Skip to main content
x
የአሸናፊዎች አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ

የአሸናፊዎች አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ፕሪሚየር ሊጉን ጨምሮ በየደረጃ የሚገኙ ክለቦች የሚያደርጓቸው የሊግ ውድድሮች የተፎካካሪነት ደረጃና ውጤታቸው ከስፖርት ቤተሰቡ ፍላጎትና ስሜት ጋር መጣጣም እየቻለ አይደለም፡፡ አንጋፋው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በአገር ውስጥ የሚዘጋጁ ውድድሮች በአሸናፊነት በማጠናቀቅ ተስተካካይ የለውም፡፡ ይሁንና በአህጉራዊም ሆነ በዓለም አቀፍ ውድድሮች የቅዱስ ጊዮርጊስ ኃያልነት በእነዚህ መድረኮች ያን ያህል ሊጠቀስ የሚችል እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በውድድር ዓመቱ ጅማሮ ሁለት ዋንጫዎችን በማንሳት ጥንካሬውን እያስመሰከረ ይገኛል፡፡ የ2009 የውድድር ዓመት የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ በማንሳት አሁንም በኃያልነቱ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡ እሑድ ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም የዓምናው የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ አሸናፊ ወላይታ ድቻን ገጥሞ 2 ለ0 አሸንፎ ነው ዋንጫውን ያነሳው፡፡