Friday, March 31, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜና

በሽብርተኝነት የተከሰሱት የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ቅጣት ተወሰነባቸው

- በድጋሚ ፍርድ ቤት ደፍራችኋል በሚል የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶ ለቅጣት ተቀጠሩ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትሕ ጠምቶታልና እግዚአብሔር ፍትሕ ይስጠው›› አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል የነበሩ ‹‹ተራ ስድብ ተሳድባችኋልና ማዕከላዊ እንድትመረመሩ እናዛለን›› ፍርድ ቤት

ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የፈልጐ ማዳን ቡድን ሊያዋቅር ነው

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአውሮፕላንና የሔሊኮፕተር አደጋ በሚፈጠርበት ወቅት በፍጥነት አደጋው የተከሰተበትን ቦታ ለይቶ ለተጐጂዎች የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና ዕርዳታ በመስጠት፣ ወደ ሕክምና ተቋማት የሚያደርስ ብሔራዊ የፈልጐ ማዳን ቡድን እንደ አዲስ ለማቋቋም እንቅስቃሴ ጀመረ፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥትና ተቋማትን በመሰለል የተጠረጠሩ ክስ ተመሠረተባቸው

በኢትዮጵያ ውስጥ አባላትን በመመልመል መንግሥትንና ተቋማቱን እንዲሰልሉ፣ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትሕዴን) ወይም ዴሞክራሲያዊ ምንቅስቃስ ሕዝቢ ትግራይ (ዴምሕት) ብሎ በሚጠራው ቡድን የተመለመሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር ገቢ በመሰብሰብ ዝቅተኛ አፈጻጸም አሳየ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት 15.4 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ቢያቅድም፣ ማሳካት የቻለው 11.04 ቢሊዮን ብር ወይም የዕቅዱን 72 በመቶ ብቻ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

ኢትዮጵያና ቻይና የዲፕሎማቲክና የሰርቪስ ፓስፖርት ለያዙ ዜጎቻቸው ቪዛ ሊያስቀሩ ነው

ኢትዮጵያና ቻይና የዲፕሎማቲክና የሰርቪስ ፓስፖርት ለያዙ ዜጎቻቸው ያለ ቪዛ መግባትና መውጣት እንዲችሉ ሊፈቅዱ ነው፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ረቂቅ አዋጅ ከሕገ መንግሥቱ ጋር እንዲታረቅ የፓርላማ አባላት ጠየቁ

መጋቢት 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ረቂቅ አዋጅ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ቢኖረውም፣ ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ጋር የሚቃረኑ አንቀጾችን የያዘ በመሆኑ እንዲስተካከል የፓርላማ አባላት ጠየቁ፡፡
- Advertisement -Girl in a jacket

የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫ ሐሙስ ይካሄዳል

-  የምልዓተ ጉባዔው ጉዳይ ውዝግብ ይፈጥራል ተብሎ ተሰግቷል በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዘጠነኛ መደበኛ ጉባዔውና በጉባዔው ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎች የተሻሩበት የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣ መጋቢት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. አዳዲስ አመራሮቹን ይመርጣል፡፡ 

ፓርላማው የዋና ኦዲተሩን ሥልጣን አራዘመ

- የሁለተኛ ምክትል ዋና ኦዲተር ሹመትም ፀድቋል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመርያ የሹመት ዘመናቸውን ያገባደዱትን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዋና ኦዲተርን ሁለተኛ የሥራ ዘመን ሹመት አፀደቀ፡፡

የአዲስ አበባ የምርጫ ተፎካካሪዎች ተለዩ

በምርጫ ክልል 17 (ቦሌ) ከፍተኛ ትንቅንቅ ይጠበቃል ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ለመወዳደር፣ በአዲስ አበባ 23 የምርጫ ክልሎች የኢሕአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች ተለይተው ታወቁ፡፡

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው የተከሰሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ቅጣት ሊወሰንባቸው ነው

ተዘረፍን በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ተደረገ በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸውና በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት፣ የሰማያዊና የዓረና አመራሮች ችሎት በማወክ፣ በማንጓጠጥ፣ የችሎቱን ስም በማጥፋትና የችሎት ሒደትን በማስተጓጎል የቅጣት ውሳኔ ሊሰጥባቸው ነው፡፡
- Advertisement -