Monday, November 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  Category Template – Kids Store - ቢዝነስ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
  - Advertisement -

  ዜና

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን ጉዳት ደረሰበት

  ባለፈው ቅዳሜ ጠዋት ከቶጐ ዋና ከተማ ሎሜ ተነስቶ ወደ ጋና አክራ ያቀናው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን ማረፊያ መስመሩን ስቶ ጉዳት ደረሰበት፡፡

  በመንግሥትና በሲቪል ማኅበራት ግንኙነት ውጥረት እንዲረግብ ተጠየቀ

  በመንግሥትና በሲቪል ማኅበራት ግንኙነት የሚስተዋለው ውጥረት እንዲረግብ ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ፎርም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) ‹‹በድህነት ቅነሳ ጥረቶች የሲቪል ማኅበራት ድርሻ›› በሚል ርዕስ አዘጋጅቶት በነበረው የውይይት መድረክ ላይ ተገለጸ፡፡

  ንግድ ባንክ ከ5.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ላስገኙለት ዕውቅና ሰጠ

  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2006 በጀት ዓመት ከዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት ከ5.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

  ሰማያዊ ፓርቲ ይቅርታ እንደማይጠይቅ አስታወቀ

  ሰማያዊ ፓርቲ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤትን እስከ ጥር 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ በጽሑፍ ይቅርታ ይጠይቅ በማለት የተላለፈው ውሳኔ ከሕግ አግባብ ውጪ ስለሆነ ተቃውሞውን በመግለጽ ይቅርታ እንደማይጠይቅ አስታወቀ፡፡

  ንግድ ባንክ ለኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ስምንት ቢሊዮን ብር አበደረ

  ግዙፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባገኘው ዋስትና መሠረት ለአዲስ አበባ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ስምንት ቢሊዮን ብር አበደረ፡፡

  የፓሪሱን የሽብር ጥቃት እናወግዛለን!

  ባለፈው ሳምንት ረቡዕ በፈረንሣይ ዋና ከተማ ፓሪስ በሳምንታዊው የሻርሊ ኢብዶ ሳምንታዊ መጽሔት አዘጋጆች ላይ የተፈጸመውን የሽብር ጭፍጭፋ እናወግዛለን፡፡
  - Advertisement -Girl in a jacket

  የገቢዎችና ጉምሩክ የወንጀል ምርመራ ቡድን አስተባባሪ ታስረው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጠ

  የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የምሥራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ቡድን አስተባባሪ፣ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አላከበሩም በመባላቸው ለ24 ሰዓታት ታሰረው እንዲቀርቡ፣ ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

  የግል አየር መንገዶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻርተር ሥራ መግባቱ ሥጋት ፈጥሮብናል አሉ

  በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የግል አየር መንገዶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአነስተኛ አውሮፕላኖች የቻርተር በረራ አገልግሎት ለመጀመር ማቀዱ፣ ከፍተኛ ሥጋት እንደፈጠረባቸው አስታወቁ፡፡

  ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ያቋቋመችው የቴክኒክ ኮሚቴ ስምምነት ላይ መድረስ አልቻለም

  ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ያቋቋሙት የጋራ ቴክኒክ ኮሚቴ ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት በመምረጥ ሒደት ላይ መግባባት አለመቻሉ ተሰማ፡፡

  ዮርዳኖስ ሆቴል የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባለማክበሩ ተሽከርካሪው በሐራጅ እንዲሸጥ ታዘዘ

  በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንችስ አካባቢ የሚገኘው ዮርዳኖስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር (ዮርዳኖስ ሆቴል) ፍርድ ቤቶች እንዲከፍል የወሰኑበትን ክፍያ ሊፈጽም ባለመቻሉ፣ ተሽከርካሪው ተሸጦ ለፍርድ ባለመብት ከነወለዱ እንዲከፍል ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  Category Template – Kids Store - ቢዝነስ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር