Skip to main content
x

የዓድዋ መንገደኞች

‹‹ያልሠለጠነ፣ ኋላቀር፣ ጨካኝ፣ ሃይማኖት የሌለው›› ተደርጎ ይታሰብ የነበረውን ጥቁር ሕዝብ ለመውረር የጣልያን ጄኔራሎች በዘመኑ የነበሩ ልዩ ልዩ የጦር መሣሪያዎችን ወደ አፍሪካ ቀንድ አጋዙ፡፡ ቀሪውን የአፍሪካ ክፍል ቅኝ ግዛታቸው አድርገው የነበሩ ምዕራባውያን ኢትዮጵያን የጣልያን ድርሻ ብለው ትተዋል፡፡

የተማሪዎች ምገባው ብርሃንና ጥላ

አዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በበጎ አድራጎት ድርጅቶች የተጀመረው የችግረኛ ተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ዛሬ ላይ በአስተዳደሩ ቦታ ተሰጥቶት በርካታ ተማሪዎች በመንግሥት በጀት የትምህርት ቤት ምገባ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ሆኖም ይህን መጠቀም ያልቻሉ አሉ፡፡

ስድስት የጨረር ሕክምና ማሽኖች ገቡ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የጨረር ሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ ስድስት ማሽኖችን አስገባ፡፡ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ የተገዙት ለካንሰር ሕክምና የሚውሉ ማሽኖች ለጥቁር አንበሳ፣ ለጅማ፣ ለሐሮማያ፣ ለአይደር፣ ለሐዋሳና ለጎንደር ሪፈራል ሆስፒታሎች መሠራጨታቸውም ታውቋል፡፡

የሕክምናው ውጋጅ

ከየመኖሪያ ቤቱና ከየተቋማቱ ተጠርጎ የሚወጣ ቆሻሻ ኑሮ ፊቷን ላዞረችባቸው የቆሼ ቃራሚዎች የህልውናቸው መሠረት ነው፡፡ የምግብ ትርፍራፊ፣ የውኃ ኮዳ፣ ሞዴስ፣ ፋሻ፣ ቤት ያፈራው ነገር ሁሉ በሚከማችበት የቆሻሻ ክምር ፌስታላቸውን አንጠልጥለው የሚርመሰመሱ ምስኪኖች ብዙ ናቸው፡፡

የትምህርቱን ዘርፍ የፈተነው የሰላም ዕጦት

በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት የዩኒቨርሰቲ ፕሮግራም አራት ዓመት እንዲሆን ይጠበቃል፡፡ ይህም ተቀባይነትን ካገኘ የመጀመርያ ዓመት ተማሪዎች በቀጥታ ወደ ሙያቸው የሚገቡ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያዊነትን ሊላበሱ የሚችሉባቸውን ኮርሶች እንዲማሩ ለማድረግ ታቅዷል፡፡

በአገር አቀፍ የውኃ ተቋማት ቆጠራ አራት ሺሕ ሰዎች ይሳተፋሉ

በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ከአራት ሺሕ በላይ ሰዎች የሚሳተፉበት አገር አቀፍ የውኃ አቅርቦት፣ ሳኒቴሽንና ኃይጂን አጠባበቅ ተቋማት ቆጠራ ሊካሄድ ነው፡፡ ቆጠራው በዋናነት በገጠርና በከተማ የውኃ ተቋማት መሠረተ ልማቶችን ከውኃ መገኛ ቦታ እስከ ማከፋፈያ ቦኖና የቤት ለቤት መስመሮችን በማካተት የሚከናወን ሲሆን፣ በዋናነት በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የመጠጥ ውኃ አቅርቦትና ሥርጭት፣ እንዲሁም የውኃ ተቋማትን ጥራት ለማወቅ ይረዳል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ በሠራተኞች የደመወዝ መነሻ ላይ ተስማሙ

ከኢትዮጵያ በቤት ሠራተኝነት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ የሚሄዱ ዜጎች መነሻ ወርኃዊ ደመወዝ 1,000 ሪያል እንዲሆን ስምምነት ላይ መደረሱ ታወቀ፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ ይከፈል ከነበረው የተሻሻለ ቢሆንም፣ አሁንም ከጎረቤት አገሮች ከኬንያና ከኡጋንዳ የሚሄዱ ዜጎች ጋር ሊመጣጠን አለመቻሉን አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡

ኑሮ ከተባለ…

በአጭር የተከረከሙት ፀጉራቸው ብዙም ሽበት አይታይበትም፡፡ ጎስቋሏ ፊታቸው ግን እርጅና የተጫጫናቸው አስመስሏቸዋል፡፡ ከወለሉ የመስኮት ያህል ከፍታ ያለውን በር እንደተደገፉ ውጭ ውጭውን ያያሉ፡፡ ዕይታው የደከመው ዓይናቸው ግን ወዳጆቻቸውን እንኳን አይለይም፡፡ በስማቸው እየጠሯቸው ለሰላምታ እጃቸውን ለዘረጉላቸው ሰዎች አፀፋውን ቢመልሱም ማን መሆናቸውን አላወቁም፡፡

ለኩላሊት ሕሙማን የገና ሥጦታ

የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ደም ግፊትና ስኳር ሕመም ቢያጋጥማቸውም ትኩረት ሰጥተው አለመታከማቸው ለኩላሊታቸው ከጥቅም ውጪ መሆን ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በወቅቱ ባይዘናጉ ኖሮም ‹‹ዝብርቅርቅ ያለ ሕይወት›› ለሚሉት ኑሮ ባልተዳረጉም እንደነበር ይገምታሉ፡፡