Skip to main content
x

ቃል ከተግባር ይዛመድ

 በ2005 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተጠቃሚ ለማድረግ በመንግሥት ምዝገባ መካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡

በወቅቱ ለተመዝጋቢዎቹ የተገለጸው 40 በመቶ ገንዘብ ቁጠባ ሲያደርጉ፣ በመንግሥት በኩል ከባንክ 60 በመቶ ብድር ተመቻችቶላቸው ከአምስት ዓመት ባነሰ ጊዜው ውስጥ የቤቶቹ ግንባታ አልቆ ለነዋሪዎች ይተላለፋ ተብሎ በመነገሩ፤ የተሻለ ገቢ ያላቸው፣ ዳያስፖራዎች እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች ጭምር የቤት ችግራቸውን ለመወጣት ብዙ ተስፋ ጥለውበት ነበር፡፡ ለዓመታት በብዙ ተስፋ ሲጠበቅ የነበረው የቤት ፕሮግራም፣ ከአምስት ዓመት በኋላ በ2010 ዓ.ም. ለ1,200 ቤቶች ለዕድለኞች ዕጣ ወጣላቸው ተባለ፡፡ 

40 በመቶ ለቆጠበ ተመዝጋቢ ይተላለፋል የተባለው ቃል ተቀይሮ በተገላቢጦሽ 60 በመቶ የቆጠበ ተባለና ይህን ያደረጉም ቢሆኑ ምንም ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ 18,000 ተመዝጋቢዎች መቶ በመቶ መቆጠባቸው ቢነገርም፣ ነገሩ መና የቀረ እስኪመስል ድረስ ምንም ሳያገኙ ቀሩ፡፡ ታዲያ አንዱ እንኳ በቅጡ ሳይፈጽም የዚህ ፕሮግራም አስፈጻሚ አካል ምን እያወራ ይሆን? ለመልካም አስተዳደር ችግር መባባስ አስትዋፅኦ እያደረገ ስለመሆኑ አላሰበ ይሆን? ኃላፊነታቸውን የተው ተመዝጋቢዎች በመንግሥት ላይ እያንጎራጎሩ ስለመሆናቸው አላወቀ ይሆን? ሕዝብ ይታዘባል፡፡ ተቋራጩ የመንግሥት ችግር ነው ሲል መንግሥት በበኩሉ  ባገኘው አጋጣሚ የተቋራጭ ደካማነትና የግብዓት ችግር ነው ይላል፡፡ ታዲያ ገንዘባቸውን መቶ በመቶ ቆጥበው የሚጠባበቁት የማን ችግር ነው ይበሉ?

ቃልን ከተግባር ማዛመድ የማይቻለው ለምንድ ነው? የምንችለውን እንሥራ፡፡ ከእኛ በላይ በሆነው ችግር ታሪክም አይወቅሰንም፡፡ የሚገርመው ግን አንዳች ቤት ያላገኘ ተመዝጋቢ ቤቱን ሳያገኝና ሳይሠራለት በሌላ ጎኑ ግን የቤቱ ዋጋ ወለድ እየቆጠረበት መሆኑ ነው፡፡ ቃሉን ባላከበረው ወገን ችግር ምክንያት ተመዝጋቢው ላይ ወለድ መጣል ሕዝብን እያበሰጫም ወይ?  ችግሩን ቀስ ብላችሁ አስቡበት፡፡ አንዲት ነገር ሳይሠሩ ሁልጊዜ ተመሳሳይ ነገር መናገር  እኮ የቂል ሥራ ነው፡፡ ሰዉ ንግግራችሁን ከመታዘብ አልፎ ወደ አለመስማት ሄዷል፡፡ ስለሆነም እባካችሁ ቃላችሁን ከተግባር አዛምዱት፡

(ከታዛቢዎች)

***

ጃጋማ ኬሎን መዘከር የአንድ ኮሚቴ ግዴታ ብቻ አይደለም

ለዚህ ቁጭትና ትዝብት አዘል ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ ባለፈው ሳምንት የዝክረ ተና ጄነራል ጃጋማ ኬሎ ጊዜያዊ ኮሚቴ ለጠቅላይ ኒስት ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የጻፉት የተማፅኖ ደብዳቤ በሪፖርተር ጋዜጣ መውጣቱ ነው።

የደብዳቤው ጥቅል ሐሳብና የኮሚቴው ተማፅኖ በአጭር ቃልጠቅላይ ሚኒስትሩና የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእኚህ ኢትዮጵያዊ፣ አርበኛና ጀግና ተገቢውን ክብርና ሥፍራ እንዲያገኙ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በአጋርነት ከጎናቸው እንዲቆሙ የሚጠይቅ፣ የሚማጸን ነው፡፡

ኔራ ጃጋማ ኬሎን ለመዘከር የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮሚቴ፣ ባለፈው ዓመት 96 ዓመታቸው በሞት የተለዩንን እኚህ ጀግና ለመዘከር በቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ግርማ ልደ ጊዮርጊስ መኖሪያ ግቢ ውስጥ በተገነባውና የሰላም አዳራሽ የሚል ሥያሜ በተሰጠው መሰብሰቢያ ውስጥ ለመገናኛ ብዙኃን የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ ተከታትያለሁ። ኮሚቴው በመግለጫው ጀግናውን አርበኛ ጄነራል ጃጋማ ኬሎን በተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች ለመዘከር፣ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚገኘው መካነ መቃብራቸውም ላይ የመታሰቢያ ሐውልት ለማቆም፣ ጀግኖች አርበኞቻችንን በተመለከተም ዐውደ ርዕይና የታሪክ ሲምፖዚየም ማዘጋጀት ከዕቅዶቹ መካከል ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ከጥቂት ወራት በፊት ገልጸው ነበር።

ይሁን እንጂ ከወራት በኋላም የዝክረ ጄነራል ጃጋማ ኬሎ ኮሚቴ ከተናገራቸው ዕቅዶች አንዱም ተግባራዊ ሆኖ አላየንም። ሌላው ቢቀር በመካነ መቃብራቸው ላይ የመታሰቢያ ሐውልት እንዴት ሳያቆምላቸው ቀረ? ብዬ መጠየቄ አልቀረም። በሌላ በኩል ከበርካታ ወራት በኋላ ጊዜያዊ ኮሚቴው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የጻፈው ደብዳቤ፣ ዕቅዶቹን ተግባራዊ ለማድረግ እንቅፋት እንደገጠመው የሚያሳብቅ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ለሕዝባቸውና ለአገራቸው በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የላቀ ሥራ የሠሩና ታላቅ አስተዋፅኦ ያበረከቱ በርካታ ጀግኖቻችን ያለ ምንም መታሰቢያ ተረስተውና ተዘንግተው ቀርተዋል። በዱር በበረሃ ተንከራተው፣ ወጥተውና ወርደው፣ ደማቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው በነፃነቷ ታፍራና ተከብራ የኖረችውን ኢትዮጵያን ያስረከቡን ባለውለታዎቻችንና ጀግኖቻችን በመንግሥትም ሆነ በሕዝብ ዘንድ ተገቢው ትኩረትና ሥፍራ ተሰጥቷቸዋል ማለት የሚቻል አይመስለኝም።

ለአብነትም ለሬጌ የሙዚቃ ንጉሥ ለቦብ ማርሌይና ለሥነ ጽሑፍ ሊቁ ለፑሽኪን የመታሰቢያ ሐውልት አቁመናል፡፡ አደባባይ ሰይመናል፡፡ በአፍሪካ ኅብረት ግቢ ውስጥ ለጋናዊው ፓን አፍሪካኒስት ለክዋሜ ንኩርማ ሐውልት ያቆምን፣ የኅብረቱን የመሰብሰቢያ አዳራሽ በኔልሰን ማንዴላ ስም ሰይመናል፡፡ በሚገርም ሁናቴ ለማንዴላም ሆነ ለንኩርማ የነፃነት ትግል የወኔ ስንቅ፣ ለአፍሪካና ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነፃነት ቀንዲል ለለኮሰው የዓድዋ ድልና ለጥቁር ሕዝብ ሁሉ የነፃነት ኩራት ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ጀግኖቻችን ግን ተገቢውን ክብርና ሥፍራ በመስጠት ረገድ እምብዛም ነን ‹‹በገዛ ዳቦዬ ልብ ልቡን አጣሁት፤›› እንዲሉ አበው፣ የራሳችንን ዕንቁዎች በገዛ ምድራቸው መዘንጋታችን በእጅጉ የሚያሳዝን፣ የሚያስተዛዝብና የሚያስቆጭ ነው፡፡

ለዚህ ድክመታችንና ውድቀታችን ዋናው ማሳያ ታላቁን አርበኛ፣ የጦር መሪ፣ የዕርቅና የኢትዮጵያዊ አንድነት ተምሳሌት የሆኑትን ጀግና አርበኛ ሌተና ጄኔራል ጃጋማ ኬሎን ሌላው ቢቀር በመካነ መቃብራቸው ላይማስታወሻ የሚሆን ሐውልት ማቆም አለመቻላችን ነው፡፡

እኚህን ታላቅ አርበኛ ለመዘከር ግዴታውና ኃላፊነቱም የአንድ ኮሚቴና የጥቂት ግለሰቦች ብቻ ሊሆን አይገባውም። ታሪካቸውና ጀግንነታቸው እንደ ቢቢሲ ባሉ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ሳይቀር፣ ‹‹የፋሽስት ሥርዓትን በጽናት ታግለው ድል ያደረጉ አፍሪካዊ ጀግና፣ የጦር ሰው፤›› በማለት ያከበራቸውንና ሰፊ ሽፋን የሰጣቸውን ሌተና ጄኔራል ጃጋማ ኬሎን መንግሥትም ሆነ ሕዝብ ሊዘነጋቸው አይገባም።

የዝክረ ተና ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ ኮሚቴም እኚህን ታላቅ ጀግና ለመዘከር የጀመረውን እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ ሕዝብና ከመንግሥት ጋር ሆኖ ከግብ እንደሚያደርሰው ተስፋ አደርጋለሁ።

 (ኒቆዲሞስ፣ ከአዲስ አበባ)

***

ኮስሞቲክስ በጤና መነፅር ሲታይ

ንፅህናና ውበት መጠበቂያ ምርቶች በኩል በምግብና መድኃኒት ዘርፍ ያለውን እንቅስቃሴ ስንመለከት አገልግሎት ላይ መዋል ስላለበት የጊዜ ገደብ አጠቃቀም በተመለከተ ብረተሰቡም ሆነ በዘርፉ ተሰማርተው የሚገኙ አካላት ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች ተብራርቷል፡፡  የቆዳ፣  የፀጉርና የጥፍር ማስያ ምርቶች ጥቅም ላይ ሲውሉ፣ ከጤና አንር መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ የምግብና መድኃኒት ጽሕፈት ቤት ሥር የአካባቢ ጤና አጠባበቅ የብቃት ማረጋገጫ ኬዝ ቲም አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ ሳባ አበበ አብራርተዋል፡፡

 ‹‹አትኩሮት ሊሰጥባቸው ከሚገባቸው ውስጥ የላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ፣ መጠቀሚያ ጊዜ በምርቶቹ ላይ መታየት አለበት፡፡ መጀመያ የገባ መጀመያ ቢወጣ (First in- first out ዘዴን ብንጠቀም)፡፡ በቂ ማከማቻ መጋዘንና መደርደሪያ መኖሩ ተገቢነት ያለው ሲሆን፣ የማከማቻ ቦታው ሙቀት መጠን ከ15 እስከ 23 ድግሪ ሴንቲግሬድ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ለፀሐይ ብርሃን ያልተጋለጠ (ጨረር የማይደርስበት ቦታ) ቀመጥምርት መሸጊያዎቹ ላይ የሚኖሩ ጽሑፎች ለብረተሰቡ ግልጽ ሆነ ቋንቋ ቢጻጥሩ ነው፤›› ብለዋል፡፡

በኢትዮያ የተለያዩ የአቅርቦት ደረጃ ያላቸው የመገበያያ ሥፍራዎች አሉ፡፡ ከእነህ መካከል የተለያደረጃ ያቸው ሱፐር ማርኬቶች ይጠቀሳሉ፡፡ የሱፐር ማርኬቶች ሥርጭት እያደገ መጥጧል፡፡ ወ/ሮ ሳባ ከላይ እንደጠቀሱት፣ ምን ዓይነት ጥንቃቄ እየተደረገ እንደሚገኝ ግን እያንዳንዳችን ከምንሰማውና ከምናየው የምንሰጠው ምላሽ በቂ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡

የቆዳን እንዲሁም የፀጉርን ጤና ለመጠበቅ የምንገለገልባቸው ምርቶች ገበያ ላይ ይቀርባሉ፡፡ የእነኚህ ምርቶችን የአጠቃቀም የጊዜ ገደብን በተመለከተ የምርቶቹ ተጠቃሚዎች (ሸማቾች)፣ የምርት አቅራቢዎች፣ አምራቾች፣ የምርቶቹን ግብይትና የአጠቃቀም ደት የሚቆጣጠሩ መንግሥታዊ አካላትና ሌሎችም በዚህ ዙ በሙያ መስክ አትኩሮት ሊሰጣቸው ይገባል የሚሏቸውን ነጥቦች የሚጠቅሱት የቆዳ ሐኪሙ ዶ/ር ወንድማገኝ እንቢአ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ ‹‹የቆዳ፣ የፀጉር እንዲሁም የጥፍር መዋያ ውጤቶች (ኮስሞቲክስ) በውስጣቸው ከሚይዙት የኬሚካል ውህድ ቅንብር ጋር በተያያዘ የተለያዩ አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ይታወቃል፡፡ እነዚህ የኬሚካል ውህዶች ባላቸው የኬሚስትሪ ባህሪ እንደማንኛውም የመድኃኒትና የምግብ ውጤት ሳይበላሹ የምንጠቀምባቸው ውስን ጊዜ ይኖራቸዋል››

የኮስሞቲክስ ምርቶች የመጠቀያ ጊዜ ከሚወስኑት ነገሮች ዋነኛው መዋብያዎቹ ሲመረቱ ከማምረቻ ድርጅቱ የተሰጣቸው የመጠቀሚያ ጊዜ ቢሆንም ሁለተኛውና ብዙውን ጊዜ በአገራችን ትኩረት የማይሰጠው ግን፣ ኮስሞቲክሶቹ ከማጓጓዝ ጀምሮ እስከ መሸጫ ቦታ ባለው ሒደት አልፈው ለጥቅም የሚውሉበት መንገድ ነው፡፡ ምሳሌ የሚሆነን አብዛኛዎቹ የኮስሞቲክስ ውጤቶች ከ25 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በታች በሆነ ሙቀት ውስጥ ለፀይ ያልተጋለጠ እንዲሁም ያልተጨናነቀአየር እንደልብ ሚያስገባ ቦታ ወይም መደርደርያ ላይ መቀመጥ ገባቸውም ይህ ግን ሲሆን አይታይም፡፡ ከአጠቃቀም ጊዜ ጋር በተያያዘ በገራችን ከሚታዩ ዋና ዋና ችግሮች መካከል፡ ደንበኞች የመገልገያ ጊዜን ትኩረት አለመስጠትበአንዳንድ የኮስሞቲክስ ምርቶች ላይ የመገልገያ ጊዜ አለመ እንዲሁም ከወደብ ጀምሮ እስከ መሸጫ ቦታዎች ያሉ አያያአቀማመጥ ዘዴዎች ለብልሽት የሚዳርጉ ሆነው መገኘታቸው ነው፡፡

ምግብና መድኃኒት አጠቃቀምና አስተዳደርን እንዲቆጣጠር ላፊነት የተሰጠው ለኢትዮጵያ ምግብ፣ መድኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለልጣን ቢሆንም፣ ኮስሞቲክስን በተመለከተ ግን ግል ላፊነት የተሰጠው ተቋም የለም፡፡ ይህ ክፍተት በየጊዜው ችግር ያለባቸው፣ ጊዜ ያለባቸው እንዲሁም በተገልጋ ላይ ከፍተኛ ችግር እያመጡ የሚገኙ የመዋቢያ ምርቶች ሲያጋጥሙ ርምጃ የሚወስድ አካል አለመኖሩ ችግሩን የተወሳሰበ ያደርገዋል፡፡

እንደ የቆዳ ክምና ባለሙነቴ በየቀኑ በኮስሞቲክስ አጠቃቀም ምክንያት የፀጉር መበጣጠስ፣ የቆዳ መበላሸትና የጥፍር ጉዳት የደረሰባቸውን ተጠቃሚዎች በተለይም ሴቶችን አስተናግዳለሁ፡፡ አንዳንዶቹ ጉዳቶች በቆዳና በፀጉር ላይ የድሜ ልክ ጠባሳ ሲጥሉ እናስተውላለን፡፡

በአሁኑ ወቅት የኮስሞቲክስ ምርቶች መሸጥ ከሚገባቸው ውቅና ከተሰጣቸው ማዕከሎች ውጭየኪዮስኩ ከየት እንደመጡ የማናቃቸው ምርቶች መንገድ ዳር ሳይቀር በጠራራ ፀለበርካታ ነገሮች ተጋልጠው ሲሸጡ እናያለን፡፡ መዋቢያ ምርቶቹ ከታሰበላቸው ላማ ውጭ ሲውሉም የሚቆጣጠር ተቋም የለም፡፡ እንደ ባለሙያ ምግብና መድኒትን የሚቆጣጠር አካል እንዳለ ሁሉ የኮስሞቲክስ ምርቶችን ይዘት፣ አመጣጥ፣ አያያዝና አጠቃቀም የሚቆጣጠር አካል ቢኖር ስል እጠይቃለሁ፡፡

በመጨረሻ መላው ኅብረተሰቡና በዘርፉ ለተሰማሩ መንግሥትና የግል ተቋማት ለዚህ ችግር ምላሻችን ምን መሆን እንዳለበት ራሳችን እንጠይቅ እያልኩ በዚሁ አበቃሁ፡፡

                                  (መክሊት ጋረደው ገብረወልድ፣ ከአዲስ አበባ)