Skip to main content
x
‹‹ላሊበላ ትናንትን ከዛሬ ጋር ያገናኘ መንፈሳዊ ድልድይ ነው!››

‹‹ላሊበላ ትናንትን ከዛሬ ጋር ያገናኘ መንፈሳዊ ድልድይ ነው!››

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነር፣ ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት መካከል ለቤተ ጐለጎታና ቤተ ሚካኤል ቤተ መቅደሶች ዕድሳት ማድረግ የሚያስችል የፕሮጀክት ስምምነት ጥር 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በተፈረመበት ወቅት የተናገሩት። ፕሮጀክቱ የሚከናወነው በአሜሪካ ኤምባሲ አማካይነት ከአሜሪካ አምባሳደሮች ድጋፍ (ፈንድ) ለባህላዊ ቅርሶች ከተሰኘው ተቋም በተገኘው ግማሽ ሚሊዮን ዶላር (13.7 ሚሊዮን ብር ግድም) እና ወርልድ ሞኒዩመንት ፈንድ በሚጨምረው 119,500  ዶላር ሲሆን፤ ስምምነቱን በላሊበላ ከተማ የተፈራረሙት የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣንና ወርልድ ሞኒዩመንት ፈንድ ናቸው፡፡ ፕሮጀክቱ የሚደገፈው በአሜሪካ ኤምባሲ፣ በወርልድ ሞኒዩመንት ፈንድ፣ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በላሊበላ ከተማ አስተዳደር፣ በአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መሆኑ ታውቋል፡፡