Skip to main content
x

የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

ሰባተኛው የሕዝባዊ ወያኔርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከፍተኛ አመራሮች ድርጅታዊ ኮንፈረንስ በመቐለ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተወሰኑ ውሳኔዎችን እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ለማስረፅ የሚረዳ አቅጣጫ የሚቀመጥበት እንደሆነ ተጠቁሟል።

ሐሙስ ጥር 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በተጀመረው ኮንፈረንስ ላይ ከክልሉ የተለያዩ ሥፍራዎች የተውጣጡ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው

ለተከታታይ ስምንት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ድርጅታዊ ኮንፈረንስ ላይ፣ የኢሕአዴግ እህትና አጋር ድርጅቶችየወከሉ 200 አመራሮችም እየተሳተፉ ነው።

የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የእህትና አጋር ድርጅቶች አመራሮችን ጨምሮ፣ ሁሉም አመራሮችና ተሳታፊዎች በነፃነትሳባቸውን እንዲያቀርቡና ጥልቅ ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

በዚህ ኮንፈረንስ የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ዘለግ ላሉ ቀናት ባካሄደው ግምገማ ወቅት በጥልቀት የለያቸውን ችግሮች፣ በተለይም በድርጅቱ ውስጥ የተከሰተውን የውስጥ ችግር ለመፍታት የሁሉም ድርሻ በመሆኑ ሁሉም ለዚህ ችግር መፍትሔ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ሊቀመንበሩ አሳስበዋል።

በማዕከላዊ ኮሚቴው ግምገማ ወቅት የአመራሩ ድክመት ድርጅቱን እንደ ጎዳው፣ የበላይ አመራሩም በዚህ ሲገመገም ብዙ ጉድለት እንደተገኘበት ሊቀመንበሩ አስታውሰዋል፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው ያካሄደውን ግምገማና ችግሮችን የመለየት ሥራ ተከትሎ እየተከናወነ ያለው የድርጅቱ ኮንፈረንስ፣ በድርጅቱ ውስጥና በከፍተኛ አመራሩ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመፍታትና ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የሚረዳ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ማዕከላዊ ኮሚቴው ባካሄደው ግምገማ መሠረት በግምገማው ወቅት ያልተለዩ አዳዲስ ሐሳቦች ያነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው የወሰናቸውን፣ እንዲሁም ከዚህ ኮንፈረንስ የሚነሱ ሐሳቦችን ጨምሮ እስከ ታችኛው የድርጅቱ መዋቅር ድረስ የሚወርድ ውይይትና የማጥራት ሥራ እንደሚከናወን ተጠቁሟል።

ከዚህ በፊት ሁሉንም ያሳተፈና ሐሳብ በነፃ የሚገለጽበት አካሄድ ባለመኖሩ፣ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ግብዓቶች እንዳይገኙ አድርጎ እንደነበር ሊቀመንበሩ ገልጸዋል።

ኮንፈረንሱወሓት ከድክመቱ እንዲወጣ ለማገዝ፣ ከሁሉም የኢሕአዴግ እህት ድርጅቶች ጋር ተቀራርቦ ለመሥራትና ለመደጋገፍ ወሳኝ እንደሆነ በአጽንኦት ገልጸዋል።

ሕወሓት በሕዝብ ዘንድ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ቆርጦ መነሳቱን በመግለጽ የወጣቶች የሥራ አጥነት ችግሮችን ለመፍታት ከወጣቶች ጋር ተቀራርቦ እንደሚሠራ የጠቆሙ ሲሆን፣ በተጨማሪም ምሁራንን በማሳተፍ ለልማትናዴሞክራሲድገት የሚያግዙ ጥናትና ምርምሮች ለማካሄድ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ድርጅቱ ቁርጠኛ መሆኑን በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት አስታውቀዋል።

ሰባተኛ ድርጅታዊ ኮንፈረንሱ የጥልቅ ተሃድሶ ሒደቱ ተጠናክሮ የሚቀጥልበት እንደሆነ፣ በክልሉና በአገሪቱ ላይ ያንዣበበውን አደጋ በሚገባ ገምግሞ መፍትሔና ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተጠቁሟል።

በኮንፈረሱ ላይ አቶ ስብሐት ነጋ፣ አቶ ሥዩም መስፍን፣ አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ እንዲሁም አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስን የመሳሰሉ ነባር የድርጅቱ አመራሮች ተገኝተዋል።

የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በቅርቡ ባካሄደው የ35 ቀናት ግምገማ፣ስና ግለ ሒስን ተከትሎ ዘጠኝ አባላት ያሉት የድርጅቱን አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ማካሄዱ ይታወሳል።

የትግራይ ክልል ምክር ቤት ሰሞኑን ባደረገው ስበሰባ የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤልን (ዶ/ር) ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መምረጡ የሚታወስ ሲሆን፣ እሳቸው የፕሬዚዳንቱን ሥራ በሙሉ ኃላፊነት እንዲያከናውኑ መወሰኑ አይዘነጋም፡፡ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ዓባይ ወልዱ ደግሞ ከፕሬዚዳንትነታቸው በምክር ቤቱ ተሰናብተዋል፡፡