Skip to main content
x

የዲቪ 2020 ምዝገባ ተጀመረ

የዲቪ 2020 ምዝገባ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 3 ቀን 2018 እንደሚጀምርና ህዳር 6 ቀን 2018 እንደሚጠናቀቅ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

በርካቶች በየዓመቱ ይህንን ዕድል በመጠቀም ወደ አሜሪካ የሚያቀኑ ቢሆንም፣ በቅርቡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባስታወቁት መሠረት በዓመት ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሰዎች ብዛት ከ30,000 እንዳይበልጥ ውሳኔ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል፡፡ ይህ ውሳኔ የሚፈጸም ከሆነም፣ በአሜሪካ ታሪክ በዓመት ወደ አገሪቱ የሚገቡ ዝቅተኛው የስደተኞች ቁጥር ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ አይነኬ የተባሉ ቦታዎች የሊዝ ውል እንዲቋረጥ ወሰነ

በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ሚድሮክን ጨምሮ በግል፣ በመንግሥትና በዲፕሎማቲክ ተቋማት ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን የሊዝ ውል በማቋረጥ ላለፉት አሥር ዓመታት ያልተደፈረ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

‹‹ጥቅም ላይ ባልዋሉ የመሬት ይዞታዎች ላይ የተጀመረው ዘመቻ ሁለተኛ ዙር በቅርቡ ይጀመራል›› ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ

በኢንቨስትመንትና በተለያዩ የልማት ሥራዎች ስም ተወስደው ለበርካታ ዓመታት ያለሙ የመሬት ይዞታዎችን ወደ ከተማ አስተዳደሩ የመሬት ባንክ የማስመለስ ዘመቻ ሁለተኛ ዙር በቅርቡ እንደሚጀመር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

በሕገወጥ መንገድ የተያዙ 500 ቤቶች በዕጣ ሊከፋፈሉ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ባደረገው ጥናት፣ በሕገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 500 ቤቶችን በማግኘቱ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች በዕጣ ሊያከፋፍል ነው፡፡ በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) አዲስ ካቢኔ ውስጥ በመካተት የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት፣ ሰናይት ዳምጤ (ኢንጂነር) እንደተናገሩት፣ ከከተማ እስከ ወረዳ በተዘረጋ ጥናትና ክትትል እስካሁን 500 የጋራ መኖሪያ ክፍት ቤቶች፣ በሕገወጥ መንገድ የተያዙና ውል የሌላው ቤቶች ተገኝተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ታግዶ የቆየው የመሬት መስተንግዶ ተጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋርጦ የነበረው የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት መስተንግዶ በይፋ ተጀመረ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ሥልጣን በተረከቡ ማግሥት፣ የመሬት ኦዲት እስኪካሄድ የመሬትና መሬት ነክ መስተንግዶ እንዳይሰጥ አግደው ነበር፡፡

አሲድ ያጠፋቸው ገፆች

ሐዘን ያጠላበት ፊቷን ወፈር ባለ ስካርቭ በከፊል ሸፍናዋለች፡፡ ከእንግዳ መቀበያው ክፍልም አልነበረችም፡፡ ከጓዳ ብቅ ያለችውም ተጠርታ ነው፡፡ በወላጆቿ ቤት እንግድነት የሚሰማት ይመስላል፡፡ በወጉ የማይዘረጉ እጆቿን ለሰላምታ ዘረጋችና ፈንጠር ብላ አንደኛው ሶፋ ላይ ተቀመጠች፡፡

የዓሹራ ክብረ በዓል

‹‹የሙሀረም ወር 10ኛ ቀን የሚከበርባት ዓሹራ ብዙ ትርጉም አላት፡፡ ሰማይና ምድር የተሆለቁት (የተፈጠሩት) በዓሹራ ቀን ነው፡፡ አደምና ሐዋ የተሆለቁት በዓሹራ ነው፡፡ ጥሩ ጥሩ ሥራ የሚሠራበት ፍርድም የሚደረግበት በዓሹራ ነው፡፡

ደም ባንክ የደም እጥረት አጋጥሞታል

ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ከፍተኛ የደም ዕጥረት እንዳጋጠመው አስታወቀ፡፡ እጥረቱ ያጋጠመው በባንኩ የነበረው ክምችት ከቡራዩ ዙሪያ ለተፈናቀሉና በደረሰባቸው የአካል ጉዳት ደም ለሚያስፈልጋቸው እንዲሠራጭ በመደረጉ እንደሆነ የደም ለጋሾች አገልግሎት ዘርፍ ዳይሬክተሩ ተመስገን አበጀ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ 400 ቦታዎች ተለዩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግንባታ ሳይካሄድባቸው ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ 400 ቦታዎች ለየ፡፡ በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የሚመራው ካቢኔ ዕርምጃ ለመውሰድ እንዲያመቸው በቅርቡ የውሳኔ ሐሳብ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ቴዲ አፍሮ ከቡራዩና አካባቢው ለተፈናቀሉ ሰዎች የአንድ ሚሊዮን ብር እርዳታ ሰጠ

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩና አካባቢው በተፈጸመ ጥቃት ሳቢያ ለተፈናቀሉ ሰዎች ሐሙስ መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ.ም. የአንድ ሚሊዮን ብር እርዳታ አደረገ፡፡