ውኃ አቅላሚ አልጌ) የሚዘጋጅ ምግብ በአገር ውስጥ መመረት ሊጀምር ነው፡፡