Skip to main content
x

ለዓይን ተስፋ

የ65 ዓመቱ አዛውንት ካጠገባቸው ከተቀመጡት ሦስት ሰዎች በተለየ ከመቀመጫቸው  ተነስተው ከነበሩበት የአውሮፕላን ክፍል ወደ ሌላኛው ይራመዳሉ፡፡ እጃቸውን አጣምረው መለስ ቀለስ እያሉ ተራቸው እስኪደርስ ይጠባበቃሉ፡፡

በቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ስም ዘመናዊ ትምህርት ቤት ሊገነባ ነው

በቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ስም፣ በቡታጅራ ከተማ በ129 ሚሊዮን ብር የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሊገነባ ነው፡፡ ትምህርት ቤቱ 95 በመቶ ለሚሆኑ ተማሪዎች በነፃ ትምህርት ሊሰጥ እንደሚችል፣ በአገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ የገቢ ማሰባሰቢያውን የሚያስተባብሩት አቶ ብሩክ ዳንኤል ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወጣቶችን ማነጋገር ጀመሩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከከተማው ወጣቶች ጋር መነጋገር ጀመሩ፡፡ ምክትል ከንቲባው ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ከቦሌና ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ጋር መነጋገራቸው ታውቋል፡፡ በሚቀጥሉት ሳምንታት ከተቀሩት ስምንት ክፍላተ ከተማ ወጣቶች ጋር እንደሚነጋገሩ፣ ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሸገር እስከ ታይም ስኴዌር

የተለያዩ አገሮች መሪዎችና ሌሎች ትልልቅ ባለሥልጣናት በሚታደሙበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓመታዊ ጉባዔ ላይ እንድሳተፍ የተጋበዝኩት ዝግጅቱ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ነው፡፡ ፕሮግራሙ የሚጀመረው መስከረም 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ሲሆን፣ ለቪዛ ቃለ መጠይቅ የተቀጠርኩት ግን ለመስከረም 24 ነበር፡፡ ለሥራ ጉዳይ ስለሆነ ቪዛው በአፋጣኝ እጄ መግባት ችሎ ነበር፡፡

የሕዝብ ቅሬታዎችን እንዲፈታ የተቋቋመው ጽሕፈት ቤት ደንብና መመርያ ሊሻሻል ነው

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትን ጭምር እያጥለቀለቀ የሚገኘውን የሕዝብ አቤቱታ በተገቢው መንገድ እንዲፈታ የተቋቋመው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገድ ጽሕፈት ቤትን የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ፣ ደንብና መመርያ የሚያሻሽል ኮሚቴ ተቋቋመ፡፡

የእሳት አደጋ በፒያሳ

ረቡዕ መስከረም 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ መሐሙድ ሙዚቃ ቤት በስተጀርባ፣ ከመኖሪያ ቤት የተነሳ እሳት ከፍተኛ አደጋ አስከትሏል፡፡  የአካባቢው ወጣቶችና የእሳት አደጋ ሠራተኞች በመተባበር ለ1፡30 ሰዓት ያህል የቆየውን እሳት ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ ለመቆጣጠር ተችሏል፡፡