Skip to main content
x

ትጥቅ የመፍታት አተካራና የመንግሥት ተገዳዳሪነት

ሐሙስ ጥቅምት 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮችና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ላይ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ባሰሙት ንግግር ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በፓርላማ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ለተጠየቋቸው አሥር ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ ካነሷቸው ነጥቦች አንዱ በአንድ አገር ውስጥ በቡድን የመታጠቅ መብት ያለው መንግሥት ብቻ ነው የሚለው ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአውሮፓ ከሚኖሩ ከ20 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ በሚያደርጉት የአውሮፓ ጉበኝት ከ20 እስከ 25 ሺሕ የሚጠጉ በአውሮፓ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በጀርመን ፍራንክፈርት እንደሚገናኙና ንግግር እንደሚያደርጉ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየ15 ቀኑ በሚሰጠው መግለጫው አስታወቀ፡፡

ሰበር የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠበት የፍትሐ ብሔር መዝገብ አፈጻጸም ታግዶ በፎረንሲክ እንዲመረመር ትዕዛዝ ተሰጠ

በሥር ፍርድ ቤቶች ታይቶ መታረም እንዳለበት እየታወቀ ክርክሩ ሰበር ችሎት ድረስ ተጉዞ የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠበት የፍትሐ ብሔር ክርክር ሒደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ አፈጻጸሙ ‹‹የሰነድ ማስረጃው በፎረንሲክ ተመርምሮ ይቅረብ›› የሚል ትዕዛዝ ታግዶ በሥር ፍርድ ቤት መሰጠቱ እያነጋገረ ነው፡፡

‹‹ወጣቶች ለፖለቲካ ፍጆታ ከሚጠቀሙባቸው አካላት ራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው››

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ሐሙስ ጥቅምት 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በፓርላማ ተገኝተው፣ በሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች መክፈቻ ላይ ፕሬዚዳንቱ ባደረጉት ንግግር ላይ ከፓርላማ አባላት በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሁሉም ሲደመር እነሱ መቀነስ እንደሌለባቸው ተናገሩ

ቁጥራቸው በውል ባልታወቁ ሰዎች ግድያ፣ በከባድ የአካል ጉዳት፣ በሃይማኖት ተቋማት ቃጠሎ፣ በንብረቶች ውድመትና መፈናቀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት፣ ሁሉም በተደመረበት በዚህ ወቅት እነሱ መቀነስ እንደሌለባቸው ዓርብ ጥቅምት 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ለፍርድ ቤት ተናገሩ፡፡

የአዲስ አበባ ወጣቶችን በማደራጀት የተጠረጠሩ የሕግ ባለሙያ ታስረው ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው

በተለያዩ ክፍላተ ከተሞች የሚገኙ የአዲስ አበባ ወጣቶችን በማደራጀት፣ ብጥብጥና ሁከት ለማስነሳት ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋለሁ ያላቸውን አንድ የሕግ ባለሙያና አንድ ሌላ ግለሰብ ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ፣ መስከረም 8 ቀን 2011 ዓ.ም. ፍርድ ቤት አቀረባቸው፡፡ የጊዜ ቀጠሮም ጠይቆባቸው ተፈቅዶለታል፡፡

አዲሱ የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀትና አዳዲስ ባህርያቱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ ሁለተኛውን ሹምሽር አድርገውና የአስፈጻሚ አካላትን ብዛትም ቀንሰው ያቀረቡት አዋጅ ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በፓርላማው በሙሉ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን፣ በአስፈጻሚው አካላት ቁጥርና አደረጃጀትንና በካቢኔ አወቃቀሩ ላይ በርካታ አዳዲስ ክስተቶች ተስተውለዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ ካቢኔና አደረጃጀት

ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበው ረቂቅ ላይ በስፋት ውይይት ተደርጎ ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አዲሱ ካቢኔ በሙሉ ድምፅ ይሁንታ አግኝቶ ፀድቋል፡፡

ጦላይ ታስረው የከረሙት የአዲስ አበባ ወጣቶች በሁለት ቀናት ውስጥ ይፈታሉ

ከአንድ ወር በላይ በጦላይ ወታደራዊ ማሠልጠኛ የከረሙት 1,174 የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች፣ በሁለት ቀናት ውስጥ እንደሚፈቱ ተገለጸ፡፡ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ወጣቶቹ ሐሙስ ወይም ዓርብ እንደሚፈቱ ነው፡፡ ወጣቶቹ የታሰሩት ከየቤታቸው ታፍሰው ሳይሆን በጎዳና ላይ ነውጥ በማድረግ፣ ንብረት በማውደም፣ አካል በማጉደልና በፀጥታ ኃይሎች ላይ ድንጋይ በመወርወር ጉዳት በማድረሳቸው መሆኑን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወጣቶቹ ከታሰሩ ቀናት በኋላ መግለጹ ይታወሳል፡፡

ለተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ኩባንያዎች በመሀል አዲስ አበባ 36 ሔክታር መሬት ተዘጋጀ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ትዕዛዝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ለተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ባለሀብቶች የሚሰጥ 36 ሔክታር መሬት አዘጋጀ፡፡፡ ይህ ሰፊ መሬት የተዘጋጀው በመሀል አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ክፍላተ ከተሞች አንዱ በሆነው ቂርቆስ ለገሃር ባቡር ጣቢያ አካባቢ ነው፡፡ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ አልጋ ወራሽ ሼክ መሐመድን ቢን ዛይድ የሚመራ የልዑካን ቡድን፣ በቅርቡ አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡