Skip to main content
x
‹‹አክሱም ወደ አደገኛ ሁኔታ እየሄደ ነው፡፡ ልክ እንደ ስሜን ተራራ ብሔራዊ ፓርክ ለአደጋ የተጋለጠ ተብሎ ከፋይል እንዳይወጣ ያሠጋል፡፡››

‹‹አክሱም ወደ አደገኛ ሁኔታ እየሄደ ነው፡፡ ልክ እንደ ስሜን ተራራ ብሔራዊ ፓርክ ለአደጋ የተጋለጠ ተብሎ ከፋይል እንዳይወጣ ያሠጋል፡፡››

የኢትዮጵያ አርኪዮሎጂ ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዚዳንትና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአርኪዮሎጂ ረዳት ፕሮፌሰር ተክሌ ሐጎስ፣ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ሆኖ ከ37 ዓመት በፊት የተመዘገበው አክሱም ሐውልቶቹና መካነ ቅርሶቹ ለከፋ አደጋ መጋለጣቸውን በማመልከት ለሪፖርተር ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ ስሜን ብሔራዊ ፓርክ በተፈጠረበት ችግሮች ሰበብ ከዓለም ቅርስነት ወጥቶ በአደጋ መዝገብ ውስጥ ለ20 ዓመት በመቆየቱ ብዙ ዋጋ ማስከፈሉን ያስታወሱት አቶ ተክሌ የአክሱም ሁኔታ ከዚህ አይለይም ያሉት ዩኔስኮ ሁለት ጊዜ በተከታታይ በመምጣት ማስጠንቀቂያ መስጠቱን በማስታወስ ነው፡፡ ‹‹በዩኔስኮ ማሳሰቢያ መሠረት አንድም የተስተካከለ ነገር የለም፡፡ አሁንም በዚህ ከቀጠለ ወደ አደገኛ መዝገብ ብሎም ከዓለም ቅርስነት ሊሰረዝ ይችላል! የአክሱም ሐውልት እንደዘመመ ነው፤ ከ10 ዓመት በላይ በካቦ ታስሯል፡፡ በሐውልቱ ዙሪያ ያሉ ቅርሶችም ችግር ላይ ነው ያሉት፡፡ የሚመለከተው ባለቤት አጥቷል፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡