Skip to main content
x

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ

ከሁለት ዓመታት በፊት መስከረም 24 ቀን 2008 ዓ.ም. የፀደቀው የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ መግቢያ፣ የልማታዊ መንግሥት መርሆዎችን የተከተለ ጥብቅ ትስስርና ቅንጅታዊ አሠራርን መፍጠር፣ ጠንካራና ውጤታማ የአስፈጻሚ ተቋማት መዋቅርን መፍጠር፣ የተፈጥሮ ሀብቶችን በተገቢ ሁኔታ መጠቀም ለሚያስችል አደረጃጀት ትኩረት መስጠትና በውድድር ውስጥ ተፎካካሪ መሆንን ታሳቢ ያደረገ መዋቅር መመሥረት በማስፈለጉ አዋጁ መዘጋጀቱን ይገልጻል፡፡

በጃኖ የደመቀው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራ ክልል ጉብኝት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በጎንደር ከተማ ተገኝተው ከከተማዋና ከአጎራባች ወረዳዎች ከመጡ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡ ዓርብ ሚያዝያ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ከማለዳው የጀመረው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት፣ በመጀመርያ በአፄ ፋሲል ስታዲዮም ለተሰበሰቡ በሺዎች ለሚቆጠሩ የከተማዋና የአጎራባች ወረዳ ነዋሪዎች ንግግር አድርገዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀይ መስመሮች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ነባርና አዲስ አመራሮች ማድረግ ወይም ማለፍ የማይችሏቸውን ቀይ መስመሮች አሰመሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ያቀረቧቸውን የካቢኔ አባላት ማንነትና የሚሸጋሸጉ ሚኒስትሮችን ሐሙስ ሚያዝያ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት፣ ‹‹የሚሾሙትም ሆነ ባሉበት የሚቀጥሉት እንዲገነዘቡ የምፈልገው፣ ሕዝብ ቅሬታ የሚያቀርብበት የአገልግሎት አሰጣጥ ማስተካከል ግዴታና አንደኛው ቀይ መስመር ነው፤›› ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግሥትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ አመራሮችን ሾሙ

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተደርገው በተሾሙት አቶ አሰግድ ጌታቸው ምትክ የፐብሊክ ሰርቪስ፣ የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አዳሙ አያና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ተደርገው ተሾሙ፡፡

የፍትሕ ተቋማት በሚያገናኟቸው የሥራ ዘርፎች ውጤታማ ሥራ እያከናወንን ነው አሉ

አምስቱ የፍትሕ ተቋማት የሚባሉት የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያገናኟቸው የሥራ ዘርፎች ላይ ውጤታማ ሥራ እያከናወኑ መሆኑን አስታወቁ፡፡

የጋምቤላ ወጣቶች ማኅበር ንብረት በእሳት ወደመ

ሐሙስ ሚያዝያ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ለዓርብ አጥቢያ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ በተነሳ ቃጠሎ የጋምቤላ ክልል ወጣቶች ማኅበር ቢሮ ወደመ፡፡ በቃጠሎው የወጣቶች ማኅበር ቢሮ፣ የኮምፒዩተር ሳይንስ ማሠልጠኛና መዝናኛ ማዕከል ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገልጿል፡፡

አዳዲስ ሹመቶች ተሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 16 አዳዲስ ሹመቶችን ካፀደቁ በኋላ እስከምሽት ድረስ ሌሎች ሹመቶችን ያሳውቃሉ በተባለው መሠረት የሚከተሉትን ዘጠኝ ሹመቶች ሰጥተዋል፡፡

አዲስ አፈ ጉባዔ ተመረጡ

ላለፉት ስድስት ዓመታት አፈ ጉባዔ ሆነው ባገለገሉት አቶ አባዱላ ገመዳ ምትክ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሰየሙ፡፡ አቶ አባዱላ ከአፈ ጉባዔነት የተነሱት ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ጥያቄ ነው፡፡ ወ/ሮ ሙፈሪያት ቃለ መሃላ ፈጽመው ኃላፊነቱን ተረክበዋል፡፡