Skip to main content
x

የለገጣፎ ተፈናቃዮች መውደቂያ አጥተናል እያሉ ነው

የለገጣፎ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የመጠለያ ችግር እንዳጋጠማቸው ገለጹ፡፡ በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ከማስተር ፕላን ውጪ ተገንብተዋል ተብለው በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ከፈረሱ በኋላ፣ ተፈናቃዮች መውደቂያ አጥተናል እያሉ ነው፡፡ መኖርያ ቤታቸው የፈረሰባቸው አባወራዎች በየዘመድና በቤተ እምነቶች ተጠልለው የሚገኙ መሆናቸውን፣ ሜዳ ላይ ድንኳን ጥለው እንደሚኖሩም ተናግረዋል፡፡

ከ200 በላይ በሚሆኑ አሠሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ ዕርምጃ ተወሰደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ሕገወጥ ድርጊት ሲፈጸሙ ተደርሶባቸዋል ባላቸው 239 አሠሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ የዕገዳና የእሸጋ ዕርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡  

ለአፋር ክልል 24 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የሕክምና መሣሪያዎች ተሰጡ

አምሪፍ ሔልዝ ኢን አፍሪካ የተባለ ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ በአፋር ክልል ለማኅበረሰብ ጤና ሠራተኞችና ለአዋላጅ ነርሶች አገልግሎት የሚውሉና 24 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የሕክምና መሣሪያዎች ለአፋር ክልል ጤና ቢሮ ባለፈው ሳምንት በዕርዳታ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ተመዝጋቢዎች መቆጠብ ያለባቸው የገንዘብ መጠን ይፋ ሆነ

የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ በሚወጣባቸው 18,576 የ40/60 ባለ አንድ፣ ባለ ሁለትና ባለ ሦስት መኝታ ቤት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ የሚካተቱት ተመዝጋቢዎች፣ እስካሁን መቆጠብ ያለባቸው 40 በመቶ የገንዘብ መጠን ይፋ ሆኗል፡፡

ከ8.3 ሚሊዮን በላይ ወገኖች አስቸኳይ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተመድ አስታወቀ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ማክሰኞ የካቲት 26 ቀን 2011 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ቅድመ ሪፖርት፣ በዚህ ዓመት ከ8.3 ሚሊዮን በላይ ወገኖች አስቸኳይ የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል አለ፡፡

የአፍ መፍቻ ቋንቋ ሲዘከር

የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለዕርቅና ለሰላም ግንባታ፣ ለዘላቂ ልማት ዕገዛና ለመሠረተ ትምህርት ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ይገልጻል፡፡

የመምህራንና የትምህርት አመራር ኮሚሽን ሊቋቋም ነው

የመምህራንን መብት ለማስጠበቅም ሆነ በመማር ማስተማሩ ሥርዓት ላይ ያሉ ግድፈቶችን ነቅሶ በማውጣትና ለመንግሥት በማሳወቅ ረገድ የነበረውን የተንዛዛ ምልልስ ያስቀራል የተባለ የመምህራንና የትምህርት አመራር ኮሚሽን ሊቋቋም ነው፡፡

ዳያስፖራዎች ለቤተሰቦች የጤናና አደጋ ኢንሹራንስ የሚገቡበት አሠራር ይፋ ተደረገ

በውጭ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአገር ቤት ለሚኖሩ ቤተሰቦቻቸው የጤናና የአደጋ መድን ሽፋን የሚሰጥ አዲስ የኢንሹራንስ አገልግሎት መጀመሩን ፀሐይ ኢንሹራንስ አስታወቀ፡፡

የጤና ጣቢያዎች ጓዳ

ዕረፍት የነሳቸው ሕመም ምን መሆኑን ለማወቅ የሠገራ፣ የሽንትና የደም ናሙና የሰጡ ታማሚዎች የላቦራቶሪውን ክፍል ከበዋል፡፡ ‹‹ውጤት በጊዜ አላገኘንም›› በሚል የሚያጉረመርሙና የሚቁነጠነጡ ብዙ ናቸው፡፡ የላቦራቶሪው የማስተናገድ አቅም ከተገልጋዮች ቁጥር ጋር አልተስማምና ወረፋው አሰልቺ ነው፡፡

በተሽከርካሪ አደጋ የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ሠራተኞችን ጨምሮ አምስት ሰዎች ሞቱ

መረጃ ለመሰብሰብ ከደቡብ ክልል አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ ወደ ደቡብ ኦሞ ዞን ሲጓዝ የነበረ የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ተሽከርካሪ በደረሰበት አደጋ፣ የኤጀንሲው የሥራ ባልደረቦችን ጨምሮ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው ከሲኖትራክ ጋር በመጋጨቱ ነው፡፡