Skip to main content
x
ዖፈ ያሬድ

ዖፈ ያሬድ

ዖፈ ያሬድ ፈካ ያለ ቡና፣ ጥቁርና ነጭ ቀለም ያላቸው ለየት ያሉ ወፎች፡፡ ወንዶቹ በጣም ረዥም ነጭ ጅራት ጥቁር ጭንቅላት ሲኖራቸው፣ ሴቶቹ ደግሞ አጠር ያለ ጅራትና ፈካ ያለ ቡና ቀለም አላቸው፡፡ መንቆራቸው አጭር ሰማያዊ ሲሆን በጭንቅላታቸው ላይ ተለቅ ያለ ጉትዬ ይታያል፡፡ በዛፍም፣ እጅብ ያለ እሾካማ ቁጥቋጦና በግራርማ ቦታዎች ይገኛሉ፡፡ አልፎ አልፎ በከተማ የጓሮ አትክልት ውስጥም ይታያሉ፡፡ ፈጣንና ቀዥቃዣ ትንኝ አሳዳጅ ወፎች ናቸው፡፡

  • ከበደ ታደሰ ‹‹የኢትዮጵያ መካከለኛው ስምጥ ሸለቆ ወፎች የኪስ መጽሐፍ›› (2000)