Skip to main content
x

የንግዱ ማኅበረሰብ ሕገወጥ ተግባራት መቆም እንዳለባቸው አሳሰበ

በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ ሕገወጥ ተግባራትን መንግሥት ማስቆም እንዳለበት የንግዱ ማኅበረሰብ ማሳሰቢያ አቀረበ፡፡ የንግዱ ማኅበረሰብ ያለ ሥጋት ሥራውን ማከናወን የሚችለው ሕገወጥ ተግባራት ሲቆሙ እንደሆነም ጥያቄ ቀርቧል፡፡

መንግሥት ኢትዮጵያ ጦሯን ከኤርትራ ድንበር አለማንሳቷን አስታወቀ

ኢትዮጵያ ጦሯን ከኤርትራ ድንበር እያነሳች ነው ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት ነው ሲል መንግሥት አስተባበለ፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር በተለይም በሽራሮ ግንባር የሚገኘው ጦሯን ኢትዮጵያ እያነሳች እንደሆነ፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው አውቶብሶችና ኦራል ወታደራዊ የጭነት ተሽከርካሪዎች ጦሩን ሲያጓጉዙ መታየታቸውን፣ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲሰራጭ ነበር፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል

ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር ጥረት ላይ ያለችው ኢትዮጵያ፣ የአምራች ኢንዱስትሪዋ አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአምራች ኢንዱስትሪውን የ2010 ዓ.ም. ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ነው፡፡ ሐሙስ ነሐሴ 10 ቀን 2010 ዓ.ም.

የአዲስ አበባ ከተማ ሹም ሽር ወደ ታችኛው መዋቅር ሊሸጋገር ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ የሚገኘው የአመራሮች ሹም ሽር፣ ከማዕከል ወደ ክፍላተ ከተሞችና ወረዳዎች ሊሸጋገር ነው፡፡ በዚህ ሳምንት በአሥሩም ክፍላተ ከተሞችና በ116 ወረዳዎች በዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚና በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊነቶች ላይ ሹም ሽር እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡