Skip to main content
x

በአዲስ አበባ ዘላቂ ሥራ እየፈጠሩ የመሄድ ችግር መኖሩ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ያለውን የዜጎች ድህነትና ሥራ አጥነት ለመቅረፍ በየደረጃው የሚፈጠሩ የልማት ሥራዎች፣ ዘላቂ የሥራ ዕድል እየፈጠሩ የመሄድ ችግር እንዳለባቸው የከተማዋ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የጎዳና ተዳዳሪዎች መፃኢ ዕድል

በብሔራዊ፣ በስታዲየም፣ በፒያሳ፣ በኢትዮጵያ ሆቴል፣ በለገሃርና በተለይ የትራፊክ መብራቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ታዳጊ ሕፃናትና ወጣቶች አንዳንዴ ልጅ ያዘሉም ጭምር በአውራ ጎዳናው የሚያልፈውን መኪና እየተከተሉ የሚበላ አሊያም፣ የውኃ፣ ፕላስቲክ ስጡን የሚሉ ጎዳና ተዳዳሪዎች የአዲስ አበባ መገለጫ ከሆኑ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

የትምህርት ማስረጃና የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ወደ ዲጂታል ሊቀየር ነው

​​​​​​​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚታየውን ሐሰተኛ ማስረጃና ማጭበርበር ለመግታት፣ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርተፍኬት፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ፣ የልደትና ሞት ሰርተፍኬት እንዲሁም የጋብቻና ፍቺ ሰርተፍኬቶችን በዲጂታል ሊቀይር መሆኑን አስታውቋል፡፡

የተቀየሩ ታሪኮች

አምቦ ጉደር አካባቢ ከአምስት ዓመት በፊት የተስተዋለው ክስተት ለጉዳዩ ባለቤቶችም ሆነ ለጎረቤቶች አስደንጋጭ ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው አይተውት የማያውቁት ነገር በእነ አቶ ባትሪ ቶላ ቤት ታየ፡፡ እናት አባትና ጎረቤቶች ሁሉ በሆነው ነገር ግራ ተጋቡ፡፡

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ጋር እየተወዛገቡ ነው

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከጥር 12 እስከ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. ሁሉም የመደበኛ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው እንዲወጡ መወሰኑን ተከትሎ፣ ተማሪዎቹና የዪኒቨርሲቲው አስተዳደር እየተወዛገቡ ነው። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ለሚ ጉታ (ዶ/ር) የተላለፈው ውሳኔ ትክክል ነው ሲሉ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ያልተጠቀመችበት የዱር ስጦታ

ኢትዮጵያ ባላት መልክዓ ምድራዊና የመሬት አቀማመጥ እንዲሁም የሥነ ምድርና የአየር ንብረት ብዙኃነት የተነሳ የበርካታ ብርቅዬ የዱር እንስሳት ዝርያዎች ባለቤት እንድትሆን ተፈጥሮ አድሏታል፡፡ የቀደምት ሥልጣኔ፣ በአያሌ ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊና ባህላዊ ቅርሶቿ ተለይታ የምትታወቅ እንደመሆኗ መጠን በዓለም ላይ ለቱሪዝም ሀብት አለኝታነታቸው በቀዳሚነት ደረጃ ከሚፈረጁ አገሮች ተርታ የመመደብ ብቃት አላት፡፡

የቀድሞ ሠራዊት አባላት ጡረታቸው እንዲከበርና ሕክምና እንዲያገኙ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አሳሰበ

የቀድሞ ጦር ሠራዊት አባላት የጡረታ ጉዳይ ሲስተናገድበት የቆየው፣ እስካሁን በሥራ ላይ ያለውና ሚያዝያ 10 ቀን 1984 ዓ.ም. በሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የወጣው ልዩ መመርያ ተፈጻሚነት እንዲቆም፣ የቀድሞ ጦር ሠራዊት አባላትን የጡረታ ጉዳይ የሚመለከት ልዩ ሕግ እንዲወጣ በአዋጅ ቁጥር 714/2003 ላይ የአሠራር ማሻሻያ ተደርጎ ዘለቄታ የጡረታ አበል እንዲከበርላቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አሳሰበ፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድኃኒቶችና የሕክምና መሣሪያዎች ግዥ በመፈጸም ላይ ነኝ አለ

በአገሪቱ የሚስተዋለውን የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች እጥረት በተወሰነ ደረጃ ለመቅረፍ፣ 6.4 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ግዥ በመፈጸም ሒደት ላይ መሆኑን የጤና ሚኒስትሩ አሚር አማን (ዶ/ር) ገለጹ።

የመሸታ ወጎች

በጠዋቱ ደጋግሞ ወደ አፉ የላከው መለኪያ ሥራውን ጀምሯል፡፡ ያለበትን የሚያውቅ አይመስልም፡፡ በሩ ባደፈ መጋረጃ የተጋረደበት ደጃፍ ላይ ጋደም እንደማለት ብሎ ተቀምጧል፡፡ ረፍዱ ላይ የወጣው ከረር ያለ ፀሐይ ልብ ልቡን ይለዋል፡፡ ሰካራሙ ግን እንኳንስ ቦታ ቀይሮ ጥላ ሥር መቀመጥ እስከሆዱ የተከፈተውን የሸሚዞቹን ቁልፎች እንኳ አስተካክሎ መቆለፍ አልቻለም፡፡