Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜና

በርካታ የኢዜማ አመራሮች መልቀቂያ ማስገባታቸው ተነገረ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ ሦስት አመራሮች ለፓርቲው የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተነገረ፡፡ ፓርቲው ባለው ሁለት ዓይነት መዋቅር ማለትም በትይዩ ካቢኔና በሥራ አስፈጻሚ ውስጥ ሲሳተፉ የቆዩ የፓርቲው አመራሮች መልቀቂያውን ማስገባታቸው ታውቋል፡፡ መልቀቂያውን ካስገቡት መካከል ባንትይገኝ...

የንብ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ በብሔራዊ ባንክ ጣልቃ ገብነት ሊካሄድ ነው

በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት የግል ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው ንብ ባንክ፣ አጋጥሞታል በተባለ የእንቅስቃሴ መዳከም ምክንያት፣ የባንኩ የቦርድ አባላት ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጣልቃ በመግባት የባንኩን ባለአክሲዮኖች ለጠቅላላ ጉባዔ...

ብሔራዊ ባንክ በሕጋዊና በጥቁር ገበያ መካከል ያለውን የምንዛሪ ተመን ለማጥበብ ማቀዱ ተሰማ

 የኢንሹራንስ ዘርፍን የሚቆጣጠር ኤጀንሲ ሊቋቋም ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሕጋዊው የውጭ ምንዛሪ ተመንና በተለምዶ ጥቁር ገበያ በሚባለው የምንዛሪ ተመን መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት በከፍተኛ ደረጃ ለማጥበብ ማቀዱ ተሰማ። ብሔራዊ ባንክ በሕጋዊውና በጥቁር ገበያው መካከል ያለውን ሰፊ...

ከ25 በመቶ በላይ ሠራተኞቹ የለቀቁበት ፀረ ሙስና ኮሚሽን መፍትሔ ይሰጠኝ አለ

‹‹ከ20 ዓመታት በላይ አገልግዬ ደመወዜ አንድ ኩንታል ጤፍ መግዛት አይችልም›› የኮሚሽኑ ከፍተኛ ኃላፊ በኑሮ ውድነት ምክንያት የሚከፈላቸው ደመወዝ አላኖር ያላቸው ከ25 መቶ በላይ ሠራተኞቹ በአንድ ዓመት ውስጥ ሥራቸውን መልቀቃቸውን ጠቅሶ መፍትሔ ይሰጠኝ ሲል፣ የሥነ ምግባርና ፀረ...

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የወረርሽኝ በሽታዎች ከመንግሥት አቅም በላይ ሆነዋል ተባለ

በቅርቡ ምሥረታውን ባካሄደው አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ለተከሰቱት የወባ፣ የኩፍኝና የአባላዘር ወረርሽኞች፣ መንግሥት ከአቅሙ በላይ ሆኖበት ምላሽ መስጠት ባለመቻሉ በተለይ የሕፃናት ሞት አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ፡፡ በመድኃኒትና በሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች እጥረት የጤና ተቋማት...

ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለተጠራቀመበት ዕዳ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲሰጥ ተጠየቀ

ኢትዮ ጂቡቲን ለሚያስተዳድረው አካል በዓመት 60 ሚሊዮን ዶላር እየተከፈለ መሆኑ ተገልጿል የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የተጠራቀመበት ዕዳ በአፋጣኝ ፖለቲካዊ መፍትሔ ካላገኘ፣ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የዕዳ መጠኑ ወደ 250 ቢሊዮን ብር እንደሚያሻቅብ፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ...
- Advertisement -

 የኤችአይቪ/ኤድስ የሥርጭት ምጣኔ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

ወጣቶችን ጨምሮ ለበሽታው ተጋላጭ ተብለው በተለዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ እየታየ ያለው የኤችአይቪ/ኤድስ የሥርጭት ምጣኔ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነገረ፡፡ የኤችአይቪ/ኤድስ ሥርጭት በቀን ሠራተኞች፣ በሴተኛ አዳሪዎች፣ በረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፣ በአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚዎች ላይ ያለው የሥርጭት ምጣኔ...

ለማዳበሪያ ግዥ 930 ሚሊዮን ዶላር መፈቀዱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

ለ2016/17 ዓ.ም. የምርት ዘመን የማዳበሪያ ግዥ 930 ሚሊዮን ዶላር መፈቀዱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ለማዳበሪያ ግዥ የተፈቀደው 930 ሚሊዮን ዶላር (71.4 ቢሊዮን ብር) በመሆኑ በዕቅድ ከተያዘው 23.3 ሚሊዮን ኩንታል ውስጥ 19.4 ሚሊዮን ኩንታል ብቻ የመግዛት አቅም...

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በጥናት በተደገፈ የሰላም ግንባታ ሥራ ላይ እንዲሰማሩ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በጥናት ላይ የተደገፈ ስትራቴጂ በመቅረጽ የሰላም ሥራ ግንባታ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ። የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግሥት አካላት፣ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላትና ሌሎችም በተገኙበት ‹‹የሲቪል ማኅበረሰብ...

ሰሊጥ ላኪዎች የሽያጭ ውል ማረጋገጫ ሳይዙ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲገበያዩ ተፈቀደ

ካለፈው ዓመት ታኅሳስ 9 ቀን 2015 ዓም. ጀምሮ ለሰሊጥ ላኪዎች የኤክስፖርት  የሽያጭ ውል ማረጋገጫ የማግኘት ግዴታ የነበረው አሠራር ላልተወሰነ ጊዜ መቆሙን፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አስታወቁ፡፡ ለዚህ አሠራር መነሻ የሆነው በወቅቱ የምርት...
- Advertisement -