Skip to main content
x

በ40/60 የቤቶች ፕሮግራም መቶ በመቶ የቆጠቡ ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩን አዲስ አቋም ተቃወሙ

በ40/60 የቤቶች ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገነቡ ቤቶችን በቅድሚያ ለማግኘት ፕሮግራሙ ይፋ በተደረገበት ወቅት በተቀመጠው መሥፈርት መሠረት መቶ በመቶ ቁጠባ ፈጽመናል ያሉ ነዋሪዎች፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ቤቶቹን መቶ በመቶ የቆጠቡ ቅድሚያ የማግኘት መብት ሊኖራቸው አይገባም በማለት በያዘው አቋም ላይ ተቃውሞ አቀረቡ።

ሠራተኞችን ወደ ዓረብ አገሮች ለመላክ መንግሥታት ስምምነት ቢፈጽሙም አስፈጻሚው ግራ እያጋባቸው መሆኑን ኤጀንሲዎች ገለጹ

በተለያዩ የሥራ መስኮች ሠራተኞችን ወደ ዓረብ አገሮች ለመላክ በኢትዮጵያ መንግሥትና በአራት የዓረብ አገሮች መንግሥታት መካከል ስምምነት ተደርጎ በየፓርላማቸው የፀደቀ ቢሆንም፣ አስፈጻሚው የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ግራ እያጋባቸው መሆኑን የውጭ ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ገለጹ፡፡

ሥርዓተ ምግብ ላይ ያተኮረ ግብርና

ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ በግብርና እንደሚተዳደር በሚነገርላት ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና አሁንም ድረስ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ የአገሪቱ የጀርባ አጥንት ነው የሚባለው ግብርና ዜጎቿን እንኳ መመገብ አልቻለም፡፡

መሀንነት በሳይንስ መነፅር

እ.ኤ.አ. በ1990ዎቹ ከ11 ልጆች መካከል አንዱ የአምስት ዓመት ልደቱን ሳያከብር ይሞት ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በ2017 አምስት ዓመት ልደታቸውን ሳያከብሩ የሚሞቱ ልጆች ቁጥር ከፊተኛው ጋር ሲነፃፀር በእጅጉ ቀንሷል፡፡

በአዲስ አበባ ዘላቂ ሥራ እየፈጠሩ የመሄድ ችግር መኖሩ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ያለውን የዜጎች ድህነትና ሥራ አጥነት ለመቅረፍ በየደረጃው የሚፈጠሩ የልማት ሥራዎች፣ ዘላቂ የሥራ ዕድል እየፈጠሩ የመሄድ ችግር እንዳለባቸው የከተማዋ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የጎዳና ተዳዳሪዎች መፃኢ ዕድል

በብሔራዊ፣ በስታዲየም፣ በፒያሳ፣ በኢትዮጵያ ሆቴል፣ በለገሃርና በተለይ የትራፊክ መብራቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ታዳጊ ሕፃናትና ወጣቶች አንዳንዴ ልጅ ያዘሉም ጭምር በአውራ ጎዳናው የሚያልፈውን መኪና እየተከተሉ የሚበላ አሊያም፣ የውኃ፣ ፕላስቲክ ስጡን የሚሉ ጎዳና ተዳዳሪዎች የአዲስ አበባ መገለጫ ከሆኑ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

የትምህርት ማስረጃና የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ወደ ዲጂታል ሊቀየር ነው

​​​​​​​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚታየውን ሐሰተኛ ማስረጃና ማጭበርበር ለመግታት፣ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርተፍኬት፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ፣ የልደትና ሞት ሰርተፍኬት እንዲሁም የጋብቻና ፍቺ ሰርተፍኬቶችን በዲጂታል ሊቀይር መሆኑን አስታውቋል፡፡

የተቀየሩ ታሪኮች

አምቦ ጉደር አካባቢ ከአምስት ዓመት በፊት የተስተዋለው ክስተት ለጉዳዩ ባለቤቶችም ሆነ ለጎረቤቶች አስደንጋጭ ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው አይተውት የማያውቁት ነገር በእነ አቶ ባትሪ ቶላ ቤት ታየ፡፡ እናት አባትና ጎረቤቶች ሁሉ በሆነው ነገር ግራ ተጋቡ፡፡