Skip to main content
x

ዳያስፖራው በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ሊሳተፍባቸው የሚችሉ አማራጮች ቀረቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለዳያስፖራው ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበርና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በጋራ ባዘጋጁት አገር አቀፍ የዳያስፖራ የውይይት መድረክ፣ ዳያስፖራው በተለያዩ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፎች እንዲሰማራ አማራጮች ቀረቡ፡፡

ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስጎብኚዎችን ይቅርታ የጠየቀበት መድረክ

አባጣ ጎርባጣ ለበዛበት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ዘርፍ መፍትሔ እንዲሆን በአዋጅ የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት በአሁኑ ስያሜው ‹‹ቱሪዝም ኢትዮጵያ›› በመስኩ ሊያመጣ ይችላል ተብሎ የተጠበቀውን ለውጥ ማምጣት ቀርቶ ባለጉዳዮችን እንኳ በአግባቡ ማስተናገድ ያልቻለ ድርጅት ነው የሚሉት ግን ጥቂት አይደሉም፡፡

 የ48 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሳይጀመር ግማሽ ዓመት ተጠናቀቀ

በተያዘው የበጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ 48 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንደሚጀመር ቢታቀድም፣ ግንባታው ሳይጀመር የበጀት ዓመቱ የመጀመርያው ስድስት ወራት ተጠናቀቁ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶቹን ግንባታ ለማካሄድ አቅዶ የነበረው በቦሌ ክፍለ ከተማ፣ በቦሌ አራብሳ፣ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፣ በኮዬ ፊጬ አካባቢዎች በሚገኙ ስምንት ሳይቶች ነበር፡፡

በተማሩበት የመሥራት ፈተና

ከጠዋቱ አራት ሰዓት አካባቢ አራት ኪሎ ከሚገኘው ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ሰሌዳ ዙርያ በርካታ ወጣቶች ዓይናቸውን ያማትራሉ፡፡ የተወሰኑት ደግሞ ክፍት የሥራ ቦታ የያዙ የጋዜጣ ክፍሎችን መሬት አንጥፈው የሚስማማቸውን ይፈልጋሉ፡፡ ከእነዚህ አንዱ የ23 ዓመቱ ናሆም ኃይለ ሥላሴ ነበር፡፡

የኩላሊት ሕሙማን የመንገድ ላይ ልመናን ለማስቆም ጥሪ ቀረበ

የኩላሊት ሕመምተኛ መሆናቸውን በመግለጽ በመኪና ላይ ወይም በጎዳና በመሆንና በድምፅ ማጉያ በመጠቀም፣ የገንዘብ ዕርዳታ የሚጠይቁ ሕሙማንን ከልመና አውጥቶ ለማሳከም ‹‹ከራስ ቆርሶ ለራስ መስጠት›› በሚል መሪ ቃል በጎ ፈቃደኞች ገንዘብ መለገስ የሚችሉበት አሠራር መዘርጋቱን የኩላሊት ሕመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት አስታወቀ፡፡

የሕገወጥ ሰዎች ዝውውር የሽውውድ ዓለም

ለሁለት አሠርት ዓመታት ያህል የዘለቀው የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት መፈታት የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ትኩረት ወደ አፍሪካ ቀንድ የሳበ ትልቅ ክስተት ነበር፡፡ የምስራቹ ዕውን ከመሆኑ በፊት በሁለቱ አገሮች ሰላም እንዲፈጠር ያላቸውን ምኞት ድምፃውያን በሙዚቃ አዚመዋል፣ ገጣሚያን ስንኝ ቋጥረዋል፣ በቀጣናው ላይ የፖለቲካ ጥቅም ያላቸውም በአገሮቹ መካከል ሰላም እንዲሰፍን ሞግተዋል፡፡

የማሠልጠኛ ተቋማት እጥረት በውጭ አገር ሥራ ስምሪት ላይ እንቅፋት ፈጥሯል

ለሥራ ወደ ዓረብ አገሮች የሚሄዱ ዜጎችን የሚያሠለጥኑ ተቋማት ቁጥር ማነስ በውጭ አገር ስምሪት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ ነው ተባለ፡፡ በአገሪቱ ይህንን አገልግሎት እንዲሰጡ 68 የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት ተለይተዋል፡፡

ሚሊዮኖች ሜዳ ላይ የሚፀዳዱባት ምድር

ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፈው የቆሙት ደሳሳ ጎጆዎች የረባ ግድግዳ የላቸውም፡፡ አብዛኞቹም ባረጀ ቆርቆሮ የተሠሩ ሲሆን፣ በክረምት ወራት በላይና በታች ዝናብና ጎርፍ የሚያስገቡ ሰቆቃ የበዛባቸው ናቸው፡፡ የበጋው ሀሩር ሙቀቱ መድረሻ ሲያሳጣቸው፣ በክረምት ደግሞ ቆፈኑ ግራ ያጋባቸዋል፡፡

አሥር ባህላዊ መድኃኒቶች ተመርተው የመጀመርያውን ፍተሻ አለፉ

ለሰውና ለእንስሳት የሚያገለግሉ አሥር የባህላዊ ሕክምና መድኃኒቶች ተመርተውና የመጀመርያውን የላብራቶሪ ፍተሻ ማለፋቸውንና ለቀጣይ የሙከራ ሽግግር መዘጋጀታቸውን የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቁ፡፡