Skip to main content
x

የውኃ እጥረት የአዲስ አበባን አረንጓዴ የልማት ሥራዎች እያደናቀፈ ነው ተባለ

በአዲስ አበባ ውበትና አረንጓዴ ልማት ሥራዎች ላይ የውኃ እጥረት ተፅዕኖ እየፈጠረ እንዲሁም የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት ያለመዳበር፣ የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶች እጥረት፣ ሕገወጥ የእንስሳት ዝውውርና ንግድም የከተማዋን ፅዳትና ውበት እየተፈታተኑ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ሲያኮበኩብ አደጋ በደረሰበት የኢትዮጵያ አውሮፕላን ላይ ጋና የቅድመ ምርመራ ሪፖርት ይፋ አደረገች

ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ሪፖርቱን እገመግማለሁ ብሏል በጋና ኮቶካ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ካረፈ በኋላ ሲንደረደር ባጋጠመው መጥፎ የአየር ፀባይ ምክንያት መስመሩን ስቶ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በሚመለከት፣ ጋና የቅደመ ምርመራ ሪፖርት ይፋ አደረገች፡፡

የጀግኖች አርበኞች ማኅበር የግራዚያኒ ሐውልት እንዲፈርስ ዳግመኛ ጥሪ አቀረበ

ፋሺስት ኢጣሊያ ከ78 ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ባደረሰው ጅምላ ጭፍጨፋ ዋና ተዋናይ ለነበረው ማርሻል ሮዶልፍ ግራዚያኒ ከሮም ወጣ ባለች ኤሬል መንደር የተሠራለት ሐውልት እንዲፈርስ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ዳግመኛ ጥሪ አቀረበ፡፡

የተሰው ሰማዕታት መታሰቢያ አፅም ከተለያዩ ቦታዎች ተለቅሞ በክብር እንዲያርፍ ተደረገ

በሕወሓት የ17 ዓመታት የትጥቅ ትግል የተሰው ከ60 ሺሕ በላይ ታጋይ ሰማዕታትን ለማስታወስ፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰበሰበ የሰማዕታት አፅም የካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚጠናቀቀው 40ኛ ዓመት ክብረ በዓል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ሁሉም የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት በተገኙበት፣ በመቐለ የሰማዕታት ሐውልት ሥር በተዘጋጀ ሥፍራ በክብር እንዲያርፍ ተደረገ፡፡

በከተማ ባቡር መስመር ላይ እየደረሰ ያለውን አደጋ ለመከላከል የሚያስችል ረቂቅ ሕግ ተዘጋጀ

ሰሞኑን ሁለት ተሽከርካሪዎች በመስመሩ ላይ ጉዳት አድርሰዋል በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ በሚገኘው የቀላል ባቡር ፕሮጀክት ላይ እየደረሰ ያለውን አደጋ ለመከላከል የሚያስችል ረቂቅ ሕግ መዘጋጀቱ ተጠቆመ፡፡