Skip to main content
x

በሥራ ላይ ለነበሩና ለተሰናበቱ ስምንት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የአምባሳደርነት ሹመት ተሰጠ

የአምባሳደርነት ሹመት የተሰጣቸው በቅርቡ ከደኢሕዴን ሊቀመንበርነታቸው በፈቃዳቸው የለቀቁት የግብርናና እንስሳት ሀብት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ዓለማየሁ ተገኑ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ ያለው አባተ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ፣ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ ዮናስ ዮሴፍ፣ እንዲሁም አቶ እሸቱ ደሴና አቶ አዛናው ታደሰ ናቸው፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፍ በወጡ ላይ የፖሊስ መኪና የነዳው ግለሰብ ታስሮ ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀበት

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ድጋፍና ምሥጋና መስቀል አደባባይ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በወጣው ሕዝብ ላይ፣ ይዞት የነበረውን ላንድክሩዘር የፖሊስ መኪና ሆን ብሎ በመንዳት ጉዳት አድርሷል ተብሎ የተጠረጠረው ግለሰብ ፍርድ ቤት ቀርቦ ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀበት፡፡

በቂሊንጦ ብጥብጥ ተነሳ

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ቂሊንጦ እስረኛ ማቆያ ውስጥ ዓርብ ሐምሌ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ብጥብጥ መነሳቱ ታወቀ፡፡

የታሳሪ ቤተሰቦች ምግብ ለማድረስ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ በሥፍራው ቢገኙም እንዳይገቡ ተከልክለዋል፡፡ የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎችና አድማ በታኞች በግቢው ውስጥ እየተሯሯጡ ሲሆን፣ ከውስጥ የጩኸት ድምፅ እየተሰማ መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡ ጠያቂ ቤተሰቦችም የተፈጠረውን ባለማወቃቸው፣ በጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የተፈጠረውን ችግር በተመለከተ የማረሚያ ቤቱን ኃላፊዎች ምላሽ ማግኘት አልተቻለም፡፡

ተሰናባቹ ከንቲባ ቀጣዩ አስተዳደር ሊያተኩርባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ጠቆሙ

ተሰናባቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ሰኞ ሐምሌ 2 ቀን 2010 ዓ.ም. ለምክር ቤቱ ባቀረቡት የአምስት ዓመት የሥራ ዘመን ማጠቃለያ ሪፖርት፣ ቀጣዩ የከተማው አስተዳደር ነዋሪዎችን እያስጨነቁ የሚገኙ ችግሮች በተለይም ድህነት፣ ሥራ አጥነት፣ መልካም አስተዳደርና የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ላይ ትኩረት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳሰቡ፡፡

የብሔራዊ መግባባትና የዕርቅ ጉባዔ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው

የኢትዮጵያውያን ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መግባባት ዓለም አቀፍ አስተባባሪ ኮሚቴ፣ የነሐሴ ወር ከማለቁ በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ሁሉን አቀፍ የብሔራዊ መግባባትና የዕርቅ ጉባዔ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት መጀመሩን አስታወቀ፡፡